Author: hellodoc

 

የአጠቃቀም ሁኔታ፡-

የወሊድ መከላከያ እንክብሎች አስተማማኝና የማይጎዱ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዴትና መቼ እንደሚወሰዱ እና ምን አይነት ዉጤት እንደሚኖራቸዉ/እንደሚጠበቅ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

• መድሃኒቶቹን መዉሰድ በጀመሩ በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የማቅለሽለሽ ስሜቶችን ለመቀነስ/ለመከላከል እንክብሎችን ከምግብ ጋር መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡መድሃኒቱን በመኝታ ሰዓት አሊያም በተከታታይነት ከወሰዱ የማቅለሽለሽ ስሜቶቹ ይጠፋሉ፡፡

• የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን መዉሰድ ሲጀምሩ ሰዉነትዎ እስኪለማመድ ድረስ መድሃኒቶቹ ለመስራት 7 ቀናት ይፈልጋል/ያስፈልጋል፡፡ስለሆነም ለመጀመሪያዎቹ 7 ቀናት ተጨማሪ/ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል( ለምሳሌ ኮንደም)፡፡


• በመድሃኒቶቹ ምክንያት የሚከሰትን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስና እርግዝናን ለመከላከል እንክብሎቹ መወሰድ ያለባቸዉ 24 ሰዓታት ባልበለጠ ልዩነት መሆን አለበት፡፡


• መድሃኒቶቹን በመጀመሪያዉ የማስቀመጫ ስፍራ/እቃ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፤
መድሃኒቶቹም መወሰድ ያለባቸዉ መያዣዉ ላይ በተቀመጠዉ ትዕዛዝ መሰረት መሆን አለበት፡፡


እንክብል ሳይወስዱ ቢረሱ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?


• አዲስ እየጀመሩ ካለዉ ዉስጥ የመጀመሪያዋን እንክብልና አንድ እንክብል ከመሃሉ ቢረሱ፡-

የረሱትን እንክብል ባስታወሱበት ሰዓት መዉሰድና ቀጣዩን በመደበኛ ሰዓቱ መዉሰድ፡፡ በቀን ዉስጥ ሁለት እንክብል በአንዴ መዉሰድ ይቻላል፡፡ከዚያን ቀሪዉን መደበኛዉን ጊዜ ተከትሎ መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡ መድሃኒቱን መዉሰድ ከጀመሩ ለ7 ቀናት ያህል ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ (ለምሳሌ ኮንደም) መጠቀም ያስፈልጋል፡፡


• የወሊድ መከላከያ እንክብል መዉሰድ በጀመሩ የመጀመሪያዉ ወይም ሁለተኛዉ ሳምንት ዉስጥ በተከታታይ ሁለት እንክብል መዉሰድ ቢረሱ፡-

ባስታወሱበት ቀን 2 እንክብሎችን በሚቀጥለዉ ቀን ደግሞ 2 እንክብል መዉሰድ፤ ከዚያን አንድ እንክብል በየቀኑ መቀጠል፡፡ ሌላ አዲስ የወሊድ መከላከያ እስኪጀምሩ ድረስ ሌላ የወሊድ መከላከያ( ለምሳሌ ኮንደም) በተጨማሪነት መጠቀም


• መከላከያ መዉሰድ በጀመሩ በሶስተኛዉ ሳምንት 2 እንክብል በተከታታይነት አሊያም ሶስትና ከዚያን በላይ እንክብሎችን በተከታታይነት በየትኛዉም ወቅት መዉሰድ ቢረሱ:


አሁን እየወሰዱ ያለዉን/መዉሰድ የጀመሩትን ሙሉ በሙሉ ትተዉ አዲስ የወሊድ መከላከያ እንክብል በአዲስ መልክ መጀመር፡፡ አዲስ ከጀመሩት እንክብሎች ለ7 ቀናት መዉሰድ እስኪችሉ ድረስ ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ (ለምሳሌ ኮንደም) በተጨማሪነት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በዚህኛዉ ወቅት የወር አበባ ዑደትዎ ላይኖር ይችላል፡፡ በተከታታይነት ለሁለት ወራት ከሌለ ግን የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ስፈልጋል፡፡
የትኛዉንም ከ28 ቀናት ሳይክል/ዑደት ዉስጥ ከሚወሰዱት የመጨረሻዎቹ 7 እንክብሎች ዉስጥ አንዱን ቢረሱ ሊፈጠር የሚችል የእርግዝና ስጋት የለም፡፡ ነገር ግን የትኛዉም እንክብል ሳይወሰድ ቢቀር፤ የሚቀጥለዉ ወር የመጀመሪያዉ ቀን የወሊድ መከላከያ እንክብል በቀኑ መወሰድ መጀመር አለበት፡፡
እርግዝናን የመከላከል ብቃት ያላቸዉና የሌላቸዉ እንክብሎች በተለያየ ቀለም የተሰሩ ናቸዉ፡፡

Recent Posts

 

የታይፎይድ ህመም እያደጉ ባሉ ሃገሮች ዉስጥ  በተለይ በህፃናት ላይ ከፍተኛ የጤና ጉዳት ሊያመጣ የሚችል የህመም አይነት ነዉ፡፡ ህመሙ የሚከሰተዉ ሳልሞኔላ ታይፊ በሚባል የባክቴሪ አይነት ሲሆን ህመሙ ከታማሚዉ ሰዉ ወደ ጤነኛዉ ሰዉ በተበከለ ዉሃና ምግብ አማካይነት ይተላለፋል፡፡

 

የህመሙ ምልክቶች

  • ሲጀምር መጠነኛ ሆኖ እያደር እየጨመረ የሚመጣ ትኩሳት
  • የራስ ምታት
  • መደካከምና የሰዉነት መዛል
  • የጡንቻ ላይ ህመም
  • ማላብ
  • ደረቅ ሳል
  • የምግብ ፍላጎት መቀነስና ክብደት መቀነስ
  • የሆድ ህመም
  • ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት መከሰት
  • የሆድ መነፋት የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

ሕመሙ የሚተላለፍባቸዉ መንገዶች

የታይፎይድ ህመምን የሚያመጣዉ ባክቴሪያ የሚተላለፈዉ በተበከለ ዉሃ ወይም ምግብና አንዳንዴ ደግሞ ከታመመዉ ሰዉ ጋር በሚኖረን ቀጥተኛ ግንኙነት አማካይነት ነዉ፡፡

 

ለህመሙ የሚያጋልጡ ነገሮች

  • የታይፎይድ በሽታ ሁሌ በሚታይባቸዉ አካባቢዎች መስራት ወይም መሄድ
  • በታፎይድ ከተያዘ ሰዉ ጋር ቅርበት ያለዉ ግንኙነት/close contact/ መኖር
  • የተበከለ ዉሃ መጠጣት (በተለይ ከተበከለ ቱቦ ጋር የሚገናኝ ከሆነ)
  • የተበከሉ ምግቦችን መመገብ ናቸዉ፡፡

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች

ህመሙን ለመፈወስ ብቸኛዉ መንገድ ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መዉሰድ ስለሚያስፈልግ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

 

የቤት ዉስጥ ህክምና

  • ፈሳሽ በበቂ መጠን መዉሰድ/መጠጣት፡- ይህ በትኩሳት ምክንያት ሊከሰት የሚችለዉንየሰዉነት ፈሳሽ እጥረትን ሊያስቀር ስለሚችል ነዉ፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ/ከመጠን ያለፈ የፈሳሽ እጥረት ካለዎ በደም ስር ፈሳሽ መዉሰድ አአስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ወደ ህክምና ድርጅት መሄድ ያስፈልጋል፡፡

ታይፎይድን እንዴት መከላከል ይቻላል?

    የእጅ ንፅህናዎን መጠበቅ፡-

  • ታይፎይድ ኢንፌክሽንን ለመከላከል አስተማማኙ መንገድእጅን በዉሃና በሳሙና መታጠብ ነዉ፡፡ ምግብ ከመመገብዎና ከማዘጋጀትዎ በፊት እንዲሁም መፀዳጃ ቤት ተጠቅመዉ ከወጡ በኃላ እጅን በደንብ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ ዉሃ ማግኘት በማይችሉበት ወቅት አልኮሆል ያላቸዉ የእጅ ማፅጃዎች/ሃንድ ሳኒታዘሮች/ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

    ያልታከመ ዉሃ ያለመጠጣት፡-

  • ታፎይድ የሚዛመተዉ በተበከለ ዉሃ ስለሆነ መጠጣት የሚያስፈልገዉ ፈልቶ የቀዘቀዘ ዉሃ አሊያም የታሸገ ዉሃ ቢሆን ይመከራል፡፡

    ጥሬ የሆኑ አታክልትና ፍራፍሬዎችን በደንብ በንፅህና አጥቦ መጠቀም፡፡

  • ይህን ማድረግ ካልቻሉና አታክልቱ ንፁህ በሆነ ዉሃ ያልታጠበ ከሆነ አሊያም እርግጠኛ ካልሆኑ ጥሬ አትክልትና ፈራፍሬዎችን አለመጠቀም ይበጃል፡፡

Recent Posts

 

የማስታወስ ችሎታ እንዳይቀንስ ለመከላከል የሚረዳ ይህ ነዉ የሚባል አስተማማኝ መንገድ ባይኖርም የሚከተሉትን መንገዶች ቢተገብሩ የማስታወስ ችሎታዎን ለመጠበቅና ለማሻሻል ሊረዳዎ ይችላል፡፡

ንቁ አዕምሮ እንዲኖርዎ ማድረግ፡-

ልክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሰዉነትዎን ቅርፅ ለመጠበቅ እንደሚረዳዎ ሁሉ አዕምሮዎን ሊያነቃቁ የሚችሉ ድርጊቶች/ባህሪያት ማከናወን አዕምሮዎ ንቁ ሁኖ እንዲቆይ ሊደርግዎ ይችላል፡፡


ከሰዎች ጋር ያለዎ ተግባቦት በመደበኛ ሁኔታ እንዲኖርዎ ማድረግ፡-

የማስታወስ ችሎታዎን ሊቀንሱ የሚችሉ እንደ ጭንቀትና ድብርት ያሉ ሁኔታዎችን ለመመቀነስ ከሚረዱ መንገዶች አንዱ እለት ከእለት ከሰዎች ጋር ያለዎ ግንኙነት ነዉ፡፡ ስለሆነም በተለይ ብቻዎን የሚኖሩ ከሆነ በተቻለዎ መጠን ከሚወዱት ጋር፣ ከጓደኞችዎ ወይም ከሌሎች ጋር ሊያገናኝዎ የሚችሉ እድሎችን መፈለግና መጠቀም፣ የተለያዩ ግብዣዎች ( ምግብ አብሮ መመገብ፣ ሲኒማ መግባትም) ላይም ይሁን ሌሎች ሁነቶችም ካሉ መሄድ/መካፈል


እራስን አስቀድሞ ማዘጋጀት/ Get organized፡-

የሚኖሩበት ቤትዎ ወይም የሚይዙት ማስታወሻ የተተራመሰ/የተዘበራረቀ ከሆነ ነገሮችን በቀላሉ እንዲረሱ ያደርግዎታል፡፡ ስለሆንም የሚሰሩ ስራዎች ፣ ቀጠሮም ይሁን ሌሎች ጉዳዮች ካሉ ለየት ባለ ማስታወሻ ደብትር፣ ካላንደር ወይም ኤልክትሮኒክ ማስታወሻ መያዣ ላይ መያዝ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ የመዘገቡትን ነገሮች ደጋግመው ማለት፡፡ የተከናወኑና ያልተከናወኑ ነገሮችን በየግዜዉ መለየት፡፡ የኪስ ቦርሳዎን፣ ቁልፎችንና ሌሎች ጠቃሚ ነገሮችን የሚስቀምጡበት የተወሰነ ቦታ ይኑርዎ፡፡ በቀላሉ በነገሮች መረበሽን/ መወሰድን መቀነስ፣ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን ያለማከናወን፡፡ ሊረሱት የማይፈልጉትን ነገር ከሌላ ከሚወዱት ነገሮች ጋር አዛምዶ መያዝ፡፡


በደንብ መተኛት፡-

አንቅልፍ መተኛት ነገሮችን በደንብ ለማስታወስ እንዲችሉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም መልካምና በቂ እንቅልፍ እንዲኖርዎ ያድርጉ


ጤናማ አመጋገብ እንዲኖርዎ ማድረግ፡-

ጤናማ አመጋገብ መኖር ለአዕምሮ መልካም ነገር ነዉ፡፡ ስለሆነም ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ማዘዉተር፡፡ ምርጫዎ ብዙ ስብነት የሌላቸዉ የፕሮቲን ምንጭ የሆኑ እንደ አሳ፣ ቀይ ስጋ እና ዶሮ ይሁን፡፡ የሚጠጡትም ነገሮች ወሳኞች ናቸዉ፡፡ በቂ ዉሃ ካላገኙ ወይም አልኮሆል በብዛት ከወሰዱ ለግራ መጋባትና ለመርሳት/የማስታወስ ችሎታ መቀነስ መከሰት ይዳረጋሉ፡፡ ስለሆነም በቂ ዉሃ መዉሰድና አልኮልን መቀነስ የመስታወስ ችሎታዎን ለመጨመር ይረዳዎታል፡፡


በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከል፡-

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የደም ዝዉዉር አዕምሮዎን ጨምሮ ወደሌሎች የሰዉነት ክፍሎች እንዲሰራጭ ያደርጋል፡፡ ይህ የማስታወስ ችሎታዎ እንዲዳብር ያደርጋል፡፡ ሙሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ካልቻሉ እንኳ ቢያንስ ለ10 ደቂቃዎች ወክ ማድረግ መልመድ ያስፈልጋል፡፡


ለረጅም ጊዜ የቆዩ ችግሮች ካለዎ መፍትሄ እንዲኖረዉ ማድረግ፡-

ለረጅም ጊዜ የቆዩ እንደ ድብርት፣ የኩላሊትም ይሁን የታይሮይድ ዕጢ ችግሮች ካለዎ የህክምና ባለሙያዎ ዘንድ ክትትል በማድረግ ህክምና ማግኘት፡፡ በተሻለ ሁኔታ ለራስዎ እንክብካቤ ማድረግ የማስታወስ ችሎታዎ እንዲሻሻል ያግዝዎታል፡፡ በተጨማሪም የሚወስዱዋቸዉ መድሃኒቶች የማስታወስ ችሎታዎን ሊቀንሱ ስለሚችሉ መደበኛ በሆነ መንገድ የሚወስዱዋቸዉን መድሃኒቶች ከህክምና ባለሙዎ ጋ በመነጋገር ክትትል ማድረግ፡፡


የህክምና ባለሙያ ማየት የሚጠበቅብዎ መቼ ነዉ?


የማስታወስ ችሎታዎን በሚመለከት ስጋት ካለዎ፡- በተለይ የማስታወስ ችሎታዎ መቀነስ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ላይ ጫና ከፈጠረ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ የህክምና ባለሙያዎ አስፈላጊዉን የአካልና የማስታስ ችሎታ መርመራ ካደረገልዎ በኃላ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጨማሪ ምርመራዎችን ያደርግልዎታል፡፡
ለማስታወስ ችሎታ መቀነስ የሚደረጉ ህክምናዎች ይህንን ችግር እንዳመጣብዎ ሁኔታ ይለያያሉ፡፡

Recent Posts

 

የጨቅላ ህፃን ቢጫ መሆን የሚታየዉ በህፃኑ ሰዉነትና አይን ላይ ነዉ፡፡ የጨቅላ ህፃን ቢጫ መሆን የሚከሰተዉ የህፃኑ ከመጠን ያለፈና ቢጫ መልክ ያለዉ ቢሊሩቢን የሚባለዉ ኬሚካል በህፃኑ ደም ዉስጥ መኖር ነዉ፡፡

የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በብዛት የሚታይ/የሚከሰት ሲሆን በተለይ ከ38 ሳመንታት የእርግዝና ጊዜያቸዉ በፊት የሚወለዱ/ያለጊዜያቸዉ የሚወለዱና አንዳንድ ጡት የሚጠቡ ህፃናት ላይ በብዛት ይታያል፡፡ የጨቅላ ህፀናት ቢጫ መሆን የሚመጣዉ ህፃናት ጉበታቸዉ በደንብ ያልጎለበተ ከመሆኑ የተነሳ ቢሊሩቢን የሚባለዉን ኬሚካል ከደም ዉስጥ እንዲወገድ ማድረግ ስለማይችል ነዉ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ መሰረታዊ የጤና ችግሮችም ካሉ ሊከሰት ይችላል፡፡


ምልክቶች


ህፃናት በተወለዱ ከ2 እስከ 4 ቀናት ዉስጥ የቆዳና የአይን ነጩ ክፍል ቢጫ መሆን ይጀምራል፡፡ የልጅዎ ቆዳ መልክ ወደ ቢጫነት መቀየሩን ለማወቅ የልጅዎን የግንባር/ አፍንጫ ቆዳ ጫን ጫን በማድረግ በተጫኑበት ቦታ የቆዳዉ ቀለም ወደ ቢጫነት መቀየር መኖሩን ማረጋገጥ ነዉ፡፡


የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ


ልጅዎ ከተወለደ ከ 3 እስከ 7 ቀናት ዉስጥ የቢሊሩቢን መጠኑ በደም ዉስጥ ከፍ የሚልበት ወቅት ስለሆነ በህክምና ባለሙያዎች መታየት አለበት፡፡ የሚከተሉት የህመም ምልክቶች በብሊሩቢኑ በጣም መጨመር ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ይገባል፡፡
• የልጅዎ ቆዳ በጣም ቢጫ መሆን ካለዉ
• በልጅዎ የእግር፣እጅና ሆድ አካባቢ ባለዉ ቆዳ ላይ ቢጫ መሆኑ ካለ
• የልጅዎ የአይኑ ነጩ ክፍል ቢጫ ከሆነ
• ልጅዎ ከታመመ/ንቁ ካልሆነ
• ልጅዎ አመጋገቡ ከቀነሰ አሊያም ክብደት እየጨመረ ካልሆነ
• ልጅዎ ሲያለቅስ ድምፁ በጣም ከቀጠነ/ከሰለለ(ከተለወጠ) –high-pitched cries
• ቢጫ መሆኑ ከ3 ሳምንታት በላይ ከቆየ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡


ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች


• ያለጊዜያቸዉ የሚወለዱ ህፃናት፡- ያለጊዜያቸዉ/ከ38 ሳምንታት የእርግዝና ጊዜ በታች የሚወለዱ ህፃናት የመዉለጃ ጊዜያቸዉ ደርሶ ከሚወለዱት ህፃናት አንፃር ሲታዩ ቢሊሩቢንን የማስወገድ አቅማቸዉ የቀነሰ ነዉ፡፡
• ህፃኑ በሚወለድበት ሰዓት ከወሊድ ጋር በተገናኘ የቆዳ ስር ደም መድባት/ bruising ከነበረዉ፡- በወሊድ ወቅት ህፃኑ የመጋጋጥ/የቆዳ ስር መጥቆር አጋጥሞት ከነበረ ብዙ ቀይ የደም ሴሎች ስለሚሞቱና የቢሊሩቢን ኬሚካል መጠን ስለሚጨምር ለቢጫነት ያጋልጣል፡፡
• የደም አይነት፡- የእናትና የህፃኑ የደም አይነት የተለያየ ከሆነ
• የጡት ወተት፡- የእናት ጡት የመጥባት ችግር ያለባቸዉ ወይም ከእናት ጡት ወተት በቂ ንጥረ ምግብ ማግኘት የሚያዳግታቸዉ ህፃናት ይበልጥ ይጋለጣሉ፡፡ በቂ ወተት ሳያገኙ ቀርተዉ የፈሳሽ እጥረት የገጠማቸዉ ወይም የካሎሪ አወሳሰዳቸዉ አነስተኛ ከሆነ ለቢጫነቱ መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ኤክስፐርቶች የእናት ጡት ካለዉ ከፍተኛ ጥቅም የተነሳ የእናት ጡት ማጥበት መቀጠሉን ይመክራሉ፡፡ ህፃናት በበቂ ሁኔታ መመገብና/ጡት ወተት ማግኘት አለባቸዉ፡፡


የቤት ዉስጥ ህክምና


የልጅዎ ቢጫ መሆን ብዙም የማያሳስብ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎ ቢሊሩቢኑን መጠን ሊቀንስ የሚችል የአመጋገብ ልማድ ሊመክርዎ ይችላል፡፡ የሚከተሉትን ምክሮች ቢተገብሩ ሊረዳዎ ይችላል
• ልጅዎን በበቂ መጠን መመገብ፡- በተደጋጋሚና በበቂ መጠን መመገብ ልጅዎ በቂ ወተት እንዲያገኝ ስለሚረዳ ካካ/ሰገራ በተደጋጋሚ እንዲወጣና ከሰዉነታቸዉ ቢሊሩብንን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ጡት የሚጠቡ ህፃናት በቀን ዉስጥ ከ8 እስከ 12 ጊዜ መመገብ አለባቸዉ፡፡ የቆርቆሮ ወተት የሚመገቡ ከሆነ እድሜያቸዉ ላይ ደግሞ በየ 2ና 3ት ሰዓታት ከ30 እስከ 60 ሚሊ ሊትር ወተት በመጀመሪያ ሳምንት ማግኘት አለባቸዉ፡፡
• ተጨማሪ ምግብ፡- ልጅዎ ጡት የመጥባት ችግር ከገጠመዉ አሊያም ክብደት እየቀነሰና አሳሽ እያጠረዉ ከመጣ የህክምና ባለሙያዎ ከጡት ወተቱ በተጨማሪ የቆርቆሮ ወተት ሊያዝለት ይችላል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የህክምና ባለሙያዎ ጡት ለተወሰነ ቀናት አንዲያረጥና የቆርቆሮ ወተት እንድቀጥል ሊደረግ ይችላል፡፡


መከላከል


ህፃናትን በበቂ መጠን መመገብ የጨቅላ ህፃናትን ቢጫነት ለመከላከል ያገለግላል፡፡ ስለሆነም ከላይ እንደተጠቀሰዉ ጡት የሚጠቡ ህፃናት በቀን ዉስጥ ከ8 እስከ 12 ጊዜ መመገብ ያለባቸዉ ሲሆን የቆርቆሮ ወተት የሚመገቡ ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያዉ ሳምንት እድሜያቸዉ ላይ በየ 2ና 3ት ሰዓታት ከ30 እስከ 60 ሚሊ ሊትር ወተት ማግኘት አለባቸዉ፡፡

 

የአመት በዓል ሲመጣ ከሚወዷቸዉ ጋር ለማሳለፍ፣ ለመደሰትና ምስጋናን ለማቅረብ ጥሩ አጋጣሚ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ በተጨማሪም አመት በዓል የጤና ስጦታን የምናስብበት ስለሆነ ለእርስዎም ይሁን ለሌሎች በበዓል ወቅት ለጤናና ደህንነት ጥንቃቄ ለመደገፍና ለማድረግ የሚከተሉትን ምክሮች እነሆ:-

እጅዎን ሁሌ መታጠብ

ከህመም ለመጠበቅና የጀርሞችን ስርጭት ወደሌሎች እንዳይዛመት ለመከላከል ከሚወሰዱ እርምጃዎች አንዱና ዋነኛዉ የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ መቻል ነዉ፡፡እጅዎን በንፁህ ዉሃና ሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

 

ምግብን ሲያሰጋጁም ይሁን ሲያቀርቡ በጥንቃቄ ያድርጉ

ለዓመት በዓል ምግብ ሲያዘጋጁ እርስዎንም ይሁን ቤተሰብዎን ምግብ ወለድ ከሆኑ ህመሞች መጠበቅ ይገባዎታል፡፡
• ከአንድ ምግብ ወደሌላ ምግብ ብክለትን ለመከላከል የተዘጋጁና ለመመገብ ዝግጁ የሆኑትን ምግቦች ካልተዘጋጁት ምግቦች( ከጥሬ ስጋ፣እነቁላልና ከመሳሰሉት) እንዲሁም የመመገቢያ ቦታ መለየት የስፈልጋል፡፡
• ምግቦችን ሲያዘጋጁ በአግባቡ መብሰላቸዉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
• የበሰሉትንም ይሁን ሌሎችንም ቢሆን አግባብ ባለዉ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት ማስቀመጥ፤በተጨማሪም በቀላሉ ሊበላሹ የሚችሉ ምግቦችን ከሁለት ሰዓታት በላይ ከፍሪጅ ዉጪ ያለማስቀመጥ፡፡

 

ጤናማ አመጋገብ እንዲኖሮትና ንቁ እንዲሆኑ ለማድረግ

የተመጣጠነና ጤንነቱን የጠበቀ ምግብ በመመገብ አመት በዓሉን በደስታና በጤናማ መንገድ ያሳልፉ፡፡
• ስብነት ያላቸዉን/የበዛባቸዉን፣ጣፋጭና ጨዉ የበዛባቸዉን ምግቦች መወሰን/መቀነስ
• አትክልትና ፍራፍሬ፡- ጣፋጭ ምግቦችን ትኩስ በሆኑ አትክልትና ፍራፍሬ መተካት
• ንቁና ደስተኛ ሊያደርጎት የሚችሉትን ነገሮች መተግበር፡- ለምሳሌ በሚወዱት የአመት በዓል ሙዚቃ መደነስ/መጨፈር
• የአልኮሆል መጠጦችን ከመጠን በላይ ያለመዉሰድ
• ሲጋራ ያለማጨስ/ሌሎች ሲያጨሱም ቢሆን ጭሱን ያለመማግ፡፡የሚያጨሱም ቢሆን ዛሬዉኑ ማጨስ ለማቆም መወሰን፡፡

 

አደጋን መከላከል( Prevent injuries)

አደጋዎች በየትኛዉም ቦታና ሰዓት የሚከሰቱ ቢሆንም አንዳንዶቹ ብዙዉን ጊዜ በአመት በዓል ወቅት ይበዛሉ፡፡በተቻለዎት መጠን
• የተጠቀሙበትን የኤልክትሪክም ይሁን ሌሎች የማብሰያ ምድጃዎች መዘጋታቸዉን ማረጋገጥ
• ለበዓል ተብለዉ የሚበሩ ሻማዎችን ከልጆች፣ከቤት ውስጥ እንስሳት( pets)ና ከመሳሰሉት ማራቅ ይገባል
• ከሰልን ከተጠቀሙ በኃላ ጭስ የሌለዉ ወይም የጠፋ መሆኑን ማረጋገጥ

መልካም በዓል ይሁንልዎ

Recent Posts

 

የኩላሊት ጠጠር በኩላሊትዎ ዉስጥ ትናንሽና ጠንካራ የሆኑ ማዕድናት ሲጠራቀሙ የሚመጣ ችግር ነዉ፡፡ ድንጋዮቹ የተሰሩት ከማዕድናትና አሲድነት ካላዉ ጨዉ ነዉ፡፡ የኩላሊት ጠጠር መነሻ መንስኤ ብዙ ሲሆኑ በየትኛዉም የሽንት መተላለፊያ መስመር ዉስጥ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ብዙዉን ጊዜ የኩላሊት ጠጠሮች የሚከሰቱት ሽንት በሚወፍርበት/ concentrated/ በሚሆንበት ወቅት ሲሆን ይህ ማዕድናቱ እንዲረጉና እንዲጣበቁ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡

የህመሙ ምልክቶች

በአብዛኛዉን ጊዜ የኩላሊት ጠጠሮች በኩላሊትዎ ዉስጥ ካልተዘዋወሩ አሊያም ወደ ዩሬተር(ሽንትን ከኩላሊትዎ ወደ ፊኛ የሚወስደዉ ቱቦ) ካልወረዱ በስተቀር ምንም አይነት የህመም ምልክት አያሳዩም፡፡ ስለሆነም የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡
• ጎንና ጀርባዎ ላይ ከፍተኛ ህመም መኖር
• ወደ ታችኛዉ የሆድዎ ክፍልና ብሽሽት የሚሰራጭ ህመም መፈጠር
• ሽንት ሲሸኑ ህመም መኖር
• ቀይ ወይም ቡናማ የመሰለ የሽንት መልክ መከሰት
• ጉም የመሰለ ወይም ሽታ ያለዉ ሽንት መዉጣት
• ማቅለሽለሽና ማስታወክ
• በተደጋጋሚ ለመሽናት መፈለግ
• ከተለመደዉ ጊዜ/ብዛት በላይ ሽንት መሽናት
• ኢንፌክሽን ካለ ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት መኖርና
• በጣም ትንሽ መጠን ያለዉ ሽንት መሽናት ናቸዉ፡፡
በኩላሊት ጠጠር ምክንያት የሚከሰተዉ ህመም ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ጠጠሩ ወደ ሌላ ቦታ ከሄደ/ ከተዘዋወረ ህመሙ ሊጨምር የችላል፡፡


የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?


የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ባስቸኳይ ያማክሩ፡፡
• ህመሙ በጣም ከፍተኛ ከሆነና መቀመጥ ያለመቻል ወይም ምቾት የሚሳንዎ ከሆነ
• ህመሙን ተከትሎ ማቅለሽለሽና ትዉከት ከመጣ
• ከህመሙ ጋር ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት ካለ
• ከሽንትዎ ጋር ደም ከመጣ
• ሽንትዎን መሽናት ከተቸገሩ


ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች


• በዚህ በፊት በቤተሰብዎ ወይም በራስዎ ላይ መሰል ችግር ከነበረ
• የፈሳሽ እጥረት/ ድርቀት ካለ፡- በየቀኑ ፈሰሽ በበቂ መጠን መዉሰድ ካልቻሉ ለኩላሊት ጠጠር ይጋለጣሉ፡፡ ከሌሎቹ ይልቅ በሞቃታማ የአየር ንብረት ዉስጥ የሚኖሩና ከመጠን ያለፈ ላብ የሚያልባቸዉ ሰዎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸዉ፡፡
• የተወሰኑ የምግብ አይነቶች፡- የፕሮቲን፣ የሶዲየምና የስኳር ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን የሚያዘወትሩ ሰዎች ለተወሰኑ የኩላሊት ጠጠር አይነቶች ይጋለጣሉ፡፡
• ዉፍረት፡- ከመጠን ያለፈ ክብደት ያላቸዉ ሰዎች ላይ የኩላሊት ጠጠር የመፈጠሩ ጉዳይ ከፍተኛ ነዉ፡፡


የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር መከላከል


የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ለመከላከል የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና መድሃኒቶች ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታሉ፡፡
• በየቀኑ በቂ ፈሳሽ/ዉሃ መጠጣት፡- ሞቃታማና ደረቅ የአየር ንብረት ዉስጥ የሚኖሩ ከሆነ ወይም በመደበኛ ሁኔታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ ሽንት በበቂ መጠን እንዲመረት/እንዲወጣ ፈሳሽ በበቂ መጠን መጠጣት ይመከራል፡፡ ሽንትዎ ነጣ ያለና ንፁህ ከሆነ ዉሃ በበቂ መጠን እየወሰዱ መሆኑን ያሳያል፡፡
• መጠነኛ የኦክዛሌት/ oxalate ይዘት ያላቸዉን የምግብ አይነቶች ማዘዉተር፡- የካልሲየም ኦግዛሌት ድንጋይ እየተፈጠረ ካለ ወይም ተጋላጭነት ካለዎ እንደ ስኳር ድንች፣ ቆስጣ፣ ኦቾሎኒ፣ ሻይ፣ ቼኮሌት፣ የአኩሪ አተር ተዋፅኦዎችና ቀይስር ያሉ ምግቦች መመገብ ያስፈልጋል፡፡
• የጨዉና የፕሮቲን ይዘታቸዉ አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን መምረጥ/ማዘዉተር፡- የሚመገቡትን የጨዉ መጠን መመጠን እንዲሁም ከእንስሳት ተዋፅኦ ዉጪ ያሉ የፕሮቲን ምንጮችን መመገብ ( ለምሳሌ ባቄላና አተር)
• የካልሲየም ይዘታቸዉ ከፍ ያለ ወይም በካልሲያም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ነገር ግን የካልሲየም ሰፕሊመንት(ተጨማሪ እንክብል) ሲወስዱ ጥንቃቄ ያድርጉ፡- በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ የኩላሊት ጠጠር የመፈጠር እድሉን አይጨምሩትም፡፡ የህክምና ባለሙያዎ ካልከለከለዎ በስተቀር የካልሲየም ይዘታቸዉ ከፍ ያሉ ምግቦችን መመገብ ይቀጥሉ፡፡ ነገር ግን የካልሲየም ሰፕልመንቶች ከኩላሊት ጠጠር መከሰት ጋር ተያያዥት/ግንኙነት ስላላቸዉ ከመዉሰድዎ በፊት የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

Recent Posts

 

አንድ ሰዉ በቀን የሚያስፈልገዉ የፈሳሽ መጠን ይህ ነው ብሎ እቅጩን ለመናገር እስከአሁን ስምምነት ላይ ያልተደረሰ ቢሆንም የሚስፈልገዉ የፈሳሽ መጠን በተለያዩ ነገሮች ይወሰናል፡፡ እነዚህም የግለሰቡ ጤንነት፣ የእንቅስቃሴ መጠን፣ እድሜ፣ የአየር ፀባይ(የሚኖርበት ስፍራ)፣ ምን ያህል ዉሃ በቡና፣ በሻይ፣ በጅዉስና በመሳሰሉት መልክ እንደሚወስድና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ እንደሚያዉቁት በየቀኑ ዉሃ ከሰዉነትዎ በትንፋሽ፣ በላቦት፣ በሽንትና በሰገራ ዉስጥ ይወጣል፡፡ ሰዉነትዎ በአግባቡ እንዲሰራ ከሰዉነትዎ የወጣዉን ፈሳሽ መልሰዉ ለመተካት ዉሀን ጨምሮ ዉሀን የያዙ ፈሳሾችን መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም አንድ ጤነኛ ሰዉ በቀን መዉሰድ የሚገባዉ የዉሀ መጠን ለወንዶች እስከ 3 ሊትር ሲሆን ለሴቶች እስከ 2.2 ሊትር መዉሰድ ይመከራል፡፡

 

ዉሃን በብዛት መጠጣት ለምን ያስፈልጋል?


1.የሰዉነትን የፈሳሽ መጠን ለማመጣጠን፡-

60 ከመቶ የሚሆነዉን ሰዉነታችንን ክፍል የተያዘዉ በዉሃ ነዉ፡፡ የሰዉነት ፈሳሽ ለምግብ መፈጨት፣ለምግብ መመጠጥና ወደተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች መዳረስ፣ ምራቅን ለመስራት፣ንጥረነገሮችን ለሰዉነታችን ለማዳረስ/ለማሰራጨትና የሰዉነትን ሙቀት ለመቆጣጠር ያገለግላል/ይጠቅማል፡፡
አልኮሆል የአእምሮንና የኩላሊትን ግንኙነት ስለሚያዉክና ብዙ ፈሳሽ ከሰዉነታችን እንዲወጣ ስለሚያደርግ ለድርቀት ያጋልጠናል፡፡ ስለሆነም አልኮል ከምንወስደዉ ፈሰሽ ዉስጥ አይመደብም፡፡

 

2. የሰውነት ክብደት መጠንን ለመቀነስ መርዳት፡-

ከፍ ያለ የካሎሪ መጠን ካላቸዉ እንደ ኮካ ያሉ ፈሳሾች ይልቅ ንፁህ ዉሃ መዉሰድ የሰዉነትን ክብደት ለመቆጣጠር/ለመቀነስ ያግዛሉ፡፡ በተጨማሪም ብዙ ፈሳሽነት ያላቸዉ ምግቦች ከፍ ያለ መጠን (volume) ስላላቸዉ፣ በቀላሉ የጥጋብ ስሜት እንዲመጣና ቀስ ብለዉ ስለሚመጠጡ ለክብደት ቁጥጥር ያገለግላሉ፡፡ ብዙ ፈሳሽነት ካላቸዉ ምግቦች ዉስጥ አትክልት፣ ፍራፍሬና ሾርባ ይጠቀሳሉ፡፡


3. ተጨማሪ ሀይልና ጉልበት ለጡንቻዎቻችን ለመስጠት ፡-

የፈሳሽንና ንጥረነገሮችን (ኤሌክትሮላይት) ምጣኔን የማይጠብቁ/ የማይቆጣጠሩ የሰዉነታችን ሴሎች ይሟሽሻሉ፤ ይህ ለጡንቻ መዛል(fatigue) ሊያጋልጠን ይችላል፡፡ የሰዉነታችን ጡንቻ ሴሎች በቂ ፈሳሽ ካላገኙ/ከሌላቸዉ በትክክል አይሰሩም፤ይህ በመሆኑም እንቅስቃሴዎችን መተግበር ያዳግተናል፡፡
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከማድረግዎ በፊት፣ በሚያደርጉበት ወቅትና ካደረጉ በኃላ በላብ መልክ የሚወጣዉን ፈሳሽ ለመተካት በቂ ፈሳሽ መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡


4. ዉሃ የሰዉነት ቆዳዎ ጥሩ እንዲሆን/እንዲጠራ/እንዲለሰልስ ያግዛል፡-

የሰዉነታችን ቆዳ ብዙ ዉሃ ያለዉ ሲሆን ከሰዉነታችን ዉስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ እንዳይወጣ ለመከላከል ያገለግላል፡፡ በቂ ፈሳሽ ካልወሰድን ቆዳችን እንዲደርቅና እንዲሸበሸብ የሚያደርግ ሲሆን ይህን ለመከላከል በቂ ፈሳሽ መዉሰድ ይገባናል፡፡ በተጨማሪም ሞይስቸራይዘሮች እርትበት/ፈሳሽ በቆዳችን በኩል እንዳይወጣና ታምቆ እንዲቀር ስለሚያደርጉ የሰዉነት ቆዳ ልስላሴዉን እንዲጠብቅ ይረዱታል፡፡


5. ዉሃ ለኩላሊት የፍሳሽ ማጣራት እና ማስወገድ አቅምን ይጨምራ፡-

የሰዉነት ፈሳሾች ቆሻሻን ወደ ሰዉነት ሴሎች ዉስጥና ዉጪ ለማጓጓዝ ያገለግላሉ፡፡ ለሰዉነታችን ሴሎች መርዛማ ከሆኑት ዉስጥ እንደ ዩሪያ ያሉ ኬሚካሎችን ከሰዉነት በኩላሊት በኩል ለማስወገድ የሚቻለዉ በየቀኑ በቂ ፈሳሽ መዉሰድ ሰንችል ነዉ፡፡ በቂ ፈሳሽ ከወሰድን ሽንታችን በደንብ ይወጣል፣ ነጣ ያለ መልክ እንዲኖረዉና ሽታ እንዳይኖረዉ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ሰዉነታችን በቂ ፈሳሽ ካላገኘ የሽንት መጠን እንዲቀንስና እንዲወፍር ያደርጋል፣መልኩ እንዲለወጥና ሽታ እንዲኖረዉ ያደርጋል:: ምክንያቱም ኩላሊት ብዙ ፈሳሽ እንዳይወጣ ስለምትከለክል፡፡


6. ዉሃ የአንጀት ስርዓት በትክክል እንዲሰራ ያደርጋል፡-

በቂ ፈሳሽ መዉሰድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ በቂ ፈሳሽ የማይወስዱ ከሆነ ትልቁ እንጀት ፈሳሽ ወደ ሰዉነታችን መጦ በመመለስ የሰዉነታችንን የፈሳሽ ምጣኔ የሚጠብቅ ሲሆን የኸን በሚያደርግበት ወቅት ድርቀት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ በቂ ፈሳሽ መዉሰድና ቃጫነት(ፋይበርናት) ያለዉ ምግብ መመገብ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡


በተጨማሪም ዉሃ


• ለመነቃቃት እና የምንሰራው ስራ ላይ የበለጠ ትኩረት ለማድረግ ይረዳል፡፡
• ከልክ ያለፈ መጠጥ በተጠጣበት ግዜ የሃንግኦቨር ስሜትን ይቀንሳል፡፡
• በጡንቻ እና በመገጣጠሚያ ላይ የሚከሰቱ ህመሞችን ይከላከላል፡፡
• የሠውነት የሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር ይጠቅማል እንዲሁም
• መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላል፡፡

Recent Posts

 

ኦቲዝም በህፃናት ላይ የነርቭና የእድገት ክትትል ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ሲሆን የልጁን ከሰዉ ጋር የሚያደርገዉን ግንኙነትና የመግባባት ችሎታ/ክህሎት  የሚጎዳ/የሚቀንስ የህመም አይነት ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

ኦቲዝም  የልጆን ከሌሎች ጋር መግባባትንና የአረዳድ ሁኔታን በመጉዳት ለእድገት አስፈላጊ የሆኑ እንደ ማህበራዊ ግንኙነቶች፣መግባባትና ባህሪያቶችን ሊጎዳ ይችላል፡፡

የኦቲዝም ምልክቶችን አንዳንዴ በጨቅላ ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፡፡ሎሎች ህፃናት ደግሞ የመጀመሪያ ወራት ወይም አመታት ላይ ያለምንም ችግር ያድጉና ድንገት መነጠል ወይም ሃይለኛ መሆን አሊያም በቅርቡ ደርሰዉበት የነበረዉን የsንs ክኅሎት እድገት በድንገት መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ለችግሩ መከሰት የሚያጋልጡ ነገሮች

·         የልጅዎ ፆታ፡- ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እስከ አራት ጊዜ እጥፍ ተጋላጭ ናቸዉ፡፡

·         በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ከነበረ፡- በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ያለበት ልጅ ያላቸዉ ቤተሰቦች ቀጣይ የሚወልዷቸዉ ልጆች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡

·         ያለቀናቸዉ በሚወለዱ ህፃናት ላይ፡- የመዉለጃ ጊዜያቸዉ ሳይደርስ ከ26 ሳምንታትና ከዚያ በታች የሚወለዱ ህፃናት ላይ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡

·         የወላጆች እድሜ፡- ተጨማሪ ጥናቶች የሚያስፈልግ ቢሆንም እድሜቸዉ ከገፉ ወላጆች የሚወለዱ ህፃናት ከሌሎች አንፃር ችግሩ ሊከሰትባቸዉ ይችላል፡፡

ህክምና

ኦቲዝምን ሊያድን የሚችል ምንም አይነት ህክምና እስከአሁን የለም፡፡ ስለሆነም የህክምናዉ ዋና አላማ ልጅዎ ላይ የሚታዩትን የህመም ምልክቶች በመቀነስ የልጅዎን እድገትና የትምህርት ሁኔታ ማሻሻል ነዉ፡፡የህክምና ባለሙያዎ በአካባቢዎ የሚገኙና ልጅዎን ሊረዱ/ሊያግዙ የሚችሉ አካላቶችን በማፈላለግ ሊያግዝዎ ይችላል፡፡ ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ፡-

  • የመግባባት ክህሎትና የባህሪ ለዉጥ ህክምናዎች፡-

    የልጁን ማህበራዊ፣ ቐንቐና የባህሪ ችግሮች ላይ የሚሰሩ ብዙ ፕሮግራሞች/መርሃግብሮች አሉ፡፡ የተወሰኑት ፕሮግራሞች የልጁን የሚያስቸግሩ ባህሪያቶችን ለመቀነስና አዳዲስ ችሎታዎችን ማስተማር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ህፃናቱ በማህበራዊ ግንኙነታቸዉ ላይ እንዴት መሆን/ምን መተግበር   እንዳለባቸዉ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ትኩረት ያደርጋል፡፡

  • ትምህርት፡-

    ኦቲዝም ያለባቸዉ ህፃናት በደንብ ለተቀረፃ የትምህርት መርሃግብር ጥሩ የሆነ አቀባበል አላቸዉ፡፡የተዋጣላቸዉ ፕሮግራሞች በዉስጣቸዉ ብዙ መርሃግብሮችን የሚይዙ ሲሆን ይህም የልጁን ማህበረዊ፣የመግባባት ክህሎትና ባህሪዉ ላይ ያተኮሩ ይሆናሉ፡፡

  • ቤተሰብ ተኮር ህክምና፡-

    ወላጆችና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የልጁን የመግባባት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ለማዳበር እንዲሁምበየቀኑ የሚጠቀምበትን የመግባባት ክህሎቱን ለማሳደግ በሚረዳዉ መልክ  እንዴት አብረዉ መጫወትና መግባባት እንደሚችሉ ማስተማር ያፈልጋል፡፡

  • መድሃኒት፡-

    ዋናዎቹን የህመም ምልክቶች የሚያሻሽል መድሃኒት እስከአሁን ባይገኝም ምልክቶቹን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተወሰኑ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ አንታይዲፕሬሳንትና አንታይሳይኮቲክ

Recent Posts

 

ለደም ግፊት ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡

• እድሜ፡-  እድሜዎ ሲጨምር የደም ግፊት እየጨመረ ይመጣል፡፡
• በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር፡- የደም ጊፊት ከቤተሰብ ሊወረስ ይችላል፡፡
• ከመጠን ያለፈ ዉፍረት ወይም ክብደት ካለዎ፡- ክብደትዎ በጨመረ ቁጥር ሰዉነትዎ ተጨማሪ ኦክሲጅንና ንጥረ ነገር ይፈልጋል፡፡ ይህ የደም መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርግ የግፊት መጠንም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• መደበኛ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ከሆነ፡- መደበኛ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎች ክብደታቸዉ ስለሚጨምር ለደም ጊፊት የመጋለጥ እድላቸዉ ይጨምራል፡፡
• ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ የደም ግፊትን ከመጨመሩ ባሻገር በሲጋራ ዉስጥ ያለዉ ኬሚካል የደም ስሮች ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ይህ የደም ስሮች እንዲጠቡ ስለሚያደርግ የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• ከምግብዎ ጋር ጨዉ በብዛት መጠቀም፡- በሚመገቡት ምግብ ዉስጥ ጨዉ በብዛት መጠቀም ፈሳሽ ሰዉነትዎ ዉስጥ በብዛት እንዲኖር ስለሚያደርግ የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• የፖታሲየም ይዘታቸዉ አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር፡- ፖታሲየም የሶዲየምን መጠን ለማመጣጠን ስለሚረዳ እነደ ሙዝ ያሉ ከፍ ያለ የፖታሲየም ይዘት ያላቸዉ ምግቦችን እንዲያዘወትሩ ይመከራሉ፡፡
• አልኮሆል በብዛት መጠጣት፡- አልኮሆል ልብንና የደም ስሮችን ይጎዳል፡፡ ወንዶች በየቀኑ ከሁለት ጠርሙስ ቢራ በላይና ሴቶች በየቀኑ ከአንድ ቢራ በላይ የሚጠጡ ከሆነ በደም ግፊትዎ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል፡፡ አልኮሆል የሚጠጡ ከሆነ መመጠን አለብዎ፡፡
• ጭንቀት፡- ከፍተኛ ጭንቀት የደም ግፊትን ሊጨምር ይችላል፡፡
• በምግብዎ ዉስጥ የቫይታሚን ዲ መጠን አነስተኛ መሆን፡- ምንም እንኳን የቫታሚን ዲ እጥረት የደም ግፊትን እንደሚጨምር/እንደማይጨምር ባይታወቅም የቫይታሚን ዲ እጥረት ከኩላሊት የሚመጣዉን ኢንዛየም ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለደም ግፊት ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
• የዉስጥ ደዌ ችግሮች፡- የኩላሊት፣ የስኳርና ሌሎች ችግሮች ለደም ግፊት ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡


ምንም እንኳ ደም ግፊት በአዋቂዎች ላይ በብዛት የሚከሰት ቢሆንም በህፃናት ላይም ሊከሰት ይችላል፡፡ ህፃናት ላይ የኩላሊትና የልብ ችግሮች ለደም ግፊት የሚዳርጉ ሲሆን ጥሩ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ዉስጥ የሚመደቡ ጤንነቱን ያልጠበቀ አመጋገብ፣ ዉፍረት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለመኖር ለደም ግፊት መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

Recent Posts

41254786_m

ከዚህ በፊት የህፃን ልጅዎን የአጨዋወት፣ አነጋገር/ቋንቋ፣ እንዴት እንደሚማር እና እንቅስቃሴዎችን እንዴት እንደሚተገብር በመከታተል ስለልጅዎ የእድገት ሁኔታ ፍንጭ ማግኘት እንደሚቻልና የሶስት ዓመት ህፃን ሊያሳይ የሚችላዉን ነገሮች መነጋገራችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዘዚያ የቀጠለ የአራት አመት ልጅ የእድገት ክትትልን እናያለን፡፡

አብዛኞቹ ህፃናት በዚህ እድሜ ምን ምን ነገሮችን ይተገብራሉ?

ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional

  • አዳዲስ ነገሮችን በመስራት ይደሰታሉ
  • እናት አባት/ እንደ እናትና አባት በመሆን/ ጨዋታዎችን ይጫወታሉ
  • ብቻቸዉን ከመጫወት ይልቅ ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወትን ይመርጣሉ
  • ከሌሎች ልጆች ጋር ይግባባሉ/ይረዳዳሉ
  • ስለሚወዱትና ስለሚያስደስታቸዉ ነገሮች ማዉራት ይችላሉ

ቋንቋ /መግባባት (Language/Communication)

  • የተወሰኑ ትክክለኛ የቃላት አገባብን /ግራመር/ አጠቃቀም ያዉቃሉ
  • ግጥም ወይም ዘፈን አስታዉሰዉ ማለት ይችላሉ
  • ተረት መንገር ይችላሉ
  • ስማቸዉን እስከ አያታቸዉ መናገር ይችላሉ፡፡

አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና  ችግርን መፍታት መቻል)

·         የተወሰኑ የከለር አይነቶችንና ቁጥሮችን መለየት መቻል

  • መቁጠር ምን እንደሆነ መረዳት መቻል
  • ሰዓት/ጊዜን መረዳት መቻል
  • የተነገረዉን የታሪክ/ተረት ክፍል በተወሰነ መልኩ ማስታወስ መቻል
  • አንድ አይነትና የተለያዩ የሚባሉ ሃሳቦችን መለየት መቻል
  • አንድን ሰዉ ከሁለት እስከ አራት የሚደርሱ የሰዉነት አካላቶቹን በማካተት መሳል መቻል
  • የፊደላትን ትላልቁን /ካፒታል ሌተሮችን/ መፃፍ መቻል
  • በካርድ የተሰሩ መጫወቻዎችን በመጠቀም መጫወት መቻል፡፡

እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development

  • በአንድ እግሩ እስከ ሁለት ሰኮንድ መቆም መቻል
  • የምትነጥርን ኳስ መያዝ መቻል
  • ክትትል እየተደረገባቸዉ ዉሃ ማንቆርቆር መቻል፣ መቁረጥ መቻል

Recent Posts