Author: hellodoc

 

ዛሬ በሆድ ድርቀት ላይ ምክሮች እንሰጥዎታለን፡፡ስለሆድ ድርቀትም ይሁን ስለሌላ የጤና ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 8896 ሃሎ ዶክተር ላይ በመደወል በቂ ልምድና ሙያ ያላቸዉን ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡ እርስዎን ለማማከር ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ፡፡

አንድ ሰዉ ለተከታታይ ሳምንታትና ከዚያ በላይ በቂ ጊዜ ሰገራ መዉጣት የሚያስቸግረዉ ከሆነ ወይም በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ የሚወጣ ከሆነ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት( Chronic constipation) አለዉ ተብሎ ይገለፃል፡፡
ጊዜያዊ የሆነ የሆድ ድርቀት ብዙ ጊዜ የሚከሰት ነገር ነዉ፡፡ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚከሰትበት ወቅት የታማሚዉን የዕለት ተዕለት የስራ እንቅስቃሴ ከማወኩም በላይ ታማሚዉ ሰገራ በሚወጣበት ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ የማስማጥና ሌሎች ምልክቶችም አሉት፡፡


የሆድ ድርቀት ምልክቶች


• በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ መዉጣት
• የደረቀ ሰገራ መዉጣት
• ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት ማስማጥ
• ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት አንዳች ነገር ደንዳኔዎትን የዘጋዉ ነገር ያለ ስሜት መሰማት
• ሰገራ ለመዉጣት እርዳታ መፈለግ(በእጅዎ ሆድዎትን መግፋት፣በጣትዎ ሰገራን ለማዉጣት መሞከር)


ለሆድ ድርቀት የሚጋልጡ ነገሮች


• በእድሜ መግፋት
• ሴት መሆን
• በቂ ፈሳሽ ያለመዉሰድ
• በፋይበር( fiber) የበለፀጉ ምግቦችን ያለመጠቀም(አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸዉን ምግቦች ማዘዉተር)
• አነስተኛ ወይም ምንም አይነት የአካል እንቅስቃሴ ያለማድረግ
• ለድርቀት ሊያጋልጡ የሚችሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡-ለምሳሌ የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ፣ለስነዓዕምሮ ችግሮች የሚሰጡ(ሴዳቲቭስና ናርኮቲክስ) የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡


የሆድ ድርቀት መንስዔዎች


የሆድ ድርቀት አብዛኛዉን ጊዜ የሚከሰተዉ ከምግብ መፈጨት በኃላ የሚቀረዉ ቆሻሻ ወይም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ(ጉዞ) በጣም ዘገምተኛ በሚሆንበት ወቅት ሲሆን የሚከተሉት መንስዔዎች አሉት፡-


ሀ. በትልቁ አንጀት ወይም በደንዳኔ ዉስጥ መዘጋት በሚኖርበት ወቅት


• የፊንጢጣ መቀደድ( Anal fissure)
• የአንጀት መታጠፍ
• የትልቁ አንጀት ካንሰር
• የትልቁ አንጀት ጥበት
• አንጀት ላይ ጭነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሌሎች የሆድ ዉስጥ ካነሰሮች
• የደንዳኔ ካንሰር
• በደንዳኔ ግድግዳ ለይ አድገዉ የሰገራን መተላለፊያ ሊዘጉ የምችሉ ነገሮች(ሬክቶ ሲል)


ለ. በትልቁ አንጀትና በደንዳኔ አካባቢ ባሉ ነርቮች ላይ ችግር በሚከሰትበት ወቅት


የነርቭ ችግር መኖር በዳንዳኔና ትልቁ አንጀት ጡንቻዎች ላይ መኮማተርን ስለሚያስከስት የሰገራን እንቅስቃሴ ይገድባል፡፡ ይህን ችግር ሊያስከስቱ ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ፡
• የህብለ ሰረሰር (Spinal cord) ጉዳት መኖር
• ስትሮክ( Stroke)
• የፓርኪንሰንስ ህመም
• አዉቶኖሚክ ንይሮፓቲይ የሚባል የነርቭ ህመም
• መልትፕል ስክሌሮሲስ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡


ሐ. ሰገራን ከሰዉነት ለማስወገድ በሚረዱ ጡንቻዎች ላይ ችግር መከሰት


• ሰገራን ለማስወገድ የዳሌ ጡንቻዎች መለጠጥ ያለመቻል( Inability to relax the pelvic muscles)—አንስመስ
• የዳሌ ጡንቻዎች በደንብ በተቀናጀ መልኩ ያለመለጠጥና ያለመኮማተር—–ዲሲነርጂ
• የዳሌ ጡንቻዎች መልፈስፈስ


መ. በሰዉነት ዉስጥ ባሉ ሆርሞኖች ላይ ችግር መከሰት


ሆርሞኖች በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ ፈሳሽ ተመጣጥኖ እንዲገኝ የሚያደርጉ ሲሆን ይህንን ስርዓት የሚያዛቡ ህመሞች ካሉ ለሆድ ድርቀት ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ፡-
• የስኳር ህመም
• የፓራታይሮይድ ዕጢ ችግር(ሃይፐርፓራታይሮይድዝም)
• እርግዝና
• የታይሮይድ ዕጢ ሆርሞኖች ማነስ(ሃይፓታይሮይድዝም)


የሆድ ድርቀት ህክምና


ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚኖርበት ወቅት ከሚመከሩ ነገሮች ዉስጥ የአመጋገብና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ሲሆን ይህም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚቆይበትን ጊዜ ይቀንሳል፡፡ይህን ማድረግዎ ለዉጥ ካላመጣ የህክምና ባለሙያ ማማከር ይጠበቅብዎታል፡፡


የህክምና ባለሙያዎት የሚከተሉትን ነገሮች ሊመክሮት ይችላል፡፡


• የፋይበር አወሳሰዶትን መጨመር እና በቂ ፈሳሽ መዉሰድ፡- ቀስ በቀስ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የጥራጥሬ ዘሮች በብዛት መመገብ
• የአካል እንቅስቃሴ ማዘዉተር፡- ይህ የአንጀትን የጡንቻዎችን እንቅስቃሴ ስለሚጨምር ድርቀትን ይከላከላል
• የሰገራ መምጣት ስሜት ባለዎት ጊዜ ሳያሳልፉ መዉጣት
• የሰገራ ማለስለሻ መጠቀም፡- ፋበሮች፣ሰገራ ማለስለሻ መድሃኒቶች፣ሰገራን ሊያላሉ የሚችሉ ነገሮችን መጠቀም( Stool softeners)
• የዳሌ ጡናቻዎች ስልጠና፡- በዚህ ረገድ በሰለጠኑ ባለሙያዎች በመታገዝ ሰገራን ከሰዉነት ለማስወገድ የሚረዱትን ጡንቻዎችን በማላላትና በማጠንከር ማሰልጠን ሰገራን በቀላሉ ለመዉጣት ይረዳል፡፡
• የቀዶ ጥገና፡-በቀዶ ጥገና ሊስተካከሉ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለምሳሌ የፊንጢጣ መቀደድ፣ሬክቶሴሌና የአንጀት ጥበት የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህ ሁኔታዎች ሲኖሩ የቀዶ ጥገና ባለሙያን ማማከር ይመከራል፡፡

Recent Posts

 

መጥፎ የአፍ ጠረን(ሃሊቶስስ) የአፍን ንፅህና በደንብ ካለመጠበቅ የሚከሰት ችግር ቢሆንም ሌሎች የአፍና የጥርስ ንፅህና ቢጠበቅም ለህክምና አስቸጋሪ የሆኑ መንስኤዎችም አሉት፡፡ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ከማስጨነቁም በላይ የታማሚዉን ሁለንተናዊ ግንኙነት (በትዳርም ይሁን በሌሎች ግንኙነቶች፤በስራ ቦታ) ሊጎዳ ይችላል፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡


• የአፍ ንፅህናን ያለመጠበቅ
• የድድ ህመም መኖር
• ሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በአፍና የአንጀት ክፍሎች ዉስጥ መራባት
• እንደ ካንዲዲያስስ ያሉ የፈንገስ ህመሞች መከሰት
• የሳይነስ እንፎክሽን
• መድኃኒቶች(በተለይ አፍን የሚያደርቁ መድሃኒቶች)
• ሲጋራ ማጨስ
• የተወሱ የምግብ አይነቶች(ነጭ ሽንኩርት፤ሽንኩርት፤ሰርዲን፤ከፍተኛ የገንቢ ምግብ(ፕሮትን) ያላቸዉ ምግቦች)
• የምግብ ያለመፈጨት ችግርና የጉበት ችግር
• የሆድ ድርቀት


መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት ሊያዉቁ ይችላሉ?


• መጥፎ ወይም የሚመር የአፍ ጣዕም ሲሰማዎት
• በጣም የሚመከረዉ ዘዴ ግን የሚያምኑት ሰዉ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደአለዎትና እንደሌለዎት እዉነቱን እንዲነግሮት መጠየቅ ናቸዉ፡፡


መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች/ምክሮች


• ምግብ ከተመገቡ በኃላ ጥርስዎትን መታጠብ(መቦረሽ)
• ቢያንስ በቀን አንዴ በጥርስ መካከል ያሉትን የምግብ ተርፍራፊ በጥርስ መጎርጎርያ ወይም ፍሎስ ማዉጣት
• ምላስዎትን መቦረሽ
• አርትፊሽል ጥርስ ወይም ድድ ካለዎት ማፅዳት
• የአፍ ድርቀትን መከላከል፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፤ዉሃ በብዛት መጠጣት(ቡና፣ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የአፍን መድረቅ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ስለዚህ አያዘወትሩ)፤ማስቲካ ማኘክ ወይም ከረሜላ መምጠጥ

Recent Posts

 

1.   ጭንቀት፡-

በሚጨናነቁበት ወቅት ሰዉነትዎ የተፈጠረዉን ጭንቀት ለመቀነስ የደም ስኳር መጠንዎን ይጨምራል፡፡ በቀን ውስጥ ለራስዎ ለ15 ደቂቃዎች ያህል ጊዜ በመስጠት ጭንቀትዎን መቀነስ ይችላሉ፡፡ ይህም ወክ ማድረግ፣ሙዚቃን በማዳመጥ አሊያም ፊልሞችን በማየት ሊሆን ይችላል፡፡

2.   የእንቅልፍ እጦት፡-

በዲያቤትክ ኬር ጆርናል ላይ በወጣዉ ጥናት መሰረት በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ሰዎች የሰዉነት ሴሎቻቸዉ የስኳርን መጠን ለሚቀንሰዉ ሆርሞን/ኢንሱሊን ስለማይታዘዙ/ሬዚስታንስ ስለሚፈጥሩ ለደም ስኳር መጠን መጨመር ምክንያት ይሆናል፡፡

3.  የወር አበባ ዑደት፡-

ብዙዎቹ የስኳር ህመም ያለባቸዉ ሴቶች በወር አበባ ዑደታቸዉ ወቅት የሆርሞን መጠን መዛባት ስለሚያጋጥማቸዉ የደም የስኳር መጠናቸዉ ይጨምራል፡፡በወር አበባ ዑደትዎ ወቅት የኢስትሮጂንና ፕሮጀስትሮን ሆርሞን መጠን መጨመርና መቀነስ ስለሚታይባቸዉ የኢንሱሊን ሆርሞን እንዳይሰራ/ሬዚስታንስ እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡

4.  የፈሳሽ እጥረት፡-

የስኳር ህመምተኛ ከሆኑ በቀን ዉስጥ በቂ ፈሳሽ መዉሰድ ይጠበቅብዎታል፡፡ ምክንያቱም ሰዉነትዎ ፈሳሽ ሲያጥረዉ በደም ዉስጥ ያለዉ የስኳር መጠን ሲለሚያይል የስኳር መጠኑ ይጨምራልና፡፡

Recent Posts

 

ብዙ ሴቶች በግብረስጋ ግንኙነታቸዉ ላይ የሆነ ጊዜ ችግር ሊገጥማቸዉ ይችላል፡፡ የሴቶች የወሲብ ችግር በህይወት ዘመናቸዉ በየትኛዉም ጊዜ ሊከሰት የሚችል ሲሆን የችግሩ ምልክቶች እንደሚከሰተዉ የግብረስጋ ግንኙነት ችግር አይነቶች ሊለያይ ይችላል፡፡

አነዚህም ችግሮች

· የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ
· የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መነቃቃት ችግር/ Sexual arousal disorder
· የእርካታ ችግርና
· በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም መኖር ናቸዉ፡፡

የወሲብ ችግር ምክንያቶች

· ስነልቦናዊና ማህበራዊ፡- ህክምና ያልተደረገለት ጭንቀት/ድብርት ና ለረጅም ጊዜ የቆየ መጨናነቅ ወይም ከዚህ በፊት ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የደረሰባት ችግር (መደፈር) ከነበረ ለችግሩ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
· የሆርሞን መለዋወጥ፡-ከማረጥ ጋር በተያያዘ በሰዉነትዎ ዉስጥ የሚገኘዉ ኢስትሮጂን ሆርሞን መጠን መቀነስ በብልትዎ አካባቢ የሚገኙ አካላት ላይ ለዉጥ እንዲከሰት ስለሚያደርግ
· አካላዊ ችግሮች፡- ማንኛዉም የዉስጥ ደዌ ችግሮች የግብረስጋ ግንኙነት ችግሮችን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡

 

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች

የሴቶች የወሲብ ችግሮች ብዙ አይነት የህመም መገለጫ፣ የህመም ምክንያቶችና ህክምናዎች አላቸዉ፡፡ ስለሆነም ለግብረስጋ ግንኙነት ችግሮችዎ መፍትሄ ለማግኘት የህክምና ባለሙያዎን ማነጋገር ያስፈልጋል፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና፡- የግብረስጋ ግንኙነት ጤንነትዎን ለመገንባት የሚከተሉትን ጤነኛ ባህሪያቶችን ማዳበር ያስፈልጋል፡፡
· ከመጠን ያለፈ አልኮሆል ያለመዉሰድ፡- ከመጠን ያለፈ አልኮሆል መዉሰድ የግብረስጋ ግንኙነት ተነሳሽነትዎን ይቀንሳል፡፡
· ሲጋራ ያለማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ በሰዉነትዎ ዉስጥ የሚደረገዉን የደም ዝዉዉርን ይቀንሳል፡፡ ስለሆንም ወደብልትዎ የሚሄደዉን የደም ዝዉዉር ስለሚቀንሰዉ የግብረ ስጋ ግንኙነት መነቃቃትንና እርካታን ይቀንሳል፡፡
· የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘዉተር፡- ተከታታይነት ያለዉ የኤሮቢክስ እንቅስቃሴ ስሜትዎን ስለሚቀሰቅስና ስለራስዎ የሰዉነት አቋምልከታ እንዲቀየር ስለሚያደርግ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
ሰዉነትን ለማፍታታተትና ዘና ለማለት ጊዜ መስጠት፡- እንዴት ዉጥረትን መቀነስና ሰዉነትዎን ዘና እንደሚያደርጉ ማወቅ፡፡ ዘና ሲሉ በግብረስጋ ግንኙነት ልምድዎ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ከመርዳቱም በላይ የተሳካ የግብረ ስጋ ግንኙነት መነቃቃትና እርካታ እንዲኖርዎ ያግዛል፡፡

Recent Posts

1913939_616443121853245_8719117733515090853_n

የአይን አለርጂ የሚከሰተው አይንዎ ላይ የመቆጥቆጥ ስሜት እንዲሁም የመቅላት ባህሪይ ሲከት ሲሆን ይህ ችግር ህፃናትንና አዋቂዎችን ያጠቃል፡፡ዋነኛዎቹ የህመሙ መገለጫዎች የአይን መቅላትና ከአይን ፈሳሽ ሲኖር መኖር ናቸዉ፡፡

የህመሙ መንስኤ፡-

የአይን አለርጂ የሚከሰተዉ አለርጂዉ እንዲከሰት የሚያደርጉ አለርጂኖች በንፋስ ምክንያት ወደ አይንዎ በሚገባበት ወቅት ነዉ፡፡የህመሙ ምልክቶች አለርጂዉን በሚያመጡ/አለርጂኑን ተከትለዉ የሚከሰቱ ሲሆን በድንገት የሚጀምሩ፣ወቅትን ተከትለዉ አሊያም አመቱን በሙሉ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡


የህመሙ ምልክቶች፡-


በብዛት ከሚታዩት የአይን አለርጂ ምልክቶች ዉስጥ የአይን መቅላት፣ዉሃ የመሰለ የአይን ፈሳሽና ሁለቱንም አይን ማሳከክ ናቸዉ፡፡ሌሎቹ የህመም ምልክቶች ብርሃን ሲያዩ ማቃጠልና የአይን ቆብ እብጠት መከሰት ናቸዉ፡፡ችግሩ ብዙዉን ጊዜ ሁለቱንም አይን የሚያጠቃ ቢሆንም ህመሙ በአንደኛዉ አይን ሊብስ ይችላል፡፡ ዐይንን ማሸት የህመሙ ምልክቶች እንዲባባሱ ያደርጋል፡፡

Recent Posts

12419291_620615218102702_8875992845249531341_o

 

እንቅርት የታይሮይድ እጢ በሚያብጥበት ወቅት የሚከሰት ህመም ነዉ፡፡የታይሮይድ እጢ በአንገት ላይ በፊትለፊት በኩል የሚገኝ አካል ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

ሁሉም የእንቅርት ችግሮች የህመም ምልክቶች ላይኖራቸዉ ይችላል፡፡የህመም ምልክቶች ከታዩ ደግሞ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡፡
·የሚታይ የአንገት ላይ እብጠት
·ጉሮሮዎ ላይ የመወጠር ስሜት መኖር
·ማሳል
·የድምፅ መጎርነን
·የመዋጥ ችግር
·የመተንፈስ ችግር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡


ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች


·በምግብዎ ዉስጥ የአዮዲን ንጥረነገር ከሌለ፡-አዮዲን በበቂ መጠን በማይኖርበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እና በአዮዲን የበለጸጉ ምግቦችን ማግኘት በማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡
·ሴት መሆን፡- ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለታይሮይድ እጢ ችግሮች የተጋለጡ ስለሆኑ ከወንዶች ይልቅ ለእንቅርት የመጋለጥ እድላቸዉ የሰፋ ነዉ፡፡
·እድሜ፡- እድሜ እየጨመረ በመጣ ቁጥር እንቅርት የመከሰቱ እድል እየጨመረ ይመጣል፡፡
·መሰል ችግር በቤሰብ ዉስጥ ከነበረ
·እርግዝናና ማረጥ፡- መክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ እንቅርት በነፍሰጡሮችና ባረጡ ሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል፡፡
·መድሃኒቶች፡- የበሽታ መከላከልን የሚቀንሱ መድሃኒቶች፣የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒቶችና ለልብ ችግር የሚሰጠዉ እንደ አሚዳሮን እንዲሁም ለስነአዕምሮ ችግር የሚሰጠዉ ሊቲየም እንቅርትን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡
· ለጨረር መጋለጥ


ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች፡-


የእንቅርት ህክምና እንደ እንቅርቱ መጠን፣የህመም ምልክትና እንቅርቱ እንዲከሰት እንዳደረገዉ መሰረታዊ ችግር ሊለያይ ይችላል፡፡ ስለሆን የህክምና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ዘዴዎች ሊከተሉ ይችላሉ፡፡
·በቅርበት መከታተል፡- የእንቅርትዎ መጠን አነስተኛ ከሆነ፣ህመም ከሌለዉና ስራዋን በአግባቡ እየተወጣች ከሆነ የህክምና ባለሙያዎ መከታተሉን ብቻ ሊመርጡ ይችላሉ፡፡
·መድሃኒቶች፡- የታይሮይድ ዕጢዉ የሚያመነጨዉ ሆርሞን መጠን ማነስ/መብዛት ካለዉ መድሃኒቶች ሊጀመርልዎ ይችላል፡፡
·የቀዶ ጥገና
·ራዲዮአክቲቭ አዮዲን የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

Recent Posts

3 year old baby

ከዚህ በፊት የህፃን ልጅዎን የአጨዋወት፣ አነጋገር/ ቋንቋ፣ እንዴት እንደሚማር እና እንቅስቃሴዎችን እንዴት እንደሚተገብር በመከታተል ስለልጅዎ የእድገት ሁኔታ ፍንጭ ማግኘት እንደሚቻልና የሁለት አመት ህፃን ሊያሳይ የሚችላዉን ነገሮች መነጋገራችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዚያ የቀጠለ የሦስት አመት ልጅ የእድገት ክትትልን እናያለን፡፡

ሕፃናት በዚህ እድሜ ምን ነገሮችን ሊተገብሩ ይችላሉ?

 

ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional

· አዋቂዎች የሚያደርጉትን ነገር መኮረጅ መቻል

· በጨዋታ ዉስጥ ተራን መጠበቅ

· ለሚያለቅስ ጓደኛዉ መጨነቅ

· የሱ፣ የሷ እና የእርሱ የሚባሉትን ሃሳቦች መረዳት መቻል

· የተለያዩ ስሜቶችን ማንፀባረቅ መቻል

· ከእናትና አባት በቀላሉ መለየት መቻል

· በእለት ከእለት ልማዶቹ ከፍተኛ ለዉጥ ሲደረግ መናደድ መቻል

· ልብሶቹን መልበስና ማዉለቅ መቻል

 

ቋንቋ /መግባባት (Language/Communication)

· ባለሁለት ወይም ሶስት ደረጃ ትእዛዞችን መከተል መቻል

· ብዙዎቹን ሊታወቁ የሚችሉ ነገሮችን ስም መጥራት መቻል

· ከላይ፣ ዉስጥ ወይም ከስር የሚባሉትን ቃላት መረዳት መቻል

· ስም ከነአባቱ እድሜዉንና ፆታዉን መናገር መቻል

· ጓደኛዉን በስሙ መጥራት መቻል

· እኔ፣እኛ፣ አንተ እና የተወሰኑ ብዙ ቁጥር ያላቸዉ ነገሮችን ማለት መቻል( መኪናዎች፣ድመቶች ወዘተ)

· ስልእንግዳ ሰዎች ለማወቅ/ለመረዳት በደንብ ማዉራት መቻል

· እስከ ሁለት አረፍተነገር ድረስ ንግግሮችን ማድረግ መቻል

 

አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና ችግርን መፍታት መቻል)

· መጫወቻን ከሚቆለፉና ከሚንቀሳወሱ ነገሮች መስራት መቻል

· ሁለት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት መቻል

· የመፅሀፍ ገፆችን አንድ ባንድ መግለጥ መቻል

· የበር እጀታን ማዞር መቻል

እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development

· ደረጃን መዉጣት መቻል

· በቀላሉ መሮጥ መቻል

·ደረጃን በሚወጣበትና በሚወርድበት ወቅት በአንድ እግሩ ደረጃዎቹ ላይ መዉጣት ወይም መዉረድ መቻል

Recent Posts

7237005_m

ጨዉ ለረጅም ጊዜ የሚታወቀዉ  በደም ግፊት ጤንነት ላይ የረጅም ጊዜ ጠላትነት እንደላለቸዉና ችግር እንደሚፈጥር ነዉ ፡፡ ምንም እንኳ ሶዲየም ለሰዉነታችን ከሚያስፈልጉ አስፈላጊ ንጥረነገሮች ዉስጥ ቢመደብም ከመጠን በላይ ይህን ንጥረነገር መዉሰድ የደም ግፊትን እንደሚጨምር በጥናቶች ተረጋግጧል፡፡ ከመጠን ያለፈ ጨዉ (ሶዲያም) መመገብ የደም ግፊቱን እንኳ ባይጨምር በልብ፣ በደም ቧንቧ፣ በኩላሊትና በአእምሮ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡

ጨዉ በልብ፣ በደም ስሮች፣ በአእምሮና ኩላሊትዎ ላይ የሚኖረዉን ጫና/ጉዳት ለመቀነስ/ ለመከላከል

የቤት ምግብ መመገብ፡-

በቤትዎ የተሰራን ምግብ ሲመገቡ ምን ያህል ጨዉ ምግብዎ ላይ እንደሚጨምሩ መቆጣጠር ስለሚችሉ የቤት ምግብ ለመመገብ ይሞክሩ፡

አትክልት፣ ፍራፍሬና ሌሎች የምግብ ይዘታቸዉ ጥሩ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር

የተመጣጠነ የምግብ ይዘት ስለሚኖራቸዉና በዉስጣቸዉ እንደፖታሲየም ያሉ ንጥረነገሮችን ስለሚኖራቸዉ ለደም ቧንቧ ጤንነት መልካም ነገሮች ናቸዉ፡፡

Recent Posts

18815668_l

የታለበ የእናት ወተት ምን ያህል ጊዜ ማቆየት እንደሚችሉ የሚወሰነዉ የሚያስቀምጡበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ለጤነኛ ህፃናት የሚከተለዉን መመሪያ መከተል ይችላሉ፡፡

በቤት ሙቀት ማስቀመጥ/ Room temperature፡-

በቅርቡ የታለበ/ትኩስ/ የእናት ወተት ፍሪጅ ዉስጥ ሳይገባ/በቤት ሙቀት ካስቀመጥነዉ እስከ 6 ሰዓታት ድረስ መቆየት ይችላል፡፡ ነገር ግን የክፍሉ ሙቀት ከፍተኛ ከሆነ መቀመጥ ያለበት እስከ 4 ሰዓታት ነዉ፡፡

 

በፍሪጅ ዉስጥ፡-

ትኩስ የታለበ የእናት ወተት በፍሪጅ ዉስጥ በንጽህና ከተቀመጠ እስከ 5 ቀናት መቆየት ይችላል፡፡ ነገርግን በፍሪጅ ዉስጥ የተቀመጠ የእናት ወተትን በ 3 ቀናት ዉስጥ ቢጠቀሙት ይመረጣል፡፡

 

ዲፕ ፊሪዘር(የበረዶ ሰንሰለት)/Deep freezer፡-

ትኩስ የታለበ የእናት ወተት በዲፕ ፈሪዘር ዉስጥ እስከ 12 ወራት ድረስ ሊቀመጥ/ማስቀመጥ ይችላል፡፡ ነገርግን በዲፕ ፍሪዘር ዉስጥ የተቀመጠ የእናት ወተትን በ 6 ወራት ዉስጥ ቢጠቀሙት ይመረጣል፡፡

 

መገንዘብ የሚገባዎ ነገር ቢኖር የእናት ጡት ወተት ለረጅም ጊዜ ታልቦ በቆየ ቁጥር/በፍሪጅ ዉስጥም ይሁን በዲፕ ፍሪዘር ዉስጥ/ በዉስጡ ያለዉን ቫይታሚን ሲ እያጣ ሊመጣ ይመጣል፡፡እናት ጡት ወተት መልክ እናትየዋ እንደምትመገበዉ የምግብ አይነት ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ሌለኛዉ ታልቦ የቆየዉ የእናት ወተት ትኪስ ከታለበዉ ወተት ጋር ሲነፃፀር በመልክና በይዘቱ ሊለያይ ይችላል፡፡ ይህም ቢሆን ህፃኑ ላይ የሚያመጣዉ ጉዳት ስለሌለዉ መመገብ ይችላሉ፡፡ ታልቦና በፍሪጅ ዉስጥ የቆየዉን ወተት ልጅዎ አልጠጥም ካለዎ የቆይታዉን ጊዜ መቀነስ ይችላሉ፡፡

Recent Posts