Author: hellodoc

የአባለዘር ህመምና ምልክቶቻቸዉ

የአባለዘር ህመም ማንኛዉም ከሰዉ ወደ ሰዉ በግብረስጋ ግንኙነት አማካይነት ሊተላለፍ የሚችል የህመም አይነት ነዉ፡፡ የአባለዘር ህመምን የሚያመጡ ከ30 በላይ የሆኑ የባክቴሪያ፣ የቫይረስና የፓራሳይት አይነቶች አሉ፡፡
እነዚህ ተዋህሲያን ሊያመጧቸዉ ከሚችሉዋቸዉ የህመም አይነቶች ዉስጥ በብዛት የሚታዩት ጨብጥ፣የክላሚዲያ ኢንፌክሽን፣ቂጥኝ፣ ትራኮሞኒያሲስ፣ ከርክር፣ የብልት ላይ ቁስለቶች(ሃርፐስ ጄኒታሊስ፣ የብልት ላይ ኪንታሮት)፣ የኤች አይ ቪ በሽታና የሄፓታይትስ ቢ(HBV) እንፌክሽን ናቸዉ፡፡
ከነዚህ ኢንፌክሽኖች ዉስጥ ኤችአይቪ፣ቂጥኝና ሄፓታይቲስ ቢ ከእናት ወደልጅ እንዲሁም በደምና የተበከሉ ነገሮች ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡

የአባለዘር ህመም ምልክቶች

የአባላዘር ህመም ምልክቶች ሁሌም ላይታዩ ይችላሉ፡፡ እርስዎ የአባለዘር ህመም ምልክቶች አሉኝ ብለዉ ካሰቡ ወይም ለአባለዘር ህመም ተጋልጠዉ ከነበረ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ይጠበቅብዎታል፡፡ አንዳንዱ የአባለዘር ህመሞች በቀላሉ የሚታከሙ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ውስብስብ ናቸዉ፡፡
ብዙዉን ጊዜ የአባለዘር ህመሞች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አያሳዩም፡፡ ምንም አይነት ምልክቶች ባይኖሩም/ባይታዩም ህመሙ ከአንዱ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ስለሆነም በግብረስጋ ግንዘኙነት ወቅት ኮንደም እንዲጠቀሙ ይመከራሉ፡፡

ክላሚዲያ

ክላሚዲያ የባክቴሪያል እንፌክሽን ሲሆን ሊያሳያቸዉ ከሚችላቸዉ ምልክቶች ዉስጥ
• ሽንት በሚሸኑበት ወቅት ህመም መኖር
• የታችኛዉ የሆድ ክፍል ላይ ህመም መኖር
• በወንዶችም ይሁን ሴቶች ላይ የብልት ፈሳሽ መታየት
• በሴቶች ላይ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም መኖር/መከሰት
• በወር አበባ ዑዳት መሃል ከብልት ደም መኖር
• በወንዶች ላይ የዘር ፍሬ ላይ ህመም ናቸዉ
የጨብጥ የህመም ምልክቶች
ጨብጥ በባክቴሪያ ምክንት የሚመጣ ሲሆን ከብልት ዉጪ በአፍ ዉስጥ፣ጉሮሮ፣ፊንጥጣ እና አይን ላይ ሊታይ ይችላል፡፡የህመሙ ምልክቶች እንፌክሽኑ ከመጣ በ10 ቀናት ዉስጥ ሊታይ ይችላል፡፡

የህመሙ ምልክቶች

• ወፈር ያለ መግል ወይም ደም የቀላቀለ ከወንድ ወይም ሴት የብልት መታየት
• ሽንት በሚሸኑበት ወቅት የማቃጠል ስሜት
• ሴቶች ላይ የወር አበባ መብዛት ወይም በወር አበባ መሃል መድማት መኖር
• በወንዶች ላይ ህመም ያለዉ የወንድ ዘር ፍሬ እብጠት
• ሰገራ ሲቀመጡ ህመም መኖር ናቸዉ፡፡
ይቀጥላል

ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ከወሊድ መከላከያ ዘዴዎች ዉስጥ የሚመደቡ ሲሆን አገልግሎታቸዉ አንዲት ሴት በድንገት ያለመከላከያ የግብረስጋ ግንኙነት ካደረገች ወይም እየወሰደች ያለዉ የወሊድ መከላከያ ዘዴ እየሰራ ካልሆነ የሚወሰድ ነዉ፡፡
ስለሆነም ይህ የወሊድ መከላከያ አንክብል እንደዋነኛ የወሊድ መከላከያ ዘዴ ሳይሆን እንደመጠባበቂያ ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ/ for backup contraception only/ የሚገለግል ነዉ፡፡ ፐላን ቢ ዋን ስቴፕ የሚባለዉ ድንገተኛ ወሊድ መከላከያ እንክብል ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊገዛ የሚችል ነዉ፡፡
ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብል የተረገዘ እርግዝናን አያቋርጥም፡፡ ነገር ግን እንደወሰዱበት የወር አበባ ዑደት ወቅት ከሚከተሉት መንገድ በአንዱ እርግዝና እንዳይፈጠር ሊያደርግ ይችላል፡፡ የእንቁላልን ከአብራኳ አኩርቶ መዉጣትን የመከላከል/የማዘግየት፣የወንድና የሴት የዘር ፍሬዎች እንዳይገናኙ መከላከል አሊያም ቢገናኙም የማህፀን ግድግዳ ላይ እንዳይጣበቁ መከላከል ናቸዉ፡፡

ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ድንገተኛ የሆነና ያለምንም ጥንቃቄ ከተደረገ የግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ የሚከሰትን እርግዝና የመከላከል ብቃት አላቸዉ፡፡ ነገር ግን ከሌሎቹ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎች ጋር ሲነፃፀሩ የመከላከል ብቃታቸዉ ስለሚያንስ በተደጋጋሚና በመደበኛነት መዉሰድ አይመከርም፡፡ እንዲያዉም ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን በትክክልም ተጠቅመዉ እረግዝናን ሳይከላከሉ ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የአባለዘር በሽታዎችን ሊከላከሉ አይችሉም፡፡

ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን ነፍሰጡር መሆንዎትን ካወቁ እንዳይወስዱ ይመከራሉ፡፡

የድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች የጎንዮሽ ጉዳቶች መድሃኒቶቹን ከወሰዱ በኃላ ለተወሰኑ ቀናቶች ሊቀጥሉ የምችል ሲሆን እነርሱም:

• ማቅለሽለሽ/ ማስታወክ
• መደበት
• የድካም ስሜት/መደካከም
• የራስ ምታት
• የጡት ህመም
• በወር አበባ ዑደት መካከል ከማህፀን ደም መፍሰስ
• የታችኛዉ የሆድ ክፍል ላይ ህመም/ቁርጠት መኖር
• የወር አበባ ዑደትዎን ማዛባት፡- የወር አበባ ዑደትዎ ከሚመጣበት ቀን ተጨማሪ ለአንድ ሳምንት መራዘም፡፡ የወር አበባ ዑደትዎ ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሉን በወሰዱ በ3ና 4 ሳምንታት ዉስጥ ካልመጣ የእርግዝና ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል/ ይመከራል፡፡
መቼ መወሰድ አለበት፡- የመከላከያ እንክብሉ የመከላከል ብቃቱ ብቁ እንዲሆን የመከላከያ እንክብሉን ግንኙነት ካደረጉ በኃላ ወዲያዉ መዉሰድ፤ ከ72 ሰዓታት ዉስጥ ግን መዉሰድ አለበት፡፡ ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብል በወር አበባ ዑደቱ በየትኛዉም ጊዜ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ዛሬ በክብደት መቀነስ ላይ ምክሮች እንሰጥዎታለን፡፡ስለክብደት መቀነስም ይሁን ስለሌላ የጤና ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 8896 ሃሎ ዶክተር ላይ በመደወል በቂ ልምድና ሙያ ያላቸዉን ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡ እርስዎን ለማማከር ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ፡፡

ክብደትን ለመቀነስ የሚረዱ ዘዴዎችና ፕሪንስፕሎች(መመሪያዎች) ተመሳይ የሆኑ ምክሮች ሲሁኑ እነሱም ጤናማ የምግብ አመጋገብ ዘዴን መከተል፣የሚመገቡትን የምግብ መጠን መወሰንና ተከታታይ የአካል እንቅስቃሴን ማዘዉተር ናቸዉ፡፡በየጊዜዉ የተወሰነ ክብደት እየቀነሱ ለመቀጠል ከፈለጉ ከዕለት ተዕለት የአኗኗር እንቅስቃሴዎት ዉስጥ ጤናማ ባህሪያትን በማካተት የአኗኗር ዘይቤዎ አካል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ክብደትን ለመቀነስ ከፈለጉ ምንም አይነት ተዓምር መጠበቅ አያስፈልግም፡፡ጤናማ አኗኗሮትን ለማጠናከርና ቀጣይንት ያለዉ ክብደትን ለመቀነስ ካሰቡ የሚከተሉት 20 ምክሮች እነሆ፡-

1. በየቀኑ ከ30 እስከ 60 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

2. በቀን ሦስት ጊዜ ጤናማ ምግብ መመገብ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ አንዱን ወይም ሌላዉን መዝለል መራብን ስለሚያመጣ መክሰስን በብዛት እንዲመገቡ ያደርገዎታል፡፡ ስለዚህ ይህን ከማድረግ መቆጠብ

3. አትክልትና ፍራፍሬ ምግቦችን ማዘዉተር

4. በየጊዜዉ የክብደት ክትትል ማድረግ/መለካት

5. በቀላሉ የሚገኙ ጣፋጭ ምግቦችን በቤት ዉስጥ ያለማስቀመጥ

6. ከቤተሰብ ጋር ሊደረጉ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ማከናወን

7. ጤናማ ምግቦችን በመጀመሪያ መመገብ፡- ለምሳሌ ፓስታና ሰላጣ መመገብ ቢገባዎ አስቀድመዉ ሰላጣዉን በመመገብ የመጥገብ ስሜትዎን ያምጡ

8. ለሚመገቡት ምግብ መጠን ትኩረት መስጠት

9. እንቅስቃሴ ሊፈጥሩ ለሚችሉ ነገሮች እድል መፍጠር

10. ከቤተሰብ ጋር አብረዉ መመገብ ጥሩ ነዉ፡፡ነገር ግን ቴሌቪዥን እያዩ መመገብ ምን ያህልና ምን እየተመገቡ እንደሆነ ለመገመት ስለሚያስቸግርዎ ጥንቃቄ ያድረጉ፡፡

11. እየተመገቡ ያሉትን ምግብ ማወቅ

12. እንቅስቃሴዎትን ማቀያየር

13. ጭንቀትን መቀነስ

14. የቤት ምግብን መመገብ

15. ጤናማ መክሰስ መመገብ

16. ቀኑን ብዙ ፋይበር ባላቸዉ ምግቦች በመመገብ ይጀምሩ

17. በምሳ ሰዓት ለ10 ደቂቃዎች ወክ ማድረግ

18. ለሳምንቱ የሚጠቀሙበትን የምግብ ፕሮግራግራም/መርሃ ግብር አስቀድሞ ማዉጣት

19. ምግብ ሲያምሮት/የምግብ መጓጓት ካለዎት ሀሳብዎትን ለመርሳት በሌላ ነገር መጠመድ

20. እራስን መሸለም/ማበረታታት

እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚቻል ያዉቃሉ? ወይንስ ደስታ እራሱ ፈልጎ እስኪያገኝዎ ድረስ እየጠበቁት ነዉ? እርስዎ ዘንድ እስኪመጣ ድረስ ጠብቀዉ.. ጠብቀዉ ..ና እስኪመጣ መጠበቅ ሰልችተዎታል? እንግዲያዉስ እርስዎ ዘንድ እስኪመጣ መጠበቁን ይተዉትና ደስታን እርስዎ እራስዎ መፈለግ ይጀምሩ፡፡

በተረት እንደሚባለዉ ደስታ በምትሃት ወይም በአንዳች ነገር የሚመጣ አይደለም፡፡ እንዲያዉም ድንገት እርስዎ ላይ የሚከሰት ክስተትም አይደለም፡፡ እርስዎ እራስዎ የሚያዳብሩት/የሚያሳድጉት ባህሪ ነዉ እንጂ፡፡ ጉዳዩ ይህ ከሆነ ምን እየጠበቁ ነዉ ታዲያ? እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ /ምን ደስተኛ እንደሚያደርግዎ መፈለግ ይጀምሩ እነጂ! ስለዚህ ደስተኛ/በተቻለ መጠን ደስተኛ ለመሆን እራስን በማለማመድ ደስታን ማግኘት ይቻላል ማለት ነዉ፡፡

እንዴት ደስታኛ መሆን እንደሚቻል ሳይንስ ምን ይላል?
10 በመቶ ብቻ በሚሆኑ በሰዎች መካከል ያለዉ የደስተኝነት አገላለፅ ልዩነት በሁነቶች መለያየት ሊገለፅ ይችላል፡፡ በተረፈ በአብዛኛዉ ሰዎች ላይ ደስተኝነትን የሚወስኑት የሰዎች ስብዕና ሲሆን በተለይ ሊለወጡ የሚችሉ አስተሳሰብና ባህሪይ ናቸዉ፡፡

ምንም እንኳን እርስዎም ብዙ ሰዎች እንደሚያስቡት ደስተኛ መሆን የሚቻለዉ ሀብታም ሆነዉ ሲወለዱ፣ ቆንጆ ሲኮን አሊያም ጭንቀት የሌለበት ኑሮ/ህይወት ሲኖሩ ነዉ የሚል አስተሳሰብ ከሆነ ያልዎት እዉነቱ እንደሱ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ሀብት ያላቸዉ ሰዎች፣ቁንጅና ያላቸዉ ወይም ጭንቀት የሌለዉ ኑሮ የሚኖሩ ሰዎች በአቬሬጅ ሲታይ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ካልታደሉ ሰዎች ጋር ሲዋዳደሩ ምንም የተለየ/የበለጠ ደስታ የሌላቸዉ መሆኑ ነዉ፡፡

ደስተኛ የሆኑ ሰዎች ደስተኛ ያደረጋቸዉን ነገር የህይወት/የኑሮ ምርጫቸዉ የድምር ዉጤት እንደሆነ የሚረዱ ሲሆን አኗኗራቸዉ በሚከተሉት ድጋፎች ላይ የተመሰረቱ ነዉ፡፡

• ለቤተሰቦቻቸዉና ጓደኞቻቸዉ ጊዜ የሚሰጡ
• ባላቸዉ ነገር የሚደሰቱ/የሚረኩ
• ቀና አመለካከት/አስተሳሰብ ያላቸዉ
• የሚኖሩት ለአላማ እንደሆነ አይንት ስሜት የሚፈጥሩና
• ዛሬን መኖር (Living in the moment) የሚሉት ናቸዉ፡፡


ስለሆነም ደስተኛ ለመሆን፡- መለማመድ፣መለማመድ፣መለማመድ

 

ደስተኛ ለመሆን እየፈለጉ ከሆነ መለካሙ ዜና ምን እንደሆነ ያዉቃሉ? የደስታዎ መጠን የሚወሰነዉ በምርጫዎ፣ ሀሳብዎና በተግባርዎ ላይ ነዉ፡፡ ምንም እንኳ ቀላል ባይሆንም የደስተኝነትዎን መጠን በተወሰነ መልኩ ከፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህ ለማድረግ የሚከተሉት መንገዶች ሊከተሉ ይችላሉ፡፡

• ከሰዎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር መጣር፡- ደስተኛ
• በኑሮዎ ዉስጥ ምስጋና መልመድ( Express gratitude)
• ለነገሮች ቀና አመለካከት/በጎ በጎ ጎኑን የማየት ባህርይ ማዳበር
• አላማዎ ምን እንደሆነ ማወቅ
• ዛሬን መኖር

የስኳር ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ዉስጥ ዛሬም ቢጀምሩት ዘገዩ የማይባሉበት የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡

በብዛት ከሚከሰቱ የስኳር አይነቶች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ ተይፕ (2) መከላከል ትልቅ ነገር ነዉ፡፡ እርስዎ ለስኳር ህመም ተጋላጭ ከሆኑ ለምሳሌ የሰነት ክብደትዎ ከፍተኛ ከሆነ ወይም በቤተሰብዎ ዉስጥ የስኳር ህመም ያለበት ሰዉ ካለ የስኳር ህመምን መከላከል ቅድሚያ መስጠት ይገባዎታል፡፡

የስኳር ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ/ከሚመከሩ መንገዶች ዉስጥ ዋናዋናዎቹ

  1. በቂ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡
    ተከታታይነት ያለዉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሰዉነትን ክብደት ለመከነስ፣ የደም የስኳር መጠንን ለመቀነስና ለኢንሱሊን ሆርሞን የመስራት አቅም መጨመር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ከሚመከሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ኤሮቢክስና የሬሲስታንስ ትሬንግ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡
  2. የፋይበር/የቃጫነት ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር፡- ይህን ማድረግ በደምዎ ዉስጥ ያለዉን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለህመሙ ተጋላጭነትዎን እንዲቀንስ ያደርጋል፤ለልብ ህመም ተጋላጭነዎን ይቀንሳል፤ የሰዉነት ክብደትዎን ለመቀነስ እገዛ ያደርጋል፡፡ ከፍተኛ የፋይበር መጠን ካለቸዉ ምግቦች ዉስጥ የሚመደቡት አትክልትና ፍራፍሬ፣ባቄላ፣ጥራጥረዎችና ኦቾሎኒ  ናቸዉ፡፡
  3. ጥራጥሬዎች/ሆል ግሬይንስ መጠቀም: ምንም እንኳ በምን ዘዴ እንደሆነ ባይታወቅም ጥራጥሬ ምግቦችን ማዘዉተር የደም የስኳር መጠንን በመቆጣጠር የስኳር ህመም ተጋላጭነትዎን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ከነዚሀ ምግቦች ዉስጥ የሚመደቡት የተለያዩ ዳቦዎች፣ፓስታና ጥራጥሬዎች ናቸዉ፡፡
  1. ክብደት መቀነስ፡- የሰዉነት ክብደትዎ ከፍተኛ ከሆነ ክብደትዎን መቀነስ የስኳር ህመምን ለመከላከል ትልወቁን ቦታ ይወሰወዳል፡፡ የሚቀንሱት እያንዳንዷ ኪሎ የጤንነትዎ ሁኔታ እንዲሻሻል የማድረግ አቅም አለዉ፡፡ በጥናት እንደታየዉ የሰዉነታቸዉን ክብደት በፊት ከነበረዉ በ7 በመቶ የቀነሱና ተከታታይነት ያለዉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የስኳር እመም ተጋላጭነትን እስከ 60 በመቶ ድረስ የመቀነስ አቅም አለዉ፡፡
  2. ጥናማ አመጋገብን መከተል፡- የስኳር ይዘታቸዉ መጠነኛ የሁኑ ምግቦችን እንዲሁም ጤናማ አመጋገብ ዘዴን በመከተል የስኳር መጠንን መቀነስ ይቻላል፡፡

ሪህ(ጋዉት) የሚባለዉ ህመም በደም ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ዩሬት ክሪስታልስ በመገጣጠሚያ አካባቢዎች እንዲጠራቀም በማድረግ መገጣጠሚያዎቹ ላይ ህመም እንዲከሰት የሚያደርግ የህመም አይነት ነዉ፡፡

ስለሆነም ለሪህ ህመም የሚስማማዉን የአመጋገብ ዘዴዎችን መከተል በደም ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠንን መቀነስ ያስችላል፡፡ ምግቦቹ ህመሙን ለማዳን ባይረዱም ህመሙ በተደጋጋሚ እንዳይከሰትና በህመሙ ምክንት የሚከሰተዉን የመገጣጠሚያ ላይ ጉዳት ለመቀነስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ህመሙን እንዲሁም በደም ዉስጥ ያለዉን የዩሪክ አሲድ መጠን ለመቀነስ መድሃኒቶችን መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡

የአመጋገቡ ዝርዝር፡   

በአጠቃላይ የአመጋገብ መርሆዉ ከተመጣጠ አመጋገብ ስርዓት ጋር የሚመሳሰል ነዉ፡፡

  • ክብደት መቀነስ፡- ክብደትዎ ሲጨምር የሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን የሚጨምር ሲሆን ክብደትዎን መቀነስ ግን ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎ እንዲቀንስ ይረዳል፡፡
  • ኮምፕሌክስ ካርቦሃይድሬትስ/ኃይል ሰጪ ምግቦቸ፡- አታክልት፣ ፍራፍሬና ጥራጥሬ ምግቦችን ማዘዉተር፡፡ እንደ ነጭ ዳቦ፣ኬክ፣ ከረሜላ ፣ ስኳርነት ያላቸዉን መጠጦችን/ፈሳሾችን መተዉ/አለመመገብ ይመከራል፡፡
  • ዉሃ፡- በቀን ዉስጥዉሃን አብዝቶ መጠጣት ለሪህ ህመም መቀነስ ጋር ተያያዥነት አለዉ፡፡ ስለሆነም በቀን ዉስጥ ከ8 እስከ 16  ብርጭቆ ፈሳሽ  እንዲጠጡ ከዚያ ዉስጥ ግማሹ ዉሃ ቢሆን ይመከራል፡፡
  • ስብ፡- ስብነት/ ጮማነት የበዛበት የእንስሳትም ይሁን የዶሮ እንዲሁም የወተተት ተዋፅኦዎችን አለመመገብ/መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
  • ፕሮቲን፡- ከቀይ ስጋ፣ አሳና ከወተት ተዋፅኦ የሚገኘዉን የፕሮቲን መጠን መጥኖ መመገብ (ከ113 እስከ 170 ግራም)፡፡ የሚመገቡት ምግብ ዉስጥ የስብነት ይዘታቸዉ አነስተኛ ወይም ምንም የሌላቸዉ እርጎ ወይም የስብነት መጠኑ የቀነሱ መተቶች/ skim milk/መጠቀም፡፡

 

ለተወሰኑ ምግቦች ወይም ምግብ ዉስጥ ለሚጨመሩ ነገሮች የሚመከሩ

  • ከፍተኛ ፕዩሪን ያላቸዉ አታክልቶች/ High-purine vegetables:- ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከፍተኛ ፕዩሪን ያላቸዉ እንደ ቆስጣ፣የአበባ ጎመንና መሽሩም ያሉ ምግቦችን መመገብ የሪህ ህመም ተጋላጭነትንና መከሰትን አይጨምሩም/አያመጡም ፡፡ በተጨማሪም ባቄላ ወይም የአበባ እህሎች መካከለኛ የፒዩሪን መጠን ግን ጥሩ የፕሮቲን ምንጮች ስለሆኑ መመገብ ይችላሉ፡፡
  • ከአካላት/ኦርጋን ወይም ግላንዲዉላር ስጋ/፡- ከፍተኛ ፕዩሪን ያላቸዉና የደምን የዩሪክ አሲድ መጠን የሚጨምሩ እንደ ጉበት፣ኩላሊት፣ጣፊያና የበግ አንጎል የመሳሰሉ ምግቦችን ያለመመገብ
  • መጠጥ/አልኮሆል፡- አልኮሆል የዩሪክ አሲድ መመረትን ይጨምራል፤የሰዉነትን የፈሳሽ ምጣኔን ያዛባል፡፡ ስለሆነም አልኮሆል ያለመጠጣት፡፡ ለምሳሌ ቢራ ለሪህ ህመም በተደጋጋሚ መከሰት ምክንት ሊሆን ይችላል፡፡
  • ቡና፡- አንዳንድ ጥናቶች እንዳሳዩት ቡናን በመጠኑ መጠጣት የሪህ ህመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ያሳያል፡፡ ነገር ግን ቡና ሲጠጡ ከሌሎች ህመሞች ጋር ያለዉን ሁኔታ አመዘዝነዉ መሆን አለበት
  • የተወሰኑ የባህር ምግቦች፡- እንደ ሰርዲንና ቱና ያሉ ምግቦችን ያለመመገብ
  • ፕሪም፡- ፕሪም መመገብ ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን እንደሚቀንሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ጤናማ እርግዝና፡-

ነፍሰጡር መሆንዎን ሲያዉቁ ስለእርግዝናዎ በየሳምንቱ እቅድ ማዉጣት ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ከእርግዝናዎ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ምን አይነት ምግብ መዉሰድ እንዳለብዎና እንደሌለብዎ፣ስለየአካል እንቅስቃሴና የግብረስጋ ግንኙነትም ሆነ ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

የመጀመሪያዉ የእርግዝና ክፍለ ጊዜ (First trimester) ፡-

ይህ የመጀመሪያዎቹን 14 ሳምንታት የእርግዝና ወቅቶች የያዘ ሲሆን በእርስዎና በፅንሱ ላይ ፈጣን የሆኑ ለዉጦች የሚታዩበት ወቅት ነዉ፡፡በዚህ ጊዜ

በእርስዎ ላይ፡- የጡት ላይ ህመም፣ድካም፤ ማቅለሽለሽ ያሉ አካላዊ ለዉጦችና ከደስታ እስከ መጨናነቅ ሊደርሱ የሚችሉ የስሜት መለዋወጦች ሊታዩ ይችላሉ፡፡

• በፅንሱ ላይ፡- ይህ ክፈለ ጊዜ ፅንሱ በፍጥነት የሚያድግበትና የሚጎለብትበት ወቅት ነዉ፡፡የፅንሱ አእምሮ፣ህብለሰረሰርና ሌሎች አካላቶች ይፈጠራሉ፤ እንዲሁም የፅንሱ ልብ መምታት ትጀምራለች፡፡

ስለሆነም በመጀመሪያዉ የእርግዝና ክፍለጊዜዎ የቅድመወሊድ ክትትል ለመጀመር የህክምና ባለሙያዎ ጋር መሄድ ይገባዎታል፡፡ በክትትልዎ ወቅት ምን ነገሮችን በዚህ ወቅትና ለወደፊቱ መተግበር እንደሚገባዎ ለመረዳት ይረዳዎታል፡፡


ሁለተኛዉ የእርግዝና ክፍለጊዜ፡-

ይህ ከ14ኛዉ እስከ 28ኛዉ ሳምንት ያለዉ የእርግዝናዎ ወቅት ሲሆን በዚህ ጊዜ ከመጀመሪያዉ የእርግዝና ክፍለጊዜ ይልቅ መልካም ጤንነት ስለሚሰማዎ እርግዝናዎን የሚያጣጥሙበት ወቅት ነዉ፡፡

በእርስዎ ላይ የሚታይ፡-እርግዝናዎ በደንብ የሚያስታዉቅበት ጊዜ ሲሆን የጡት መጠን መጨመር የሆድ መግፋትና የቆዳ ላይ ለዉጦች የሚታዩበት ጊዜ ነዉ፡

• በፅንሱ ላይ፡- 20ኛዉ ሳምንት የእርግዝናዎ እኩሌታ ሲሆን በዚህ የእርግዝና ክፍለጊዜ ፅንሱ መገለባበጥና መስማት ይችላል፡፡


ሶስተኛዉ የህክምና ክፍለጊዜ፡-

ይህ የመጨረሻዉ የህክምና ክፍለጊዜ ከ28ኛዉ እስከ 40ኛዉ ሳምንታት ድረስ ያለዉ ሲሆን ፈታኝ የሆኑ አካላዊና ስነልቦናዊ ጫናዎች የሚታዩበት ነዉ፡፡ በዚህን ጊዜ የጀርባ ህመም፣የእግር እብጠት መጨናነቅ ሊመጣ ይችላል፡፡

• በፅንሱ ላይ፡- አይኑን መክፈትና መዝጋት ይችላል፤ክብደት ይጨምራል፡፡ ፈጣን የሆነ እድገት ስላለዉ እንቅስቃሴ እንዲጨምር ሊያደርገዉ ይችላል፡፡ 39ኛዉን ሳምንት ላይ ልጁ ሙሉ በሙሉ ያደገ ነዉ፡፡

• በእርስዎ ላይ፡-በዚህ የእርግዝና ክፍለጊዜ በመደበኛ ሁኔታ ክትትልዎን መቀጠል፡፡ የህክምና ባለሙያዎ የፅንሱን አቀማመጥ፣የማህፀን አንገት ለዉጦችንንና የመሳሰሉትን ይመረምራሉ፡፡ እርስዎም የመዉለጃ ወቅትዎ እየተቃረበ ስለሆነ መጠየቅ ያለብዎን ሁሉ መጠየቅ ይገባዎታል፡፡

እርስዎ በቤቶ ሊተገብሩት የሚችሉ ምክሮች

• ሞቅ ባለ ዉሀ አፍዎትን መጉመጥምጥ
• በጥርስ መጎርጎሪያ በጥርስዎት መካካል የቀሩ የምግብ ትራፊዎችን ማዉጣት
• ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት መዉሰድ


ወደ ጥርስ ህክማና መስጫ ማዕከል መሄድ


• የእንፌክሽን ምልክቶች ካለዎት ለምሳሌ እብጠት ካለ፤ ምግብ ሲመገቡ ህመም ካለ፤ የድድ መቅላት ወይም ሽታ ያለዉ ፈሳሽ ካለዎት ሀኪም ያማክሩ
• ህመሙ ከአንድ ቀንና ከዚያ በላይ ከቀጠለ
• ከጥርስ ህመሙ ጋር ትኩሳት ካለዎት
• በአተነፋፈስዎ ላይ ወይም ምግብ ሲዉጡ ከተቸገሩ

አንዳንድ ህመሞች ያለግብረስጋ ግንኙነት ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡

 

1.  ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ፡-

ይህ ቫይረስ በቆዳ ለቆዳ ንኪኪ ኣማካይነት ሊተላለፍ የሚችል ሲሆን በእርግዝናና ወሊድና በጡት ማጥባት  ወቅት ከእናት ወደ ልጅ፣በግብረስጋ ግኑነት ወቅት የአካል ንኪኪ በሚኖርበት ሊተላለፍ ይችላል፡፡ይህ ቫይረስ የብልት አካባቢ ቁስለት/ዋርትና ቅድመካንሰር ችግሮችን ያመጣል፡፡

 

2.  ሞሊዩስከም ኮንታጅዮሰም፡-

ይህ ቀይ፣ ህመም የሌለዉ፣ መሃሉ ክፍት የሆነ  ትንንሽ የቆዳ ላይ ችግሮች ከሰዉ ወደ ሰዉ በቆዳ ለቆዳ ንኪኪ(በመጨባበጥ፣በመተቃቀፍ) የሚተላለፉ ናቸዉ፡፡ሞሊዩስከም በራሱ ሰዓት ሊድን የሚችል ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መድሃኒት መዉሰድ ይቻላል፡፡

 

3.  ሀርፐስ፡-

ሀርፐስ በመሳሳም፣ህመምተኛዉ የተጠቀመበትን የመመገቢያ እቃዎችን በመጠቀምና እንዲሁም በመላጫ እቃዎች ሊዛመት ይችላል፡፡ሁለት አይነት ሀርፐስ ቫይረሶች አሉ-ሀርፐስ ታይፕ 1 እና ታይፕ 2.

ሄፓታይትስ ሲ የጉበት ህመምን ከሚያመጡ የጉበት ቫይረስ አይነቶች አንዱ ሲሆን በጉበት ላይ በአጭር ጊዜ ምልክት የሚያሳይ ወይም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጉበት ላይ እንፌክሽን እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ የሚከሰተዉ ህመም አጭር ጊዜ/ለሳምንታት ከሚቆይ መጠነኛ ደረጃ እሰከ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅና በጉበት ለይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ህመም ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡ እስከአሁን ድረስ በአለማችን ሄፓታይትስ ሲን የሚከላከል ክትባት የሌለ ሲሆን ጥናቶች ግን እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በሄፓታይትስ ሲ ቫይረተስ ከተጠቁ ሰዎች ዉስጥ ከ15 እስከ 45 በመቶ የሚሆኑት ቫይረሱን በ6 ወራት ዉስጥ ከሰዉነታቸዉ  ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ የሚጠፋ/የሚድን ሲሆን ከ 55-85 በመቶ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ግን ቫይረሱ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጉበት ላይ እንፌክሽን/ chronic HCV infection/ እንዲከሰት ያደርጋል፡፡

 

መተላለፊያ መንገዶች

·         አደንዛዥ እፅ የሚጠቀሙ ሰዎች የሚወጉበትን መርፌ በጋራ ሲጠቀሙ

·         ያልተመረመረ የደምና የደም ተዋፅኦን መዉሰድ

·         በመጠነኛ ደረጃ ቢሆንም በግብረ ስጋ ግነኙነትና ከእናት ወደ ልጅ ይተላለፋል፡፡

 

የማይተላለፍባቸዉ መንገዶች፡-

በጡት ወተት፣በምግብ፣ በዉሃና በማህበራዊ መስተጋብር ግንኙነቶች ( መተቃቀፍ፣ መሳሳምና ምግብ አብሮ በመብላት)

 

የህመሙ ምልክቶች

እንፌክሽኑ ከተከሰተ በኃላ እስከ 80 በመቶ የሚደርሱ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክት ላይኖራቸዉ ይችላል፡፡ የህመም ምልክቶች ከተከሰቱ ደግሞ እንደ ትኩሳት፣፣ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣የሆድ ህመም፣ የሽንት ወደ ኮካኮላነት መልክ መቀየር፣የመገጣጠሚያ ላይ ህመምና የአይንና የቆዳ ወደ ቢጫነት መቀየር ናቸዉ፡፡

 

ምርመራዎች

ምርመራን በጊዜዉ/በወቅቱ ማድረግ በእንፌክሽኑ ምክንያት ሊደርሱ የሚችሉ የጤና ችግሮችንና የህመሙን ከአንዱ ወደ ሌላዉ የመተላለፍ እድልን መቀነስ ይቻላል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት ለህመሙ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡ እነርሱም

·         አደንዛዥ እፅ የሚወጉ ሰዎች

·         የደምና የደም ተዋፅኦዎችን የሚወስዱ ሰዎች

·         በሄታይትስ ሲ ከተያዘች እናት የሚወለዱ ህፃናት

·         የፍቅር/የትዳር ጓደኛቸዉ ሄፓታይትስ ሲ የተያዙ ሰዎች

·         የኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸዉ ያለ ሰዎች

·         ከዚህ በፊት ንቅሳት የተደረገላቸዉ/የነበራቸዉ ሰዎች ናቸዉ፡፡

 

ሊደረግ የሚችል ህክምና

የሄፓታይትስ ሲ እንፌክሽን አለማለት ሁሌ ህክምና ያስፈልገዋል ማለት አይደለም፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የበሽታ መከላከል ስርዓታቸዉ እንፌክሽኑን ከሰዉነታች በራሱ ጊዜ እንዲድን/እንዲጠፋ ሊደርግ ይችላል፡፡ በሌሎች አንዳንድ ሰዎች ላይ  ደግሞ ምንም እንኳ ለረጅም ጊዜ የቆየ የጉበት ላይ እንፌክሽን ቢኖራቸዉም ጉበት ላይ የከፋ ጉዳት ላይከሰት ይችላል፡፡ ህመሙ ለመዳን ብዙ የሚወስኑት ነገሮች ቢኖሩም የቫይረሱ ስትሬይን (አይነትና) የሚሰጠዉ የህክምና አይነት ግን ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡