Author: hellodoc

አንዲት ሴት ያለምንም ችግር ምን ያህል ጊዜ በኦፕራሲዮን ልትወልድ ትችላለች?

 

በተደጋጋሚ የሚሰራዉ /የሚደረገዉ ኦፕራሲዮን ከበፊቱ ይልቅ የሚኖረዉ ጉዳት ከፍ እያለ ይመጣል ፡፡ ምንም እንኳ ጥናቶች አንዲት እናት ያለምንም ችግር ምን ያህል ጊዜ በኦፕራሲዮን መዉለድ እንደምትችል በዉል ባያረጋግጡም/ባያስቀምጡም ከሶስትኛ ጊዜ በኃላ የሚደረግ ኦፕራሲዮን የሚያደርሰዉ/የሚያመጣዉ ጉዳት እየከፋ እንደሚመጣ በትትክል ተዘግቧ፡፡

በተደጋጋሚ ኦፕራሲዮን የሚደረጉ እናቶች ለሚከተሉት ነገሮች ሊጋለጡ ይችላሉ፡-

 

• ጠባሳ በማህፀናቸዉና አከባቢዉ ላይ ባሉ አካላት ላይ መከሰት፡- ምንም እንኳ ደረጃቸዉ ቢለያይም በማህፀንና በአካባቢዉ ባሉ አካላት ላይ መጣበቅ ሊፈጠር ይችላል፡፡

 

• የአንጀትና የሽንት ፊኛ ላይ ከኦፕራሲዮን ጋር የተያያዘ አደጋዎች መድረስ፡- የሽንት ፊኛ ላይ አደጋ በመጀመሪያዉ ኦፕራሲዮን ወቅት የመድረስ አጋጣሚዉ ቢኖርም የተለመደ ግን አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህ አደጋ በሚቀጥሉት ኦፕራሲዮኖች ላይ በፊት በተደረገዉ ኦፕራሲዮን ምክንያት ከማህፀንና ከሌሎች አካላት ጋር ሲድን ስለሚጣበቅ ለአደጋ የመጋለጡ እድል እየጨመረ ይመጣል፡፡ ይህ አንጀትም በበፊቱ ኦፕራሲዮን ምክንያት ከማህፀን ጋር ስለሚጣበቅ አደጋ እንዲከሰት ያደርጋል

 

• መጠኑ ከፍ ያለ የብልት መድማት መከሰት፡- ከማንኛዉም ኦፕራሲዮን በኃላ የመድማት እድሉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡ ነገር ግን የሚደረገዉ የኦፕራሲዮን ቁጥር እየጨመረ በመጣ ሰዓት ብዙ የመድማቱ እድል እየጨመረ ይመጣል፡፡ የሚደረጉት ኦፕራሲየኖች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ የእናትየዋን ህይወት ለመታደግና መድማቱን ለመቆጣጠር ማህፀን ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ የማድረጉ እድልም እየጨመረ ይመጣል፡፡

 

• ከእንግዴ ልጅ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ችግር፡- የሚሰራልዎ የኦፕረሰሲዮን ቁጥር በጨመረ በመጣ ቁጥር ከእንግዴ ልጅ ጋር ተያይዞ ሊደርስ የሚችለዉ ችግር እየጨመረ ይመጣል፡፡ ይህም የእንግዴ ልጁ ወደ ማህፀንዎ ግድግዳ ከመጠን ባለፈ ሁኔታ መጣበቅ(ፕላሴንታ አክሬታ) አሊያም በትክክለኛዉ ቦታ ያለመቀመጥ(ለምሳሌ የማህፀን አንገትን መሸፈን–ፕላሴንታ ፕሬቪያ) ሊሆን ይችላል፡፡

 

ሁለቱም ማለትም በማህፀንም(አምጦ መዉለድም) ይሁን በኦፕራሲዮን መዉለድ የየራሳቸዉ ጉዳትና ጥቅም አላቸዉ፡፡ ከኦፕራሲዮን በኃላ በሚቀጥሉት ጊዜ በየትኛዉ መንገድ መዉለድ እንዳለብዎ መወሰን የተወሳሰበ ነዉ፡፡ ስለሆነም ከህክምና ባለሙያዎ ጋር ስለቀጣይ የመዉለጃዉ መንገድና ቀጣይ ቢያረግዙ ሊኖሩ ስለሚችለዉ ችግር እንዲወያዩ ይመከራሉ፡፡

አስም/Asthma

 

አስም የአየር ቧንቧ እንዲጠብ፣አንዲያብጥና ተጨማሪ አክታ እንዲፈጥር የሚያደርግ የህመም አይነት ነዉ፡፡ ይህ የአየር ቧንቧ ጥበት ሂደት አተነፋፈስ ላይ ችግር እንዲፈጠር በማድረግ ሳል፣ ሲር ሲር የሚሉ ድምፆችና የትንፋሽ መቆራረጥ እንዲመጣ/እንዲከሰት ያደርጋል፡፡

የህመሙ ምልክቶች

 

የህመሙ ምልክቶች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊድረስ የሚችል ሲሆን ከሰዉ ሰዉ ይለያያል፡፡ህመሙ አንዳንዴ ብቻ ሊከሰት ይችላል፡፡ሌሎች ላይ ደግሞ ሁል ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡የህመሙ ምልክቶች

• የትንፋሽ ማጠር
• ደረትን ወጥሮ መያዝ/የደረት ላይ ህመም
• በትንፋሽ ማጠር ምክንያት፣ በሳልና ሲር ሲር በሚል ምክንያት እንቅልፍ ማጣት
• ወደዉጪ በሚተነፍሱበት ወቅት ሲር ሲር የሚል ድምፅ መኖር
• ጉንፋን በሚይዝዎት ወቅት ሊባባስ የሚችል ሳል ወይም ሲርሲር የሚል ድምፅ መከሰት

 

የአስም ህመምዎ መባባሱን የሚያሳዩ ምልክቶች፡

 

• የአስም ህመም ምልክቶች ተደጋግሞ መከሰትና የሚያስጨንቅዎ ከሆነ
• የአተነፋፈስ ችግርዎ እየጨመረ መምጣት
• የአስም ህመምዎን በፍጥነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ መድሃኒቶችን በተደጋጋሚ መዉሰድ ካለ

 

አስምን ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮች

 

• የአየር ዉስጥ አለርጂዎች፡- የአበባ ሽታ( ፖለን)፣ሻጋታ፣ የበረሮ ሽታ፣ አቧራ
• እንደ ጉንፋን ያሉ የመተንፈሻ አካል አንፌክሸኖች መኖር
• የአካል እነቅስቃሴ ካደረጉ በኃላ የሚመጣ
• ቀዝቃዛ አየር
• የአየር መበከል፤ለምሳሌ በጭስ
• መድሃኒቶች፡- ቤታ ብሎከርስ፣አስፕሪን፣አይቡፕሮፌን
• የስሜት መለዋወጥ፣ ጭንቀት
• የቃር ህመም
• በተወሰኑ ሴቶች ላይ በወር አበባ ዑደት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡

ለአስም የሚያጋልጡ ነገሮች

አስም እንዲከሰት የሚደርጉ የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡እነዚህም
• በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ካለ
• ሌሎች የአለርጂ ህመሞች ካለዎ(የቆዳ፣የሳይነስ)
• ክብደት መጨመር
• የሚያጨሱ ከሆነ
• ሌላ የሚያጨስ ሰዉ ካለ(የሲጋራ ጭስ መማግ)
• ለአየር ብክለት መጋለጥ
• እንደ እርሻ፣ የፀገር ስራና ከፋብሪካ ጋር የተገናኙ ኬሜካሎች ከስራቹ ሁኔታ የተነሳ የተጋለጡ ሰዎች
• ለአለርጂዎች፣ለተወሰኑ የበሽታ አምጪ ጀርሞች የተጋለጡ ሰዎችም ለህመሙ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

 

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መች ነዉ?

ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ አስም ለህይወት አስጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የህመምዎ ምልክቶች እየተባባሱ ከመጡ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ የሚከተሉት ምልክቶች ካለዎ የህክምና ባለሙያዎን በፍጥነት ያማክሩ፡፡
• የትንፋሽ ማጠር ወይም ሲር ሲር የሚለዉ ድምጽ በፍጥነት ከተባባሰ
• እንደ አልቡቴሮል ያሉ ለድንገተኛ ጊዜ የሚሆኑ መድሃኒቶችን ወስደዉ የማይሻሻል ከሆነ
• መጠነኛ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት የትንፋሽ ማጠር የሚከሰት ከሆነ

 

አስም እንዴት ሊመጣ ይችላል

ለምን የተወሰኑ ሰዎች አስም እንደሚያዙና ሌሎች ደግሞ ለምን እንደማይያዙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ አስም የአካባቢያዊና ከዘር ጋር በተገናኘ ሊከሰት የሚችል የህመም አይነት ነዉ ተብሎ ይገመታል፡፡

 

የአስም ህክምና

አስም በህክምና ሊድን አይችልም፡፡ ነገር ግን የህመም ምልክቶቹን ልንቆጣጠራቸዉ እንችላለን፡፡ አስም በጊዜ ሂደት ብዙዉን ጊዜ ሊለዋወጥ ስለሚችል ከህክምና ባለሙያዎ ጋር በመመካከር መድሃኒትዎን እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡

አስምን ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮችን መከላከል፡-አስምን ሊያስነሱ/ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮች መቀነስ አስምን ለመቆጣጠር ከሚረዱ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ከነዚህም ዉስጥ

• ቅዝቃዜ በሚኖርበት ወቅት አፍና አፍንጫን መሸፈን
• ሻጋታን ማስወገድ፡- የሻጋታ ቡናኝን ለመከላከል በሻወር ቦታ፤በኩሽናና በመኖሪያ ቤትዎ አካባቢ ያሉ ሻጋታዎችን ማስወገድ
• ከቡናኝ መከላከል
• በመደበኛ ሁኔታ የመኖሪያ ቤትዎን ማፅዳት
• መደበኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

መጥፎ የእግር ጠረን

በአብዛኛዉ ጊዜ መጥፎ የእግር ሽታ የሚያመጡ ነገሮች በቀላሉ ሊታከሙ/ሊወገዱ የሚችሉ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ላይ የእግር ሽታዉ በቀላሉ የማይጠፋና ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል የህክምና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያዉ የሽታዉን መንስኤ ካረጋገጠ በኃላ አስፈላጊዉን ህክምና እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

መጥፎ የእግር ጠረን መንስኤዎች

ባክቴሪያ:-

ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚደርሱ መጥፎ የእግር ሽታ እንዲከሰት የሚያደርጉት በስኒከር መጫሚያዎች ዉስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ናቸዉ፡፡ ባክቴሪያዎቹ የሞቱ የቆዳ ሴሎችን የሚመገቡ ሲሆን እርጥበታማና ላብ እንዲከሰት የሚያደርጉ የእግር ጫማዎች ባክቴሪያዎቹን የመሳብና ምቹ መራቢያ ቦታዎች ይፈጥርላቸዋል፡፡

እነዚህ ባክቴሪያዎች ኦርጋኒክ አሲድና ሰልፈር ዉሁድ ስለሚያመርቱ እግር የተበላሸ እንቁላል ጠረን እንዲኖረዉ  ያደርጋሉ፡፡

ፈንገስ እንፌክሽን፡-

መጥፎ የእገር  ሽታ በብዛት ከሚያመጡ መንስኤዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ የፈንገስ እንፌክሽን ሲሆን ፈንገስ በተጨማሪም በእግር መርገጫ/ተረከዝ ቆዳ ላይ የመድረቅና በእግር ጣቶች መሃል የቆዳ መላላጥ እንዲመጣም ያደርጋል፡፡ይህ አትሌትስ ፉት ወይም ቲንያ ፔዲስ ይባላል፡፡ ቲንያ ፔዲስ ከሰዉ ወደ ሰዉ የሚተላለፍ ሲሆን በእርጥበት አዘል አካባቢዎች ለምሳሌ የልብስ መቀየሪያ ስፍራዎች( ፈንገሱ ሌላ ያለተሸፈነ ሰዉ ቆዳ ጋር የሚገናኝበት ስፍራ) ፈንገሱ በብዛት ሊገኝ ስለሚችል መተላለፉን ሊጨምር ይችላል፡፡

የተሰነጣጠቀ የእግር ቆዳ ለፈንገሱ በቀላሉ መያዝ ምቹ እድል ሊፈጥር ይችላል፡፡

ከመጠን በላይ ላብ( Hyperhidrosis)

የላብ እጢዎች ከመጠን ያለፈ ላብ የሚያመርቱ ከሆነ መጥፎ ጠረን እንዲከሰት ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በብብታቸዉና በእግር/እጅ መዳፍ ዉስጥ ከመጠን ያለፈ ላብ ሊያልባቸዉ ይችላል፡፡  ይህ ከመጠን ያለፈ ላብ መጥፎ የብብትና እግር ጠረን እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ እነዳንድ ሰዎች ላይ ይህ ከመጠን ያለፈ ላብ የመሸማቀቅ ወይም የማፈር ስሜት ሊፈጥርባቸዉ ስለሚችል እራሳቸዉን ከማህበራዊ መስተጋብር ሊያገሉ ይችላሉ፡፡

ሊደረግ የሚችል ሕክምና

የእግርን ንፅህና በአግባቡ በጠበቅ ባክቴሪያዉን ማጥፋት ይቻላል፡፡ እግርን በየቀኑ በመታጠብ፣የእግር ካልሲዎችን/ሹራቦችን ቶሎ ቶሎ በመቀየርና እንዲሁም ጫማን በመቀያየር የእግር ላይ ባክቴሪያ እድገትን መቀነስ ይቻላል፡፡

የችግሩ መንሳኤ ፈንገስ ከሆነ ፓውደር ወይም መድሃኒቶችን በመጠቀም ሊታከም ይችላል።

ለተወሰኑ ጉዳዩች የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች መዳኒቶችን ሊያዙ ይችላሉ።

የተፈጥሮ ማር ጥቅሞች( ያልተቀነባበረ)

ማር በተፈጥሮዉ የተለያዩ የምግብ ንጥረ ነገሮችንና ኢንዛየሞችን የሚይዝና ለጤናና ለመድሃኒትነት የሚያገለግል የምግብ አይነት ነዉ፡፡ ማር በሚቀነባበርበት ወቅት በሚደረገዉ ሂደት በተፈጥሮ ያለዉን ፀረባክቴሪያነቱንና አንታይኦክሲዳንትነቱን ባህሪ ሊያጣ ይችላል፡፡

የማር ጥቅሞች

– ፀረ ባክቴሪያነትና ፀረ ፈንገስ ባህሪይ

– ቁስልን ለማዳን

– የምግብ መፈጨት ሂደትን ለማሻሻል

– የጉሮሮ ላይ ህመምን ለመቀነስ፡- በተለይ ጉንፋንን፡፡ ጉንፋን ሲኖረዎ ማር፣ሻይና ሎሚ ጥሩ መድሃኒቶች ናቸዉ፡፡ ማር ደረቅ ሳልንም ለማስታገስ ይረዳ

– አንታይ ኢነፍላማቶሪና አንታይ ኦክሲዳንት ባህሪይ፡ ማር ከአበባ ስለሚሰራ ተክሎች ደግሞ ፋይቶኒዩትረንት የሚባለዉን ነገር አላቸዉ፡፡ ይህ ደግሞ በማር ዉስጥ በብዛት ስለሚገኝ አንታይ ኢንፍላማቶሪና አንታይኦክሲዳንትነት ባህሪይ እንዲኖረዉ ያደርገዋል፡፡

የጨጓራ ባክቴሪያ / H. pylori infection

 

ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ የሚባለዉ ባክቴሪያ የጨጓራ ኢንፌክሽን እንዲከሰት የሚያደርግ የባክቴሪያ አይነት ሲሆን ይህ ኢንፌክሽን በብዛት የሚከሰተዉ በልጅነት የዕድሜ ክልል ነዉ፡፡ ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ቁስለት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሁነኛ መንስዔዎች ዋነኛዉ ሲሆን ኢንፌክሽኑ በአለማችን ከግማሽ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ አንደሚታይ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

ብዙዎች የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ እንፌክሽን የተፈጠረባቸዉ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አይታይባቸዉም/ላይኖራቸዉ ይችላል ፡፡ የህመም ምልክቶችም ከታዩ የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
• የሆድ ላይ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት
• ጨጓራዎ ባዶ ሲሆን የሚባባስ የጨጓራ ላይ ህመም
• ማቅለሽለሽ
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• በተደጋጋሚ ማስገሳት
• የሆድ መንፋት
• የክብደት መቀነስ (ለመቀነስ ሳይፈልጉ) መከሰት ናቸዉ፡፡

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚጠበቅብዎ መቼ ነዉ?

የሚያሳስብዎና ቀጣይነት/በተደጋጋሚ የሚከሰት የህመም ስሜት ካለዎ እንዲሁም የሚከተሉት ምልክቶች ካሉ ባፋጣኝ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡
• ከፍተኛና የማያቋርጥ የሆድ ላይ ህመም ካጋጠመዎ
• የመዋጥ ችግር ካለዎ
• ደም የተቀላቀለበት ወይም የአስፋልት ሬንጅ የመሰለ/ የጠቆረ ሰገራ ከወጣ
• ቀይ ወይም የቡና አተላ የመሰለ ነገር ካስታወከዎ በአፋጣኝ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

ለኢንፌክሽኑ ሊያጋልጥዎ የሚችሉ ነገሮች

• በተፋፈገ/በተጨናነቀ ቦታ መኖር
• ንፁህ የዉሃ አቅርቦት በሌለበት መኖር
• በማደግ ላይ ባሉ/ባላደጉ አገሮች/ የሚኖሩ ሰዎች፡ ንፅህናዉ በማይጠበቅ ሁኔታ ዉስጥ መኖር
• የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ባክቴሪያል እንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች

• የደም ምርመራ
• የትንፋሽ ምርመራ/ዩሪያ ብሬዝ ቴስት
• የሰገራ ምርመራ ናቸዉ፡፡

ሊደረግ የሚችል ህክምና

የባክቴሪያዉ እንፌክሽን መኖሩ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያዎ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባክቴሪያዉን ሊያጠፋ የሚችሉ መድሃኒቶች ሊያዝልዎ ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

ሊያደርሰዉ የሚችለዉ ጉዳት/ Complications

ከጨጓራ ባክቴሪያ እንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶች
• ቁስለት፡- የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራዎን መከላከያ እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ የጨጓራ አሲዱ ጨጓራዎ ላይ ቁስል አንዲከሰት ያደርጋል፡፡
• የጨጓራ ሽፋን እንዲቆጣ ያደርጋል- የጨጓራ ባክቴሪያ ጨጓራዎን በመቆጥቆጥ እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡
• የጨጓራ ካንሰር፡- የጨጓራ ባክቴሪያ ለተወሱ የጨጓራ ላይ ካንሰሮች መከሰት ዋነኛ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡

ጡትዎን በራስዎ የመመርመር ዘዴ

እራስ በራስ ጡትዎን በየጊዜዉ የሚያዩና የሚከታተሉ ከሆነ እራስ በራስ ጡት የመመርመር ዘዴ ይባላል፡፡ ስለጡትዎ ያለዎትን ግንዛቤ ለመጨመር አይንዎንና እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን በመዳሰስና በማየት በቀላሉ ጡትዎ ላይ ያሉ ለዉጦችን መለየት ይችላሉ፡፡

ለምን ይህን ማድረግ ያስፈልጋል?

ጡትዎን እራስዎ መርምረዉ መገንዘብ ጥቅሙ የጡትዎን ኖርማል/ትክክለኛ የሆነዉን ይዘትና ሁኔታ ለማወቅ ስለሚረዳ ነዉ፡፡ጡትዎ ላይ ትክክለኛ ነገር ያልሆነና የተለወጠ ነገር ካጋጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ስለሚያስችልዎትም ነዉ፡፡
የጡት ካንሰርን ጨምሮ የጡትዎን ሁኔታ ሊለዉጡ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እራስን በራስ ጡትን የመመርመር ዘዴ የጡት ካንሰርን ለማወቅ/ለመመርመር የሚተማመኑበት ሁነኛ መንገድ/ዘዴ አይደለም፡፡ ይሁንና ቁጥራቸዉ ብዙ የሆኑ ሴቶች ሪፖርት እንዳደረጉት ከሆነ የጡት ካንሰር የመጀመሪያዉ ምልክት የሆነዉ የጡት ዉስጥ እብጠት/ሴቶች እራሳቸዉ ጡታቸዉን በሚዳብሱበት ወቅት የተገኘ ነዉ፡፡በዚህ ምክንያት የተነሳ የህክምና ባለሙያዎች የሚመክሩት ሴቶች ኖርማል የሆነዉን የጡታቸዉን ይዘት እንዲያዉቁ ነወ፡፡
እጅዎትን በሰዉነትዎ በጎን በኩል በማድረግና ከወገብ በላይ ራቁት በመሆን በመስታወት ፊት መቆም፡፡ ከዚያን ጡትዎ ላይ የሚከተሉትን ነገሮች/ለዉጦች ካሉ ማየት
  • • ወደፊት ዘምበል በማለት ጡት ላይ የመሸብሸብ፣ የመሰርጎድ፣የመጠን የቅርፅና በሁለቱ ጡት መካከል የመጠን ልዩነት መኖሩን
    • የጡት ጫፍዎ ወደዉስጥ መግባት ያለመግባቱን
    • ሁለቱን እጅዎን በዳሌዎ ላይ በመጫን ጡትዎን ማየት/መመርመር
    • እጅዎን ከራስዎ በላይ ከፍ በማድረግና ሁለቱን መዳፍና መዳፍዎን አንድ ላይ መጫን
    • ጡትዎን ወደላይ ከፍ ማድረግና በታች በኩል ያሉት የጡት ጠርዞች በሁለቱም በኩል ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ
    ከዚያን እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን መመርመር፡ ብዙዉን ጊዜ የሚመከሩ ዘዴዎች
    • መንጋለል፡- በጀርባዎ ለመተኛት እንዲመችዎ በአልጋ ላይ ወይም ለጥ ያለ ቦታ መምረጥ
    • በሻወር ወቅት፡- ጡትዎንና ጣትዎን ሳሙና በመቀባት በደንብ እንዲያሟልጭ በማድረግ በቀላሉ በቆዳዎ ላይ እንዲሸራተት ማደረግ
    ጡትዎን በሚዳስሱበት/በሚመረምሩበት ወቅት ሊከተሉት የሚገባ ምክር
    • የእጅዎን መዳፍ መጠቀም
    • ጡትዎን በሚመረምሩበት ወቅት በተለያየ ደረጃ መጫን(አንዳንዴ በስሱ ሌላ ጊዜ በደንብ ጫን በማድረግ)
    • በደንብ ጊዜ ወስዶ መመርመር
    • የሚመረምሩበትን ዘዴ/ንድፍ አዉቆ መከተል

ዉጤት

በወር አበባ ዑደት ወቅት የሚከሰቱ ለዉጦች ብዙዎቹ ኖርማል ናቸዉ፡፡ በጡትዎ ላይ ለዉጥ ወይም የሆነ እብጠት/የጠጠረ ነገር ቢያገኙ መደናገጥ የለብዎትም፡፡ በጡትዎ የታችኛዉ ጠርዝ ላይ የሚታዩ ጠንከር ያሉ ነገሮች እምብዛም የሚያሳስቡ ነገሮች አይደሉም፡፡ እድሜዎ በጨመረ ቁጥር የጡትዎ ሁኔታ እየተቀየረ ይመጣል፡፡

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያለብዎ መቼ ነዉ?

  • • በጡትዎ ላይ ጠንካራ/ጥጥር የሆነ እብጠት ወይም በብብትዎ ስር ጥጥር የሆነ እብጠት ካለ
    • ጡትዎን ሲዳስሱት ወይም ሲያዩት የተለወጠ ከመሰለዎ፡- የመወፈር፣ በዙሪያዉ ካለዉ አካል በተለየ ሁኔታ ማበጥ/መለየት ካለዉ
    • የሰረጎደ፣የተሸበሸበ፣ያበጠ ወይም ጠርዝ ያወጣ ነገር በጡትዎ ላይ ከተመለከቱ
    • በቅርቡ የተከሰተ ወደ ዉስጥ የገባ የጡት ጫፍ
    • የመቅላት፣የመሞቅ፣የማበጥ ወይም ህመም ጡትዎ ላይ ካለ
    • የማሳከክ፣ሽፍታ፣ቁስለት ጡትዎ ላይ ካዩ
    • ደም የተቀላቀለበት የጡት ፈሳሽ ካለዎ ናቸዉ፡፡

ቆስጣ ይመገባሉ?

እንግዲያዉስ በይበልጥ እንዲያዘወትሩት እንመክሮታለን።
ይህ የጓሮ ኣትክልት በውስጡ አራት የሚሆኑ ቫይታሚኖችን (Vitamin A, C, K,B,(B2 &B6) ይይዛል በተጨማሪም በሽታ የመከላከል አቅምን ያጎለብታል፡፡

የሰዉነት ሸንተረር (Stretch marks)

ሸንተረር ቀይ፣ሃምራዊ ወይም የወይንጠጅ ቀለም ያለዉና በብዛት በሆድ፣ ጡት፣በክርና ትከሻ መሃል፣በመቀመጫና በታፋ ላይ የሚከሰት ሲሆን በሂደት መልኩ እየደበዘዘ ወደ ነጭ ወይም ግራጫ መልክ እየተቀየረ የሚመጣ የቆዳ ላይ ችግር ነዉ፡፡

ምልክቶች

ሁሉም ሸንተረሮች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ የመለያየታቸዉ ምክንያት ደግሞ በሰዉነት ላይ ከወጡ በኃላ የነበራቸዉ እርዝማኔ፣ ሸንተረሩ እንዲከሰት እንደአደረገዉ ምክንያትና የተከሰተ ቦታ እንዲሁም የቆዳዎ ሁኔታ ናቸዉ፡፡

· በቆዳዎ ላይ ወደ ዉስጥ ገባ ያለ መስመር

· ቀይ፣ሃምራዊ ወይም የወይንጠጅ ቀለም ያላቸዉ ሸንተረሮች በብዛት መከሰት

· ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ወደ ነጭ ወይም ግራጫ መልክ የሚቀየር ደማቅ የሆነ ሸንተረር መከሰት ናቸዉ፡፡

ለሸንተረር መከሰት ምክንያቶች

ሸንተረር የሚከሰተዉ የሰዉነት ቆዳ በሚወጠርበት ጊዜ ሲሆን ይህ እንዲፈጠር የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ:: እነርሱም

· እርግዝና

· ክብደት መጨመር

· መድሃኒቶች፡- የኮርቲኮስቴሮይድ ክሬም፣ ሎሽን ወይም እንክበሎች

· ህመሞች፡- የአድሬናል ግላንድ/ዕጢ ችግሮችና ኩሽንግ ሲንድረም የሚባለዉ ህመም ሲኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች

ምንም እንኳን ሸንተረር በማንኛዉም ሰዉ ላይ ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ይበልጥ የመከሰቱን ነገር ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎች

· ሴት መሆን

· በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር

· እርግዝና ከነበረ

· ከመጠን ያለፈ ክብደት ወይም ዉፍረት መኖር

· ክብደት በፍጥነት የሚጨምሩ ወይም የሚቀንሱ ሰዎች- ለምሳሌ በእርግዝና ጊዜያት

· ኮርቲኮስቴሮይድ መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች

የሚሰጡት ህክምናዎች ሸንተረሩ እንዲደበዝዝ ቢደርግም ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋዉ ግን አይችልም፡፡ ምንም እንኳ ሸንተረር ሲከሰት ሰዎች ላይ አሳሳቢ ቢመስልም/ cosmetic concern ቢኖረዉም/ በጤናዎ ላይ ምንም ጉዳት አያደርስም፡፡ በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ይመጣል፡፡

ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ

· የሌዘር ህክምና፡- ይህ የህክምና ዘዴ በቆዳዎ ዉስጥ ያሉትን ኮላጂን፤ኢላስቲን ወይም ሜላሊን የተባሉ ኬሚካሎችን እንዲመረቱ በማነቃቃት ችግሩ እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡

· የቤት ዉስጥ ህክምናና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ፡- እንደ ክሬም፣ ቅባትና ሌሎች ዉጤቶች ሸንተረርን ለመቀነስ ይረዳሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ እነዚህ ነገሮች በዉስጣቸዉ የኮኮአ ቅቤ፣ቫይታሚን ኢ ወይም ግላይኮሊክ አሲድ ስላላቸዉ ብዙ ባይረዱም በመጠቀምዎ የሚኖራቸዉ ጉዳት ስለሌለ መጠቀም ይችላሉ፡፤

እንዴት መከላከል ይቻላል

የቱንም ያህል መጠን ያለዉ ሎሽንም ይሁን ቅባት በሰዉነትዎ ላይ ቢቀቡ ሸንተረርን መከላከል አይችሉምም፡፡ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ የሸንተረርን የመከሰት ሂደት ለመቀነስ ከሚረዱ መንገዶች ዋነኛዉ ነዉ፡፡

የሰዉነት ሸንተረር (Stretch marks)

ሸንተረር ቀይ፣ሃምራዊ ወይም የወይንጠጅ ቀለም ያለዉና በብዛት በሆድ፣ ጡት፣በክርና ትከሻ መሃል፣በመቀመጫና በታፋ ላይ የሚከሰት ሲሆን በሂደት መልኩ እየደበዘዘ ወደ ነጭ ወይም ግራጫ መልክ እየተቀየረ የሚመጣ የቆዳ ላይ ችግር ነዉ፡፡

ምልክቶች

ሁሉም ሸንተረሮች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ የመለያየታቸዉ ምክንያት ደግሞ በሰዉነት ላይ ከወጡ በኃላ የነበራቸዉ እርዝማኔ፣ ሸንተረሩ እንዲከሰት እንደአደረገዉ ምክንያትና የተከሰተ ቦታ እንዲሁም የቆዳዎ ሁኔታ ናቸዉ፡፡

· በቆዳዎ ላይ ወደ ዉስጥ ገባ ያለ መስመር

· ቀይ፣ሃምራዊ ወይም የወይንጠጅ ቀለም ያላቸዉ ሸንተረሮች በብዛት መከሰት

· ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ወደ ነጭ ወይም ግራጫ መልክ የሚቀየር ደማቅ የሆነ ሸንተረር መከሰት ናቸዉ፡፡

ለሸንተረር መከሰት ምክንያቶች

ሸንተረር የሚከሰተዉ የሰዉነት ቆዳ በሚወጠርበት ጊዜ ሲሆን ይህ እንዲፈጠር የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ:: እነርሱም

· እርግዝና

· ክብደት መጨመር

· መድሃኒቶች፡- የኮርቲኮስቴሮይድ ክሬም፣ ሎሽን ወይም እንክበሎች

· ህመሞች፡- የአድሬናል ግላንድ/ዕጢ ችግሮችና ኩሽንግ ሲንድረም የሚባለዉ ህመም ሲኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች

ምንም እንኳን ሸንተረር በማንኛዉም ሰዉ ላይ ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ይበልጥ የመከሰቱን ነገር ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎች

· ሴት መሆን

· በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር

· እርግዝና ከነበረ

· ከመጠን ያለፈ ክብደት ወይም ዉፍረት መኖር

· ክብደት በፍጥነት የሚጨምሩ ወይም የሚቀንሱ ሰዎች- ለምሳሌ በእርግዝና ጊዜያት

· ኮርቲኮስቴሮይድ መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች፡- የሚሰጡት ህክምናዎች ሸንተረሩ እንዲደበዝዝ ቢደርግም ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋዉ ግን አይችልም፡፡ ምንም እንኳ ሸንተረር ሲከሰት ሰዎች ላይ አሳሳቢ ቢመስልም/ cosmetic concern ቢኖረዉም/ በጤናዎ ላይ ምንም ጉዳት አያደርስም፡፡ በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ይመጣል፡፡

ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ

· የሌዘር ህክምና፡- ይህ የህክምና ዘዴ በቆዳዎ ዉስጥ ያሉትን ኮላጂን፤ኢላስቲን ወይም ሜላሊን የተባሉ ኬሚካሎችን እንዲመረቱ በማነቃቃት ችግሩ እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡

· የቤት ዉስጥ ህክምናና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ፡- እንደ ክሬም፣ ቅባትና ሌሎች ዉጤቶች ሸንተረርን ለመቀነስ ይረዳሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ እነዚህ ነገሮች በዉስጣቸዉ የኮኮአ ቅቤ፣ቫይታሚን ኢ ወይም ግላይኮሊክ አሲድ ስላላቸዉ ብዙ ባይረዱም በመጠቀምዎ የሚኖራቸዉ ጉዳት ስለሌለ መጠቀም ይችላሉ፡፤

እንዴት መከላከል ይቻላል

የቱንም ያህል መጠን ያለዉ ሎሽንም ይሁን ቅባት በሰዉነትዎ ላይ ቢቀቡ ሸንተረርን መከላከል አይችሉምም፡፡ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ የሸንተረርን የመከሰት ሂደት ለመቀነስ ከሚረዱ መንገዶች ዋነኛዉ ነዉ፡፡

የአባለዘር ህመም ህክምና

መድሃኒቶች

በባክቴሪያ የሚከሰቱ የአባለዘር ህመሞችን በቀላሉ በፀረባክቴሪያ ማከም ይቻላል፡፡በቫይረስ አማካይነት የሚመጡትን የአባለዘር ህመሞች ማከም ቢቻልም ሁሌ ሙሉ በሙሉ ማዳን አይቻልም፡፡የአባለዘር ህመም ህክምና እንደ እንፌክሽኑ አይነት የሚከተለዉ ሊሆን ይችላል፡፡

• ፀረባክቴሪያ

ፀረባክቴሪያዎች ብዙዎችን በባክቴሪያና በፓራሳይት ምክንያት የሚከሰቱትን የአባለዘር ህመሞች ለማከም ይረዳሉ፡፡እነርሱም ጨብጥ፣ቂጥኝ፣ክላሚዲያ እና ተሪኮሞኒያሲስን የመሳሰሉትን ያክማል፡፡ ጨብጥና ክላሚዲያ ብዙዉን ጊዜ አብረዉ የሚከሰቱ ስለሆነ ህመም ሲመጣ ሁለቱም በአንዴ ይታከማሉ፡፡
አንዴ ህክምና ከጀመሩ በሚገባ ተከታትለዉ መጨረስ ይገባዎታል/ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የአባለዘር ቁስለት/ ህመሙ ሙሉ ለሙሉ እስኪድን ድረስ ከግብረስጋ ግንኙነት መታቀብ ይኖርብዎታል፡፡

• ፀረቫይረስ

ፀረቫይረሶች የቫይረስ እንፌክሽኑን ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡
የትዳር/ፍቅር አጋርን ማሳወቅና የመከላከል ህክምና
እርስዎ የአባለዘር ህመም እንዳለብዎ ከታወቀ የትደር አጋርዎ፣ አሁን አብረዉ ያሉ የፍቅር አጋርዎ አሊያም ከሌላ የፍቅር አጋር/አጋሮች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ባለፈዉ 3 ወር እስከ አንድ አመት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ከነበረዎ ሁሉም አዉቀዉ ምርመራና ህክምና እንዲያደርጉ ሊነገራቸዉ ይገባል፡፡

የአባለዘር ህመምን መከላከል

የአባለዘር ህመም ተጋላጭነትዎን ለመቀነስ የሚመከሩ መንገዶች

• መታቀብ

የአባለዘር ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ ዋነኛ መንገዶች ዉስጥ ዋናዉ መታቀብ ነዉ፡፡

• አንድ ለአንድ ተማምኖ መኖር

ሌለኛዉ ከአባለዘር ህመም እራስን ጠብቆ ለመኖር የአባለዘር እንፌክሽን ከሌለዉ አንድ የፍቅር/ትዳር አጋር ጋር ተማምኖ መዝለቅ

• መዘግየት/መረጋጋትና ማረጋገጥ

ሁለታችሁም ለአባለዘር ህመም ምርመራ አድርጋችሁ ነፃ መሆናችሁን እስክታረጋግጡ ድረስ ማንኛዉንም የግብረስጋ ግንኙነት ሳያደርጉ መቆየት/መዘግየት

• ኮንደምን መጠቀም

በእያንዳንዱ የግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ኮንደምን ሁሌ በትክክል መጠቀም

• ከአልኮሆል/አደንዛዥ ዕፅ መቆጠብ

አልኮልን ከመጠን አልፈዉ ያለመጠጣት፤ እራስን ከአደንዛዥ ዕፅ መጠበቅ፡፡ አለበለዚያ እራስዎን ለአላስፈላጊ የግብረስጋ ግንኙነት ተጋላጭነትዎን ይጨምራሉና

• መነጋገር

ከግብረስጋ ግንኑነት በፊት ከፍቅር/ትዳር አጋርዎ ጋር ጥንቃቄ ስለተሞላበት የግብረስጋ ግንኙት መነጋገር።