Author: hellodoc

ከአልኮልነት ጋር ያልተያያዘ የጉበት ላይ ስብ ማለት በጣም ትንሽ ወይም ምንም አይነት አልኮሆል ሳይጠቀሙ/ሳይጠጡ በጉበት ላይ የስብ መጠራቀም ችግር በሚከሰትበት ወቅት ነዉ፡፡

 

የህመሙ ምልክቶች

ችግሩ ምንም የህመም ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ነገር ግን የህመም ምልክቶች ከታዩ የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡

  • የሰዉነት ድካም
  • በቀኝ የላይኛዉ የሆድ ክፍል ህመም መሰማት
  • የክብደት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

 

የህመሙ ምክንያቶች

የጉበት ላይ ስብ መጠራቀም የሚከሰተዉ ጉበት ስብን ለመሰባበር በሚየደርገዉ ሂደት ላይ ችግር ሲገጥመዉ ሲሆን ይህ ክስተት ስብ በጉበት ላይ እንዲጠራቀም ያደርገዋል፡፡

 

ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች

 

  • የሰዉነት የኮለስትሮል መጨመር
  • በደም ዉስጥ ያለዉ የትራይግላይስራድ ስብ መጠን መጨመር
  • ሜታቦሊክ ሲንድረም
  • ዉፍረት
  • ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም የሚባለዉ የጤና ችግር ሲኖር
  • ስሊፕ አፕኒያ( ከእንቅልፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ችግሮች)
  • የስኳር ህመም ሲኖር
  • የታይሮይድ ችግር ሲኖርና የመሳሰሉት ናቸዉ፡
ብጉር በሰዉነት ቆዳ ላይ የሚከሰት ችግር ሲሆን የላብ መዉጪያ ቀዳዳዎች( hair follicles) በስብ፣ በሞቱ የቆዳ ሴሎችና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በባክቴሪያዎች በሚደፈንበት ወቅት የሚመጣ ነዉ፡፡

ብጉር በብዛት የሚከሰተዉ በጣም ብዙ የሆኑ የስብ አመንጪ ዕጢዎች በብዛት የሚገኝባቸዉ የቆዳ ክፍሎች ባሉበት የሰዉነት ክፍሎች እንደ ፊት፣አንገት፣ደረት፣ጀርባና ትከሻ ያሉ ቦታዎች ላይ ነዉ፡፡ ብጉር ከሰዉነት ላይ ሳይጠፋ በሚቆይበትና ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ያለ ከሆነ እንደ እፍረትና መንፈስ ጭንቀትን የመሳሰሉ ስነልቦናዊ ጉዳቶችንና የቆዳ ጠባሳን ሊያመጣ ስለሚችል እነዚህ ነገሮች የተጎጂዉን ማህበረዊና የስራ ቦታ ጫናን ሊያመጣ ይችላል፡፡ብጉር ጥሩ የሆነ ህክምና ያለዉ ሲሆን በወቅቱ ከታከመ የሚያመጣዉን የአካልና መንፈስ ጉዳት መቀነስ ይቻላል፡፡

 

ለብጉር መከሰት ምክንያቶች ምንድናቸዉ

· የስብ ከመጠን በላይ መመረት

· የሞቱ የቆዳ ሴሎች በአግባቡ ያለመወገድ( Irregular shedding of dead skin cells)
· የባክቴሪያዎች መራባት(መጠራቀም)

 

ለብጉር ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች( Risk factors)


· ለሰዉነት ሆርሞን መለዋወጥ ምክንት የሆኑ ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት፡-ጉርምስና፣እርግዝና፣የሴቶች የወር አባበ ዑደት ከመከሰቱ ከ 2 እስከ 5 ቀናት በፊት ያሉ ቀናት፣የተወሰኑ መድሃኖቶችን የሚወስዱ ሰዎች(አንድሮጅን፣ሊትየምና እስቴሮይድ)

· በቆዳ ላይ የሚቀቡ ዘይትነት ወይም ግሪሲ የሆኑ ነገሮች( greasy or oily substances) ወይም የተወሰኑ የመዋቢያ ቅባቶች(ኮስሞቲክሶች)

· በቤተሰብ ዉስጥ የሚከሰት

· በቆዳ ላይ ፍትጊያና ግፊት የሚያሳድሩ ነገሮች፡-ሄልሜንት፣ስልክ፣ጥብቅ ያሉ አልባሳት

ብጉርን የሚያባብሱ ነገሮች(Agravating factors)

· ሆርሞኖች፡-ለምሳሌ በጉርምስና ወቅት አንድሮጂን፣እርግዝና፣ብጉር እያለ የተወሰኑ መድሃኒቶችን መዉሰድ፡-አንድሮጅን፣ሊትየምና እስቴሮይድ

· የተወሰኑ ምግቦች፡-የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን እንዲሁም ሃይልሰጪ በብዛት ያላቸዉ ምግቦችን መጠቀም (dairy products and carbohydrate-rich foods)

· ጭንቀት( Stress)


የብጉር ህክምና


የብጉር ህክምና የስብ መመረትን በመቀነስ፣የቆዳ ሴሎች ቶሎ ቶሎ እንዲቀያየሩ በማድረግ፣የባክቴሪያ ኢንፌክሽንን በመቀነስና የቆዳ መቆጣትን በመቀነስ የሚሰራ ሲሆን በህክምናዉ ጥሩ ዉጤት ሳያዩ ከ4 እስከ 8 ሳምንታት ሊቆዩ ስለሚችሉ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ መድሃኒቶቹን በአግባቡ እየወሰዱ ብጉሩ ሊባባስ ስለሚችል ህክምናዎትን ሳያsርጡ በትዕግስት መከታተል ያስገልጋል፡፡ለብጉር ህክምና የሚረዱ የተለያዩ መዱሃኒቶች ያሉ ሲሆን እነሱም በቆዳ ላይ የሚቀቡ፣የሚዋጡ አንቲባዮትክሶች እንዲሁም ሌዘርና ላይት ቴራፒ የሚባሉ ዘዴዎች ያሉ ሲሆን የትኛዉን መንገድ መጠቀም እንደሚሻል ለመወሰን የቆዳ እስፔሻሊስት ሀኪሞችን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

በብጉር ምክንያት የሚከሰተዉን የቆዳ ላይ ጠባሳም ቢሆን የራሱ የሆነ የተለያዩ ህክምናዎች ያሉት ስለሆነ ለዚህም የቆዳ እስፔሻሊስት ሀኪሞችን ማማከር ያስፈልጋል

 


ብጉርን እንዴት መከላከል ይቻላል


· ለብጉር ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መታጠብ፡-ይህ ከመጠን በላይ የሆነዉን የቆዳ ቅባትና የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ያስወግዳል፡፡ከመጠን ያለፈ መታጠብ ቆዳዎትን ስለሚቆጠቁጥና ለብኩር ስለሚያጋልጥዎ ይህን ከማድረግ ይቆጠቡ

· ከመጠን ያለፈ ፋዉንዴሽን ሜካፕ ያለመጠቀም፡- ከክሬምነት ይልቅ ፓዉደር ኮስሞቲክሶችን ይምረጡ፡፡ምክንቱም ፓዉደር ኮስሞቲክስ ከክሬም አንፃር ሲታዩ ቆዳን እምብዛም አይቆጠቁጡም

· ከመተኛትዎ በፊት ሜክአፕ ተቀብተዉ ከሆነ ማስወገድ/መታጠብ፡-በቆዳ ላይ ከነተቀባዉ ኮስሞትክሰዎ መተኛት የላብ መዉጪ ቀዳዳዎችን ስለሚደፍነዉ ለብጉር መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡የሜካፕ መቀቢያ ብሩሾችም በየጊዜዉ በዉሀና ሳሙና መታጠብ አለባቸዉ፡፡

· ለቀቅ ያሉ ልብሶችን መልበስ፡-ጥብቅ ያሉ ልብሶችን መልበስ ሙቀትንና እርጥበትን ስለሚይዝ ለሰዉነት መቆጣት ምክንያት ይሆናሉ፡፡ሄልሜንቶች፣የስፖርት አልባሳትም ቢሆኑ ከሰዉነት ጋር ያላቸዉን ፍትግያ ለመቀነስ ከተቻለ በጣም ጥብቅ ያሉ መሆን የለባቸዉም፡፡

· ከበድ ያለ ስራ ወይም የአካል እንቅስቃሴ ካደረጉ በኃላ ሰዉነትን መታጠብ፡-የሰዉነት ላብና ስብ ቆሻሻንና ባክቴሪያዎችን ስለሚስቡ ሻወር መዉሰድዎትን አይርሱ፡፡

· በሰዉነት ላይ ያለዉን ከመጠን ያለፈ ቅባት ለማድረቅ ያለሀኪም ትእዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ ወይም ሳሊሲሊክ አሲድን ያያዙ የብጉር ክሬም ወይም ጄል መጠቀም

 

የብልት ያለመቆም ችግር( Erectile dysfunction)

የብልት ያለመቆም ችግር አለ የምንለዉ የወንድ ብልት ለግብረ ስጋ ግንኙነት ሲዘጋጅ አልቆም ሲል ወይም የተወሰነ ቢቆምም ምንም ጥንካሬ የሌለዉ ከሆነ ነዉ፡፡ይህ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከቀጠለ በወንድየዉ ላይ ጭንቀትን፣በራስ ያለመተማመንንና የግብረስጋ ግንኙነት ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል፡፡

የወንዶች ብልት ያለመቆም ችግርን ለህክምና ባለሙያዎ ማወያየት የሚከብድ ቢመስልም ለብልት ያለመቆም ችግር መንስኤ የሆኑና ቢታከሙት ችግሩን ሊያቃልል የሚችሉ እንደ የልብና የስኳር ህመም ያሉ የውስጥ ደዌ ችገሮች ስላሉ ምንም ሳያፍሩ የህክምና ባለሙያዎን ማወያየት ይመከራል፡፡ጭግሩን ያመጡትን ነገሮችን በመታከም ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች ስላሉ ባለሙያዎትን ማማከርን አይርሱ፡፡ 

 

የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች

  • የብልት አልቆብ ማለት
  • የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ቶሎ መልፈስፈስ( Trouble keeping an erection)
  • የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ

የህክምና ባለሙያዎትን ማማከር ያለቦት መቼ ነዉ?

  • የብልት ያለመቆም ችግር ወይም ሌሎች የወሲብ ችግሮች እርስዎንና አጋርዎን ካስጨነቅዎ
  • ከብልት ያለመቆም ችግር ጋር ተያያዥ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ የስኳር፣የልብ ህመም ወይም ሌሎች የጤና ችግሮች ካለዎ
  • ከስንፈተ ወሲብ ጋር የሚገናኙ የማይመስሉ ሌሎች የህመም ምልክቶች ከስንፈተ ወሲብ ጋር አብሮ ካለዎ

ለብልት ያለመቆም ችግር ምክንያቶች ምንድንናቸዉ?

ለወንዶች የወሲብ ስሜት መነቃቃት አእምሮ፣ሆርሞኖች፣ ነርቮች፣ጡንቻዎች፣የደም ስሮችና ስሜት( emotions ) የሚሳተፉ ሲሆን ይህ እጅግ ውስብስብ ነዉ፡፡የብልት ያለመቆም ችግር ከእነዚህ በአንዱ ወይም በሌለኛዉ ላይ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ሊመጣ ይችላል፡፡ ጭንቀትና የስነ አዕምሮ ችግሮች ችግሩን ሊባብሱት ይችላሉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮች የብልት ያለመቆም ችግርን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡

የብልት ያለመቆም ችግርን ሊያመጡ የሚችሉ አካላዊ ችግሮች

  • የልብ ህመም
  • የደም ስሮች መዘጋት( atherosclerosis)
  • የደም ግፊት መጨመር(የደም ብዛት)
  • የኮሌስትሮል መጨመር
  • የስኳር ህመም
  • ዉፍረት
  • የፓርኪንሰንስ ህመም
  • መልትፕል ስኬሎሮሲስ
  • የወንዶች ሆርሞን(ቴስቴስትሮን) መጠን መቀነስ
  • በወንዶች ብልት ዉስጥ ጠባሳ መፈጠር(ፔይሮኒስ ህመም)
  • ለህክምና የሚታዘዙ መድሃኒቶች
  • መጠጥ(አልኮሆል) ና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች
  • የፕሮስቴት ዕጢ መደግ ወይም የፕሮስቴት ዕጢ ህክምና
  • በዳሌ አካባቢ ወይም በህብለሰረሰር ላይ በሚደረግ ቀዶጥገና ወቅት የሚደርስ አደጋ

የብልት ያለመቀም ችግር የሚያመጡ ስነልቦናዊ ምክንያቶች፡-

አዕምሮ ተከታታይነት ያለዉ አካላዊ ሁነቶችን በማነሳሳት ለብልት መቆምና ወሲባዊ ደስታዎችን በማምጣት ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል፡፡ ለወሲባዊ ስሜቶች ችግርና  ለብልት ያለመቆም ችግርን የሚያባበሱ የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ከነዚህም ዉስጥ፡-

  • ድብርት፣መረበሽ ወይም ሌሎች የስነአዕምሮ ችግሮች
  • ጭንቀት
  • በጭንቀት ምክንያት የግንኙነት ችግሮች፣የሰዉ ከሰዉ ተግባቦት ችግር ወይም ሌሎች ነገሮች

ለብልት ያለመቆም ችግር የሚያጋልጡ  ነገሮች

ዕድሜዎ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ብልት ለመቆም ረዘም ያለ ሰዓት የሚወስድ ሲሆን ከቆመም በኃላ በጣም ጠንካራ ላይሆን ይችላል፡፡ዕድሜ እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት የብልት ያለመቆም ችግር የሚከሰተዉ ከእድሜ መጨመር ጋር አብረዉ የሚመጡ የጤና ችግሮችና የሚወስዷቸዉ መድሃኒቶች ስላሉ ነዉ፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ችግሮች

  • የውስጥ ደዌ ችግሮች፡- ስኳርና የልብ ችግሮች
  • ሲጋራ ማጨስ
  • ዉፍረት፡-በተለይ በጣም መወፈር
  • የተወሰኑ መድሃኒቶች፡ለድብርት፣ለአለርጂዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች፣ለካንሰርና ለደም ግፊት ህክምና የሚሰጡ መድሃኒቶች
  • አደጋ፡-በተለይ ለብልት መቆም የሚረዳዉ ነርቭ ላይ አደጋ ሲደርስ
  • ስነልቦናዊ ችግሮች፡- ጭንቀት፣ድብርት
  • አደንዛዥ ዕፅና አልኮሆል የሚጠቀሙ፡- በተለይ ረዘም ላለ ጊዜ ለተጠቀሙ

ለረጅም ጊዜ ብስክሌት የሚያሽከረክሩ፡-ይህ ነርቮችን ስለሚጫንና ወደ ብልት በሚሄደዉ የደም ዝዉዉር ላይ ችግር ስለሚያመጣ ግዜያዊ የብልት ያለመቆም ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡

ለብልት ያለመቆም ችግር ጊዜ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች፡-

  • አካላዊ ምርመራ፡- በብልትዎ፣በዘር ፍሬዎና በነረቮች ላይ ምርመራ ማድረግ
  • የደም ምርመራዎች
  • የሽንት ምርመራ
  • የአልትራሳዉንድ ምርመራ
  • በእንቅልፍ ሰዓት የብልት መቆም ምርመራ፡-
  • ስነልቦናዊ ምርመራዎች

ለብልት ያለመቆም ችግር የሚደረጉ ህክምናዎች

መጀመሪያ የሚደረገዉ ለሌላ ህመም እየወሰዱ ያለ መድሃኒት ካለ ለብልትዎ ያለመቆም ችግር ምክንት መሆን ያለመሆኑን ማረጋገጥ

በአፍ የሚዋጡ መድሃኒቶች

  • ሲልደንፊል(ቪያግራ)
  • ታደልፊል(ሲያሊስ)
  • ቫርድንፊል

እነዚህ መድሃኒቶች የሚሰሩት ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ሲሆን የብልትዎን ጡንቻዎች በማላላትና ወደ ብልት የሚሄደዉን ደም በመጨመር ወሲባዊ መነቃቃት በሚፈጠርበት ወቅት ብልትዎ እንዲቆም ያደርጋሉ፡፡እነዚህን መድሃኒቶች ከመዉሰድዎ በፊት የጤና ባለሙያዎትን ማማከር ያስፈልጋል፡፡እነዚህ መድሃኒቶች የሚከተሉት ነገሮች ካሉ ላይሰሩ ይችላሉ ወይም ለጤና አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡-

  • ናይትሬት ያላቸዉን መድሃኒቶች እየወሰዱ ከሆነ(ናይትሮግላይሴሪን)
  • ለደም ማቅጠኛ የሚሰጡ መድሃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ፣አልፋ ብሎከርስ የሚባሉና ለፕሮስቴት ህክምና እየወሰዱ ከሆነ፣የደም ግፊት መቀነሻ መድሃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ
  • የልብ ችግር ወይም ድካም ካለዎት
  • የደም ግፊት በጣም መቀነስ ካለዎት ወይም በህክምና ያልተቆጣጠረ የደም ብዛት ካለዎት
  • በስትሮክ ከዚህ በፊት ታመሁ ከሆነ
  • በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም ካለዎት

ሌሎች መድሃኒቶች

  • እራስን በራስ የሚወጉ አልፕሮስታዲል
  • በብልት የሚገቡ አልፕሮስታዲል
  • የወንዶች ሆርሞንን(ቴስቴስትሮን) መተካት

ከመድሃኒቶች አልሰራ ካሉ ወይም በተለያ ምክንያት መድሃኒቶችን መጠቀም የማቻል ከሆነ ሀኪምዎ የሚከተሉትን ሊያዝሎት ይችላል

  • ፔኒስ ፓምፕ
  • ፔኒስ ኢምፕላንትስ
  • የደም ስር ቀዶጥገናዎች

ስነልቦናዊ ምክሮች

የብልት ያለመቆም ችግርዎ ከጭንቀት፣መረበሽ ወይም ድብርት ጋር የተገናኘ ከሆነ የስነዓዕምሮ ባለሙያዎችን ወይም የስነልቦና ባለሙያዎችን ማማከር ያስልጋል፡፡ የብልት ያለመቆም ችግር የመጣዉ አካላዊ በሆነ ችግር ቢሆን እንኳ ጭንቀትና የግንኙነት ችግር ማምጣቱ ስለማይቀር እነዚህን ባለሙያዎች ማማከር ይጠቅማል፡፡

የኑሮ  ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ

  • ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቛረጥ
  • ክብደትን መቀነስ
  • የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ/ማዘዉተር
  • አደንዛዥ ዕፅ ወይም አልኮሆል በመዉሰድ እየተቸገሩ ከሆነ ህክምና ማግኘት
  • የግንኙነት ችግሮች ካለቦት መፍትሄ መፈለግ

ተጨማሪ ምክሮች

  • ችግሩ ለረጅም ጊዜ ያለ/የሚቀጥል ነዉ ብሎ ያለመዉሰድ
  • የትዳር ወይም የፍቅር አጋረዎን በመፍትሄዉም ይሁን በችግርዎ ዉስጥ አጋር ማድረግ
  • ጭንቀትን፣መረበሽንም ይሁን ማንኛዉንም የስነአዕምሮ ችግሮች ችላ ብሎ ያለማለፍ

ከመጠን በላይ የሆነ ላብ ማላብ ሀይፐርሀይድሮስስ ይባላል፡፡
ሀይፐርሀይድሮስስ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ በእጅ መዳፍ፤በእግር መዳፍ(የዉስጥ እግር)ና ብብት ዉስጥ ሲሆን እንደ ጤና ችግር የሚቆጠረዉ የእረስዎን የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን የሚያስተጓጉል ከሆነ ነዉ፡፡ ሀይፐርሀይድሮስስ የእለት ከዕለት እንቅስቃሴዎትን ከማስተጓጎሉም በተጨማሪ ማህበራዊ ጭንቀትንና እፍረትን ሊያስከትል ይችላል፡፡


ሃኪሞትን ማማከር የሚገባዎት መቼ ነዉ?


• ላቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን ካስተስጓጎሎት
• ያልተለመደ ከበፊቱ የተለየ ብዙ የሚያልቦት ከሆነ
• ምክንያቱን ያላወቁት ማታ ማታ ላብ ካለዎት

ይኸንን ችግር ለማሻሻል ከሚረዱ ዘዴዎች ዋነኛዉ የላብን መመረት የሚቀንሱ መድሀኒቶችን መጠቀም ሲሆን ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ከሆነ ደግሞ ላብን ከመጠን በላይ የሚያመርቱትን የላብ ዕጢዎች ወይም ወደ ላብ ዕጢዎች የሚሄዱትን ነርቮች በቀዶጥገና እንዲስተካከል ማድረግ ይቻላል፡፡


አጠቃላይ ምክሮች


• በየቀኑ መታጠብ፡ ይህን ማድረግዎ በሰዉነትዎ ላይ ያሉትን የባክቴሪያ መጠን ይቀንሳል
• ሻወር ከወሰዱ በኃላ እግሮትን በደንብ ማድረቅ፡ በጣትዎት መካከል በደንብ ማድረቅ፤ፓዉደር መጠቀም
• የሚጠቀሙትን ጫማና ካልሲ መምረጥ፡ ጫማዎትንና የጫማዎትን ሶል ከቆዳ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል
• ጫማዎትን መቀያየር፡ አንድን ጫማ ከሁለት ቀን በላይ ያለማድረግ
• የሚጠቀሙት ካልሲ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከጥጥ ወይም ከሱፍ የተሰሩ ካልሲዎች እርጥበትን የመምጠጥ ባህሪይ ያላቸዉ ሲሆን እንቅስቃሴ በጣም በሚያበዙበት ወቅት ደግሞ እርጥበትን በደንብ ሊመጡ የሚችሉ የአትሌት ካልሲ የሚባሉትን መጠቀም ይመረጣል
• እግሮት አየር እንዲያገኝ ማድረግ፡ በሚመቾት ሰዓት እግሮትን ከጫማ ማዉጣትና ማናፈስ፤እቤት ዉስጥ ደግሞ ባዶ እግር ወይም ነጠላ ጫማ ማድረግ
• ከጥጥ፤ ሱፍ ወይም ናይለን የተሰሩ ልብሶችን ማዘዉተር፡ እነዚህ አየር በደንብ እንዲዘዋወር ያደርጋሉ

ጨቅላ ህፃንዎን መመገብ ያለማቛረጥ የሚደረግ ሃላፊነት ነዉ፡፡ አዲስ ከመጣዉ የቤተሰብ አባልዎ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመመስረት ጥሩ አጋጣሚን የሚፈጥርዎ እደል ነዉ፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን ሰባት ነጥቦች/ምክሮች ጨቅላ ህፃንዎን ለመመገብ ይረዳዎ ይችላል፡፡

1. የጡት ወተት ወይም የቆርቆሮ ወተት ብቻ መጠቀም፡-


ብዙዉን ጊዜ ለህፃናት እድገት የሚመከረዉና የሚመረጠዉ የእናት ጡት ነዉ፡፡ ጡትዎን እንዳያጠቡ የሚያስገድድዎ ነገር ካለ/ጡት ማጥባት የማይችሉ ከሆነ ግን የቆርቆሮ ወተቶችን (ፎርሙላ ወተትን) መጠቀም ይቻላል፡፡ ጤናማ ህፃናት እስከ 6 ወር ድረስ ዉሃ፣ ጭማቂም ይሁን ሌላ ፈሳሾችም ቢሆን አያስፈልጋቸዉም፡፡ (ጡትና ጡት ብቻ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡)


2. አዲስ የተወለደ ልጅዎን በሚፈልግበት ሰዓት መመገብ፡-


አዲስ የተወለደ ልጅዎ በቀን ከስምንት እስከ አስራ ሁለት ጊዜ መመገብ ይገበዋል፡፡ ይህ ማለት በየሁለትና ሶስት ሰዓት ልዩነት መመገብ ያስፈልጋል ማለት ነዉ፡፡ ህፃኑ ምግብ ሲፈልግ/ሲራብ የመወራጨት፣ መጥባት ምልክቶችንና ከንፈሮቹን ማንቀሳቀስ ይጀምራል፡፡ እነዚህን አይተዉ ካላጠቡት/ካልመገቡት ማልቀስ ይጀምራል፡፡ ልጅዎ መጥባቱን ካቆመ ወይም አፉን ከዘጋ አልያም ፊቱን ከጡት ወይም ጡጦ ላይ ካዞረ የመጥገብ ምልክት ሊሆን ይችላል ወይም እረፍት እየወሰደ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ጡትዎንም ይሁን ጡጦ ከመስጠትዎ በፊት ትንሽ ጊዜ ይጠብቁ፡፡
የልጅዎ እድሜ እየጨመረ ሲመጣ በትንሽ ሰዓት ዉስጥ ብዙ እየተመገበ ይመጣል፡፡


3. ቫይታሚን ዲ መስጠት፡


የጡት ወተት ለልጅዎ አጥንት ጥንካሬ የሚሰጡ እንደ ካልሲየምና ፎስፈረስ ያሉ ማዕድናቶች ከልጅዎ አንጀት እንዲመጠጥ የሚያደረገዉን ቫይታሚን ዲ በበቂ መጠን ስለሌለዉ የህክምና ባለሙያዎን በማነጋገር ተጨማሪ ቫይታሚን ዲ (ሰፕልመንት) እንዲሰጠዉ መጠየቅ:: ለልጆች ሌላ የቫይታሚን ዲ ማግኛ አማራጭ የቫይታሚን ዲ ምንጭ ከሆኑት ነገሮች አንዱ የሆነዉ የፀሃይ ብርሃን ሲሆን ብዙ ሰዎች የፀሃይ ብርሃን በመሞቅ ብቻ የተወሰነ የቫይታሚን ዲ ፍላጎታቸዉን ሊያሟሉ ይችላሉ፡፡ እርስዎም ልጅዎን ቫይታሚን ዲ ለልጅዎ መስጠት ካልቻሉ እንደአማራጭ ሁልጊዜ የፀሀይ ብርሃን ማሞቅ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም በየቀኑ የጠዋት የፀሃይ ብርሃን ሙሉ ሰዉነቱን ከሆነ ከ10-15 ደቂቃዎች ማሞቅ የሚያስፈልግ ሲሆን ጭንቅላቱን፣ እጅና እግሮቹን ብቻ የሚያሞቁት ከሆነ ደግሞ ለ30 ደቂቃዎች ያህል ማሞቅ ያስፈልጋል፡፡


4. አዲስ የተወለደ ልጅዎ የአመጋገብ ስርዓቱ/ሂደት ሊለያይ እንደሚችል መገመት


አዲስ የተወለደ ልጅዎ በየቀኑ የግድ አንድ አይነት መጠን ያለሙ አመጋገብ ላይኖረዉ ይችላል፡፡ እድገቱ በፍጥነት በሚሆን ወቅት ለምሳሌ ከተወለደ በ2ኛና በ3ኛዉ ሳምንት እንዲሁም 6ኛ ሳምንቱ አካባቢ በአንድ ጊዜ ብዙ ሊመገብና እንዲሁም ቶሎ ቶሎ ሊርበዉ ስለሚችል ከላይ የተጠቀሰዉን የሰዓት ገደብ ሳይጠብቁ በቶሎ የልጅዎን የረሃብ ስሜት ምልክቶች በመረዳት መመገብ ያስፈልጋል፡፡


5. ዉስጥዎን/ደመ ነፍስዎንና ልጅዎን ማመን

 

ልጅዎ በቂዉን ያህል አልተመገበም ብለሁ ሊጨነቁ ይችላሉ፡፡ ነገርግን ልጅዎ ምን ያህል እንደሚያስፈልገዉ እራሱ ያዉቃል፡፡ ልጁ ምን ያህልና በምን ያህል ልዩነት ተመገበ ላይ ሳይሆን በሚከተሉት ነገሮች ላይ ባይበልጥ ትኩረት ማድረግ
• ቐሚ/ተከታታይነት ያለዉ ክብደት መጨመሩን
• በአመጋገቡ መካከል እርካታ/ምቾት መኖሩን
ልጅዎ ክብደት እየጨመረ የማይመጣ ከሆነና የመመገብ ፍላጎት ከሌለዉ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

 

6. እያንዳንዱን የመመገቢያ ጊዜ ከልጅዎ ጋር የጠበቀ ግንኙነት/ትስስር( bond) የሚፈትሩበት ጊዜ አድርጎ መዉሰድ


በሚመግቡበት ወቅት ልጅዎን ወደራስዎ/ሰዉነትዎ አስጠግቶ መያዝ፤ የልጅዎን እይን አይኑን ማየት፤ በቀስታ ከልጅዎ ጋር ማዉራት እንዲሁም እያንዳንዱን የመመገቢያ ወቅት የልጅዎን የደህንነት ስሜት( sense of security )፣ አመኔታና( trust) ምቾት እንዲሰማዉ ለማጎልበት አጋጣሚዉን ሊፈጥርልዎ ይችላል፡፡


7. እርዳት መቼ እንደሚያስፈልግዎ ማወቅ/መረዳት


ለምሳሌ ጡት በማጥባት ወቅት ችግር ከገጠመዎ፤ ጡት በሚያጠቡበት ወቅት ህመም ካለዉ ወይም ልጅዎ ክብደት የማይጨምር ከሆነ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

የማህፀን አንገት ካንሰር ከማህፀን አንገት ሴሎች የሚነሳ የካንሰር አይነት ነዉ፡፡ ለብዙዎቹ የማህፀን አንገት ካንሰር መከሰት ከፍተኛዉን ሚና የሚጫወተው ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ/ human papillomavirus /የሚባለዉና በግብረስጋ ግንኙነት አማካይነት የሚተላለፈዉ የቫይረስ አይነት ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

ህመሙ በሚጀምርበት  የመጀመሪያ ጊዜያቶች ምንም አይነት የሚታይ የህመም ምልክት ላይኖር ይችላል፡፡ ህመሙ እየቀጠለ ሲመጣ ግን የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡

  • የግብረስጋ ግንኙነት ካደረጉ በኃላ፣ በወር አበባ ዑደት መካከል ወይም ካረጡ በኃላ ከብልት ደም መታየት
  • ዉሃማ፣ ደምነትና ሽታ ያለዉ ፈሳሽ መጠነኛ ወይም ከፍተኛ በሆነ መጠን ከብልት መፍሰስ
  • የዳሌ ዉስጥ ህመም፣ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡


የህመሙ መንስኤ

የማህፀን አንገት ካንሰር የሚከሰተዉ የማህፀን አንገት ሴሎች ጤነኛ ወዳልሆኑ ሌሎች ሴሎች በሚለወጡበት ወቅት( genetic change (mutation)) የሚመጣ ነዉ፡፡

የማህፀን አንገት ካንሰር መንስኤዎች በትክክል ምን እንደሆኑ ባይታወቅም ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ብዙ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በዚህ ቫይረስ የተያዙ ሁሉም ሴቶች የማህፀን አንገት ካንሰር ይያዛሉ ማለት ግን አይደለም፡፡ ስለሆነም ሌሎች እንደ አካባቢያዊና የአኗኗር ዘይቤ ለችግሩ መፈጠር ሚና ሊኖራቸዉ ይችላሉ፡፡

ለህመሙ የሚያጋልጡ ነገሮች

  • ከአንድ በላይ የወንድ ጓደኛ ያላቸዉ ሴቶች፡- ከብዙ ወንዶች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት የሚያደርጉ ሴቶች ወይም ከብዙ ሴቶች ጋር ግንኑነት ካለዉ ወንድ ጋር ጥንቃቄ የጎደለዉ የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያደርጉ ሴቶች በሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ የመያዝ እድላቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
  • በለጋነት እድሜ የግብረስጋ ግንኙነት መጀመር፡-እድሜያቸዉ ከ18 አሜታት በታች እያሉ የግብረ ስጋ ግንኑነት የሚጀምሩ በቫይረሱ የመጠቃት እድሉ ይጨምራል፡፡
  • በሌሎች የአባለዘር ህመሞች መያዝ፡- እንደ ጨብጥ፣ ከርክርና ሌሎች አባለዘር ህመሞች መያዝ በሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ የመያዝ እድሉን ይጨምራል፡፡
  • የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ/ የቀነሰ ከሆነ፡- የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን ካለና የበሽታ መከላከል አቅም የደከማ አሆነ በማህፀን አንገት ካንሰር የመያዝ እድሉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡
  • ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ ለማህፀን አንገት ካንሰር ያጋልጣል፡፡

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች

ለማህፀን አንገት ካንሰር የሚደረጉ ህክምናዎች እንደ ካንሰሩ የህመም ደረጃ፣እንዳለዎት ሎሎች የህመም አይነቶችና የህክምና ምርጫዎ ሊለያይ ይችላል፡፡ስለሆነም ሊሰጡ ከሚችሉ የህክምና ዘዴዎች ዉስጥ ቀዶ ጥገና፣የጨረር ህክምና፣ኬሞቴራፒና ከሶስቱ ዉስጥ አንዱን ከአንዱ ጋር በማዳበል ሊሆን ይችላል፡፡

 

የተከበራችሁ ወዳጆቻችን፤ በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ ብዙዎቻችሁ ስለፎረፎር መረጃ እንድንሰጣችሁ አስተያየቶቻችሁን ኢንቦክስ ባደረጋችሁልን መሰረት በፎረፎር ችግር ላይ የተወሰኑ መረጃዎች እነሆ:-

ፎረፎር ብዙ ጊዜ የሚከሰትና የራስ ቆዳ እየተቀረፈ እንዲፈረፈር፣ እነዲላላጥና እንዲራገፍ የሚያደርግ የራስ ቆዳ ችግር ነዉ፡፡ ምንም እንኳ ፎረፎር ከአንድ ሰዉ ወደሌላ ሰዉ የማይተላለፍና ከፍ ያለ ችግር የማያስከትል የቆዳ ችግር ቢሆንም ሀፍረትን ሊያስከትል እና ለህክምና አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለፎረፎር ጥሩ ነገሩ በቀላሉ መቆጣጠር መቻሉ ነዉ፡፡ ቀላል የፎረፎር አይነት በተከታታይነት በሻምፖ ከማፅዳት በላይ ብዙ የተለየ ነገር ማድረግ አያስፈልገዉም፡፡ ከፍ ያለ የፎረፎር አይነት ከሆነ ግን ፎረፎርን ለማከም የሚረዱ የሻምፖ አይነቶችን በመጠቀም ችግሩ እንዲቃለል ማድረግ ይችላል፡፡


የህመሙ ምልክቶች


ለብዙዉዎቹ ታዳጊዎችና አዋቂዎች ፎረፎርን እንዳዩት መለየት በጣም ቀላል ሲሆን ምልክቶቹ ነጭ የሆነ፣ ነጠብጣብ መሳይ ወዝነት ያለዉ በፀጉርና በትከሻ ላይ የሚራገፍ የሞቱ የቆዳ ሴሎች፣ ማሳከክና የራስ ቆዳ እንደ ቅርፊት መቀረፍ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ ይህ ችግር የቆዳን መድረቅ ሊያባብሱ የሚችሉ ሞቃታማ የአየር ሁኔታዎች ወቅት የሚባባስ ሲሆን በቀዝቃዛማ ወቅቶች ችግሩ ይቀንሳል፡፡
ህፃናት ላይ ክረድል ካፕ( cradle cap ) የሚባለዉ የፎረፎር አይነት ሚታይ ሲሆን ምልክቶቹ ከህፃናቱ ጭንቅላት ላይ እየተቀረፈ የሚነሳ ነገር ይታያል፡፡ ይህ ሁኔታ አብዛኛዉ ጊዜ በጨቅላ ህፃናት ላይ የሚታይ ቢሆንም በየትኛዉም የህፃንነት እድሜ ክልል ሊታይ ይችላል፡፡ ምንም እንኳ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ወላጆችን የሚያሳስብ ጉዳይ ቢሆንም ክረድል ካፕ በህፃናቱ ላይ የሚያመጣዉ ጉዳት የሌለ ከመሆኑም በላይ የልጁ እድሜ 3 አመት እየሆነዉ ሲሄድ ችግሩ በራሱ ጊዜ እየጠፋ ይመጣል፡፡

የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?

 

ብዙዎቹ የፎረፎር ችግሮች የህክምና ባለሙያ እገዛ/ምክር አያስፈልጋቸዉም፡፡ ነገር ግን ለሳምንታት ያህል ያለሀኪም ትእዛዝ ሊገዙ የሚችሉትን የፎረፎር ሻምፖዎች እየተጠቀሙ ቆይተሁ አሁንም ፀጉርዎ የሚያሳክኮት ከሆነ፣ ወይም የራስ ቆዳዎ ከቀላ ወይም ካበጠ የህክምና ባለሙያዎን ወይም የቆዳ ህክምና ባለሙያዎችን ያማክሩ፡፡ ምናልባት ከፎረፎር ጋር ተመሳሳይነት ያላቸዉ ሌላ ነገር ወይም ሴቦሪክ ደርማታይትስ የሚባለዉ ችግር ሊሆን ስለሚችል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ የህክምና ባለሙያዎ ያለተጨማሪ ምርመራ ፀጉርዎንና የራስ ቆዳዎን በማየት ችግሩን ሊለይ ይችላል፡፡


የፎረፎር ምክንያቶች፡-


ፎረፎር የተለያዩ መንስኤዎች ያሉት ሲሆን የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡

• የቆዳ ድርቀት፡-
የቆዳ ድርቀት ብዙዉን ጊዜ ለፎረፎር መከሰት አይነተኛ ምክንያት ነዉ፡፡ ከደረቀ ቆዳዎ የሚራገፉ ነገሮች በጣም መጠኑ ትንንሽ የሆኑ ቡናኝና ወዝነት የሌለዉ ሲሆን ምናልባትም ከራስ ቆዳዎ ዉጪ በሌላ የሰዉነትዎ ክፍልዎ ላይ ድርቀት ሊታይ ይችላል፡፡
• ሴቦሪክ ደርማታይትስ(የተቆጣ፣ወዛማ ቆዳ)፡-
ይህ ብዙዉን ጊዜ ለፎረፎር መከሰት ምክንያት ከሆኑት ዉስጥ አንዱ ሲሆን ዋና መለያዉ ቀይ፣ ወዛማ ቆዳ ሆኖ የተፈረፈረ ነጭ ወይም ቢጫማ ቅርፊት መሳይ ያለዉ የቁዳ መልክ ነዉ፡፡ ሴቦሪክ ደርማታይትስ ቅባትነት ያለዉ ፈሳሽ የሚመነጩ ዕጢዎች( oil glands) በብዛት በሚገኙበት የራስ ቆዳን ጨምሮ እንደ ቅንድብ፣ የአፍንጫ ግራና ቀኝ፣ የጆሮ ግንድ፣ በጡት መካከል በደረት ላይ ባለዉ አጥንት ላይ፣ ብሽሽትና አንዳንዴ ብብት ስር በብዛት ይከሰታል፡፡
• በብዛት የማይታጠቡ ከሆነ፡-
ፀጉርዎን ተከታታይነት ባለዉ መልኩ የማይታጠቡ ከሆነ የራስዎ ቆዳ የሞቱ ሴሎችና ወዝ በላይ በላዩ ስለሚደራረብ ለፎረፎር ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡
• ሌላ የቆዳ በሽታ ሲኖር፡-
ኤክዜማ ወይም ሶሪያሲስ የሚባሉትን የቆዳ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ፎረፎር ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡
• ፈንገስ(ማላሴዚያ)፡-
ማላሴዚያ የሚባለዉ የፈንገስ አይነት በአብዛኛዉ ሰዎች የጭንቅላት ቆዳ ላይ የሚኖር ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ላይ የጭንቅላት ቆዳን የመቆጥቆጥ ባህሪይ አለዉ፡፡ ይህ ቆዳን የመቆጥቆጥ ባህሪይ ብዙ የቆዳ ሴሎች በጭንቅላት ቆዳ ላይ እንዲያድጉ ስለሚደርግ እነዚህ በገፍ ያደጉት ሴሎች ሲሞቱ ነጭ፣ ወዛማ ነገር ሆነዉ በፀጉርና ትከሻዎ ላይ ይራገፋሉ፡፡
• ለፀጉር ዉበት መጠበቂያነት የሚጠቀሙት ነገሮች በጭንቅላት ቆዳዎ ላይ አለርጂ ካመጣብዎ (ኮንታክት ደርማታይትስ/contact dermatitis)፡-
አንዳንድ ለራስ ለፀጉር መዋቢያነት የሚጠቀሙባቸዉ ነገሮች ወይም ቀለሞች አንዳንድ በዉስጣቸዉ ያሉ የተሰሩባቸዉ/የተቀመሙባቸዉ ነገሮች (ለምሳሌ ፓራፌኒይልኢንዳሚን) በራስ ቆዳዎ ላይ የመቅላት፣ የማሳከክና መቀረፍ ባህሪይ እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡ በጣም በተደጋጋሚ መታጠብ ወይም የፀጉር ዉበት መጠበቂያ ዉጤቶችንም አብዝቶ መጠቀም የጭንቅላት ቆዳዎን በመቆጥቆጥ ለፎረፎር ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡

 

የፎረፎርን ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች


ሁሉም ሰዉ እኩል በሚባል ደረጃ ፎረፎር የመያዝ እድል ቢኖራቸዉም የተወሰኑ ነገሮች/መንስኤዎች ተጋላጭነትዎን ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ እነርሱም
• እድሜ፡-
ፎረፎር ብዙዉን ጊዜ በወጣትነት እድሜ የሚከሰት ሲሆን እስከ መካከለኛዉ የእድሜ ክልል ሊዘልቅ ይችላል፡፡ይህ ማለት ፎረፎር በጎልማሳነትና በእርጅና ወቅት አይከሰትም ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ፎረፎር እስከ እድሜ ልካቸዉ ላይተዋቸዉ/ላይጠፋላቸዉ ይችላል፡፡
• ወንድ መሆን፡-
ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ ፎረፎር ስለሚበዛ አንዳንድ ተመራማሪዎች ይህ ክስተት ከወንዶች ሆርሞን ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል ይላሉ፡፡ ሌላዉ በወንዶች ላይ ለፎረፎር መከሰት አስተዋፅኦ የሚያደርግ በጭንቅላት ቆዳቸዉ ላይ ብዙ የስብ እጥዎች አሉዋቸዉ፡፡
• ወዛማ ፀጉርና የራስ ቆዳ፡-
ማላሴዚያ የሚባለዉ የፈንገስ አይነት በጭንቅላት ቆዳ ላይ ያለዉን ስብ/ዘይት መሳይ ነገር የሚመገብ ሲሆን በጣም የበዛ ወዛማ ቆዳና ፀጉር ለፎረፎር መጋለጥ/መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
• ያልተመጣጠነ ምግብ (Poor diet):-
የሚመገቡዋቸዉ ምግቦች እንደ ዚንክ፣ ቫይታሚን ቢ ና የተወሰኑ የስብ ዘሮችን የማይመገቡ ከሆነ ለፎረፎር ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
የተወሰኑ ህመሞች ፡- ምክንያቱ በዉል/በትክክል ባይታወቅም የነርቭ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች(ምሳሌ ፓርኪንሰን)፣ኤች አይ ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ፣ ከተወሰነ አስጨናቂ ህመሞች እያገገሙ ያሉ( ስትሮክ፣የልብ ችግር) እና የሰዉነት በሽታ የመከላከል አቅም የቀነሰባቸዉ ሰዎች ለፎረፎርና መሰል የቆዳ ችግሮች የተጋለጡ ናቸዉ፡፡


የፎረፎር ህክምና


ፎረፎርን በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ትዕግስትና ሳይታክቱ ክትትል ይፈልጋል፡፡ የፀጉርን ንፅህና መጠበቅ የቆዳዉንና የፀጉሩን ወዛማነትና የሞቱትን ሴሎች ስለሚቀንስ መጠነኛ የፎረፎር ችግሮችን እንዲቀንሱ ያደርጋል፡፡
የተለያዩ የፎረፎር ሻምፖዎች ያሉ ሲሆን እንደሚይዙት መድሃኒት እንደሚከተሉት ይከፈላሉ፡፡
• ዚንክ ፓይሪቲዮን ሻምፖ( Zinc pyrithione shampoos)፡- ይህ ፀረ ባቴቴሪያና ፀረ ፈንገስ መድሃኒት የያዘ ሲሆን ፎረፎርን ለመቀነስ ያገለግላል::
• ታር ቤዝድ ሻምፖስ- Tar-based shampoos (ለምሳሌ ንዩትሮጅን ቲ ጄል)፡- ነዳጅ ሲጣራ ተረፈ ምርት የሆነዉ ኮል ታር የቆዳ ሴሎች የመሞትና የመራገፍ ሂደትን በመቀነስ ለፎረፎር፣ ለሰቦሮይክ ደርማታይትስና ሶሪያሲስ ለመሳሰሉ የቆዳ ችግሮች ህክምና ያገልግላል
• ሳሊሲሊክ አሲድ የያዙ ሻምፖዎች፡- ይህ የቆዳን መቀረፍ ያስወግዳል፤ ነገር ግን ቆዳዎ እንዲደርቅ ስለሚያደርግ ለበለጠ የቆዳ መፈግፈግ ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡ ስለሆነም ድርቀቱን ለመከላከል ሻምፖዉን ከተጠቀሙ በኃላ ኮንዲሽነር መጠቀም ችግሩን ያቃልለዋል፡፡
• ሴሊንየም ሰልፋይድ ሻምፖዎች(ምሳሌ ሴልሰን ብሉ)፡- ሴሊሰን ብሉ የቆዳ ሴሎችን የመሞት ሂደትንና ማለሴዚያ ፈንገስን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
• ኬቶኮናዞል ሻምፖ -Ketoconazole shampoos (ምሳሌ-ኒዞራል)፡- ኬቶኮናዞል ሻምፖ ኬቶኮናዞል የሚባለዉን ፀረ ፈንገስ መድሃኒት የያዘ ሲሆን ሌሎች የሻምፖ አይነቶች ሳያሽሉ ሲቀሩ የሚሰጥ ነዉ፡፡

ከእነዚህ ሻምፖዎች አንዱን ፎረፎሩ እስኪሻልዎ አንድ ቀን እያለፉ መጠቀም፤ ከዚያን በሳምንት ሶስት ቀን ብቻ ማድረግ፡፡ አንዱ ሻንፖ ለዉጥ እያሳየ ቆይቶ የመስራት አቅሙ ከቀነሰብዎ ሌላ የሻምፖ አይነት በመግዛት እያፈራረቁ መጠቀም፡፡ ሻምፖዉን ሲጠቀሙ በደንብ ከራስ ቅል ቆዳዎ ጋር ማሸት፣ ከዚያን ለ5 ደቂቃዎች መጠበቅ (ይህ በሻምፖ ዉስጥ ያለዉ መድሃኒት እንዲሰራ እድል ይሰጠዋል)፡፡ ሻምፖዎችን ለተወሰኑ ሳምንታት ተጠቅመዉ ምንም አይነት ለዉጥ ከሌለዉ የቆዳ ህክምና ባለሙያ ማማከር ይመከራል፡፡


ሊደረጉ የሚችሉ የቤት ዉስጥ ህክምና


• ጭንቀትን እንዴት ማስወገድ እንዳለብዎ ማወቅ
• ንፅህናዎን መጠበቅ
• ጤናማ አመጋገብ መከተል
• የተወሰነ የፀሀይ ብርሃን መሞቅ

ስለወር አበባ ዑደትዎ ትክክል የሆነዉና ያልሆነዉ  ነገር ምንድን  ነዉ?

የወር አበባዎን መከታተል ስለእርስዎ የወር አበባ ዑደት ትክክል የሆነዉን ለመረዳት፣እንቁላል ከአብራኳ የምትወጣበትን ጊዜ ለማወቅና ሌሎች አስፈላጊ ለዉጦችን ለመለየት ይጠቅምዎታል፡፡  ለምሳሌ የወር አበባ ዑደት መዘግየትን ለማወቅ ወይም ቀኑን ያልጠበቀ የወር አበባ መፍሰስ የመሳሰሉትን ለመከታተል ይረዳል፡፡ ምንም እንኳ የወር አበባ ዑደት መዛባት ሊከሰት የሚችል ነገር ቢሆንም አንዳንዴ የህመም ማሳያም ሊሆን ይችላል፡፡

ስለወር አበባ ዑደት ትክክል የሆነዉ/ኖርማል ነገር ምንድነዉ?

 የወር አበባ ዑደት የሚቆጠረዉ መፍሰስ ከጀመረበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከሚቀጥለዉ የወር አበባ ዑደት የመጀመሪያ ቀን ሲሆን ይህ ርዝማኔ በሁሉም ሴቶች ላይ አንድ አይነት አይደለም፡፡ ኖርማል የሚባለዉ የወር አበባ ዑደት በየ 21 እስከ 35 ቀን ባለዉጊዜ ዉስጥ የሚመጣ ሲሆን መፍሰሱ ከሁለት  እስከ ሰባት ቀናት ሊቆይ ይችላል፡፡ የወር አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ማያት በጀመሩበት ጊዜያት/ዓመታት ያሉ የወር አበባ ዑደቶች ርዝማኔ አጫጭር ሲሆኑ እድሜዎ እየጨመረ ሲመጣ ግን እየተስተካከለ ይመጣል፡፡

እድሜዎ እየጨመረ መጥቶ ወደማረጥ ሲቃረቡ ደግሞ የወር አበባ ዑደቱ ተመልሶ እየተዛባ ሊመጣ ይችላል፡፡ እድሜዎ እየጨመረ ሲመጣ ለማህፀን ካንሰር የመጋለጥ እድሉ እየጨመረ ስለሚመጣ የወር አበባ መዛባት በዚህ ጊዜያት ካለዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

የወር አበባ ዑደቱን እንዴት መከታተል ይቻላል?

የራስዎን የወር አበባ ዑደት ትክለኛዉን እርዝማኔ ለማወቅ የወር አበባ ዑደትዎን በካላንደር ላይ መመዝገብ ይጀምሩ፡፡ ይህም የወር አበባ ዑደቱ በትክክል መምጣቱንና አለመምጣቱን ለመከታተል እንዲረዳዎ የወር አበባ ዑደቱ መፍሰስ ከጀመረበት ቀን ጀምረዉ ለተከታታይ ወራት (ቢያንስ ለ6 ወራት) በየወሩ በመደዳ ይመዝግቡ፡፡

ስለሆነም ስለወር አበባ ዑደትዎ የሚያሳሰውብዎ ነገር ካለ በሚከተሉትን ነገሮች ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ይመዝግቡ

  • የመጨረሻ ቀን፡-   

    የወር አበባ ዑደቱ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል? ከተለመደዉ የዑደት እርዝማኔ ማጠር ወይም መርዘም አለዉ ወይ?

  • የአፈሳሰሱ ሁኔታ፡-

    የወር አበባ ዑደቱ የአፈሳሰስ መጠን ከተለመደዉ በላይ ነዉ ወይስ በታች? የንፅህና መጠበቂያዉን በቀን ምን ያህል ጊዜ ይቀይራሉ? የረጋ ደም ይፈሳል ወይ?

  • ያልተለመዳ ከብልት ደም መፍሰስ ካለዎ፡-

    በወር አበባ ዑደትዎ መሃል ከብልት ደም መፍሰስ አለዎ?

  • ህመም፡-

    ከወር አበባ ዑደቱ ጋር ተያያዥነት ያለዉ ህመም አለዎ? ህመሙ ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ የተባባሰ ነዉ?

  • ሌሎች ለዉጦች ካሉ፡-

    የባህሪይ ወይም ፀባይ/ሙድ/ መቀያየር ገጥሞታል? የወር አበባ ዑደት ለዉጥ በነበረበት ወቅት አዲስ የተቀየረ ነገር አለ?

የወር አበባ ዑደት ያለመስተካከልን/መለዋወጥን የሚያመጡ ነገሮች ምንድናቸዉ?

የወር አበባ ዑደት መለዋወጥን የሚያመጡ/ የሚያስከትሉ የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ እነርሱም

  • እርግዝና/ጡት ማጥባት፡-

    የወር አበባ ዑደት መዘግየት ካለ የእርግዝና ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከእርግዝና በኃላ ጡት ማጥባት የወር አበባ ዑደት ተመልሶ ሳይመጣ እንዲዘገይ ሊያደርግ ይችላል፡፡

  • ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም/ Polycystic ovary syndrome (PCOS)፡-

    የዚህ የሆርሞን መዛባት ችግር ያላቸዉ ሴቶች ያልተስተካከለ የወር አበባ ዑደትና የእንቁሊጤ መጠን መጨመር ሊታይ ይችላል( የመጠን መጨመሩ እንቁሊጤዋ ዉሃ ስለምትቋጥር ነዉ፡፡

  • የዳሌ ዉስጥ መቆጥቆጥ /Pelvic inflammatory disease (PID)፡-

    የመራቢያ አካላት ኢነፌክሽን ለዚህ አይነት ችግር ሊዳርግ ይችላል፡፡

  • የማህፀን ላይ እጢ፡-

    የማህፀን ላይ እጢ ካለዎ የወር አበባ ዑደት መጠን መብዛትና መራዘም እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡

  • የተወሰኑ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎች፡-

    የወሊድ መከላከያ እንክብሎች፣ ሉፕና ሌሎችም የወር አበባ ዑደቱን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡


የወር አበባ ዑደት መዛባት እንዳይከሰት እንዴት መከላከል ይቻላል?

ለአንዳንድ ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል መዉሰድ የወር አበባ ዑደቱ ተስተካክሎ እንዲመጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የሚከተሉት ለዉጦች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡

  • እርግዝና ሳይኖር የወር አበባ ዑደትዎ ከ90 ቀናት በላይ መቋረጥ ካጋጠመዎ
  • ተስተካክሎ ይመጣ የነበረዉ የወር አበባ ዑደት መዛባት ከጀመረ
  • የወር አበባ ዑደት ከሰባት ቀናት በላይ መፍሰስ ካለዉ
  • ከተለመደዉ መጠን በላይ የደም መፍሰስ ካለ ወይም በቀን ዉስጥ ከተለመደዉ ቁጥር በላይ የንፅህና መጠበቂ/የወር አበባ ደም መቀበያ ፓድ መቀያየር ካጋጠመዎ
  • የወር አበባ ዑደት እርዝማኔዉ/የሚመጣበትገዜ/ በየወሩ ከ21 ቀናት በታች ካጠረ ወይም ከ35 ቀናት በላይ መዘግየት ካለዉ
  • በወር አበባ ዑደት መካከል የደም መፍሰስ ካለዎ ናቸዉ፡፡

 

ማስታወስ የሚገባዎ ነገር ቢኖር ስለወር አበባ ዑደትዎ ማወቅ ስለእርስዎ የወር አበባ ዑደት ትክክለኛ የሆነዉንና ያልሆነዉን ለመለየት ይጠቅምዎታል፡፡ስለሆነም ከተለመደዉ ዉጪ ትክክል ያልሆነ ነገር ካለዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

10611899_m

ከዚህ በፊት የህፃን ልጅዎን የአጨዋወት፣ አነጋገር/ ቋንቋ፣ እንዴት እንደሚማር እና እንቅስቃሴዎችን እንዴት እንደሚተገብር በመከታተል ስለልጅዎ የእድገት ሁኔታ ፍንጭ ማግኘት እንደሚቻልና የአራት ዓመት ህፃን ሊያሳይ የሚችላዉን ነገሮች መነጋገራችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዚያ የቀጠለ የአምስት አመት ልጅ የእድገት ክትትልን እናያለን፡፡

 

አብዛኞቹ ህፃናት በዚህ እድሜ ምን ምን ነገሮችን ይተገብራሉ?

ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional

  • እንደጓደኛ መሆን ይፈልጋሉ
  • በህግ/በደንብ መስማማት ይችላሉ/ ደንብ ያከብራሉ
  • መዝፈን፣ መደነስና መተወን ይወዳሉ
  • ለሌሎች መጨነቅና ማዝንን ያሳያሉ
  • ስለ ፆታ ልዩነት ያዉቃሉ
  • ምን ሊያሳምን እንደሚችልና ምን ትክክል እንደሆነ መናገር ይችላሉ
  • በራስ መተማመንን ያሳያሉ( ለምሳሌ ሳይፈሩ ጎረቤት ብቻቸዉን መሄድ) ይችላሉ፡፡
  • አንዳንዴ በጣም አስቸጋሪ ይሆናሉ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተባባሪ

ቋንቋ /መግባባት (Language/Communication)

  • ጥርት አድርገዉ ማዉራት ይችላሉ
  • ሙሉ አረፍተነገር በመጠቀም ተረት/ታሪክ መንገር ይችላሉ
  • ወደ ፊት የሚመጣዉን ድርጊት ቃላት/ future tense/ መጠቀም ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ አክስቴ ነገ/በኃላ ትመጣለች ብለዉ ቃላትን በአግባቡ ተጠቅመዉ መናገር ይችላሉ
  • ስምና አድራሻን መናገር ይችላሉ፡፡

አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና  ችግርን መፍታት መቻል)

  • አስርና ከዚያ በላይ የሆኑ እቃዎችን/ ነገሮችን መቁጠር መቻል
  • አንድን ሰዉ ስድስት የሰዉነት ክፍሎችን በማካተት መሳል ይችላሉ
  • የተወሰኑ ፊደላትን/ቁጥሮችን መፃፍ ይችላሉ
  • ትሪያንግል ወይም ሌሎች የጂኦሜትሪ ቅርፆችን ኮፒ ማድረግ ይችላሉ
  • በየቀኑ የምንጠቀምባቸዉን ነገሮች መረዳት/ማወቅ ይችላሉ፡ ለምሳሌ ገንዘብ፣ ምግብ

እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development

  • በሁለት እግር መዝለል መቻል
  • በሹካ/ማንኪያ መጠቀም መቻል
  • ሶፋ/ምንጣፍ ላይ ወደፊት መገለባበጥ መቻል
  • ራሳቸዉን ችለዉ መፀዳጃ ቤት መጠቀም መቻል
  • ዥዋዥዌ መጫወትና መሰላል/ሌሎች ነገሮች ላይ መዉጣት መቻል ናቸዉ፡፡

21870470_m

ጉንፋን የላይኛው የመተንፈሻ አካልን (አፍንጫን፣ጉሮሮሮንና ሳንባን) የሚያጠቃ በቫይረስ ኢንፌክሽን አማካይነት የሚመጣ የህመም አይነት ነዉ፡፡ ከአምስት አመት በታች በተለይ ደግሞ ከ 2 አመት በታች ያሉ ህፃናት፣ነፍሰጡር እናቶችና የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ የተዳከመ ሰዎች ለህመሙ በብዛት የተጋለጡ ናቸዉ፡፡

 

የህመሙ ምልክቶች

በብዛት የሚከሰቱት የህመም ምልክቶች

  • ትኩሳት
  • የጡንቻ ላይ ህመም በተለይ የጀርባ፣ እጅና እግር ላይ
  • ብርድ ብርድ ማለትና ማላብ
  • የራስ ምታት
  • ተከታታይነት ያለዉ ደረቅ ሳል
  • የአፍንጫ መጠቅጠቅና
  • የጉሮሮ መከርከር/ህመም ናቸዉ፡፡

 

እንዴት ሊተላለፍ ይችላል

ጉንፋንን የሚያመጣዉ ቫይረስ ታማሚዉ በሚያስነጥስበት፣ በሚያወራበትና በሚያስልበት ወቅት በአየር ዉስጥ በቅንጣቢ/በድሮፕሌት መልክ ይጓዛል፡፡ጤነኛዉ ሰዉ ይህን አየር ወደዉስጥ በሚስብበት/በሚተነፍስበት ወቅት ይኸንን ድሮፕሌት ወደ ዉስጥ ያስገባል፡፡

በተጨማሪም ታማሚዉ የነካቻቸዉ እቃዎች ካሉ ለምሳሌ የበር እጀታ፣ ጠረንጴዛ፣ስልክ፣ የኮምፒዩተር ፣  የመሳሰሉትን ነክቶ ጤነኛዉ ሰዉ ቢነካቸዉ እንዲሁም እጅ ለእጅ ከተጨባበጡ በኃላ ጤነኛዉ ሰዉ አይኑን፣ አፍንጫዉንና አፉን ቢነካ ቀጥታ ቫይረሱ ሊተላለፍበት ይችላል፡፡በጉንፋን ህመም የተያዙ ሰዎች ቫይረሱን የበሽታዉ ምልክቶች ከመታየታቸዉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ወይም የህመም ምልክቶቹ ከታዩበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ቫይረሱን ወደ ጤነኛዉ ሰዉ ሊያስተላልፉ ይችላሉ    (ምንም እንኳ አንዳንዴ  የህመሙ ምልክቶች መታየት ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ባሉት10 ቀናት ዉስጥ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ የሚችሉ ሰዎች ቢኖሩም)፡፡

 

ህመሙን እንዴት ማከም ይቻላል

አብዛኛዉ የጉንፋን ህመም ያላቸዉ ሰዎች የህክምና ባለሙያ ማየት ሳያስፈልጋቸዉ በቤታቸዉ ሆነዉ እራሳቸዉን ማከም ይችላሉ፡፡

 

የቤት ዉስጥ ህክምና

  • ፈሳሽ በብዛት መጠጣት (የአልኮል መጠጥን አይጨምርም)፡-

    ዉሃ፣ ጁስ/የፍራፍሬ ጭማቂና ሞቅ ያለ ሾርባ በብዛት መዉሰድ የሚከሰትብዎንየፈሳሽ እጥረት ለመከላከል ይረዳል፡፡

  • በቂ እረፍት ማድረግ፡-

    የበሽታ መከላከል አቅምዎን ለማጎልበትና ቫይረሱን መዋጋት እንዲችሉ በቂ እንቅልፍ ያግኙ፡፡

  • የህመም ማስታገሻ፡-  

    ያለሃኪም ትእዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንደ ፓራስታሞል ያሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን መዉሰድ

  • እንፋሎት መታጠን/መማግ፡- ፎጣ/ማንኛዉንም ነገር ጭንቅላትዎ ላይ በመሸፈን እየፈላ ባለ ዉሃ እንፋሎቱን መታጠን፡፡ ይህ የመቆጥቆጥና የአፍንጫ መጠቅጠቅ ስሜቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

 

Recent Posts