ልጅዎ የአራት አመት ዕድሜ ሳለ

41254786_m

ከዚህ በፊት የህፃን ልጅዎን የአጨዋወት፣ አነጋገር/ቋንቋ፣ እንዴት እንደሚማር እና እንቅስቃሴዎችን እንዴት እንደሚተገብር በመከታተል ስለልጅዎ የእድገት ሁኔታ ፍንጭ ማግኘት እንደሚቻልና የሶስት ዓመት ህፃን ሊያሳይ የሚችላዉን ነገሮች መነጋገራችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዘዚያ የቀጠለ የአራት አመት ልጅ የእድገት ክትትልን እናያለን፡፡

አብዛኞቹ ህፃናት በዚህ እድሜ ምን ምን ነገሮችን ይተገብራሉ?

ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional

  • አዳዲስ ነገሮችን በመስራት ይደሰታሉ
  • እናት አባት/ እንደ እናትና አባት በመሆን/ ጨዋታዎችን ይጫወታሉ
  • ብቻቸዉን ከመጫወት ይልቅ ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወትን ይመርጣሉ
  • ከሌሎች ልጆች ጋር ይግባባሉ/ይረዳዳሉ
  • ስለሚወዱትና ስለሚያስደስታቸዉ ነገሮች ማዉራት ይችላሉ

ቋንቋ /መግባባት (Language/Communication)

  • የተወሰኑ ትክክለኛ የቃላት አገባብን /ግራመር/ አጠቃቀም ያዉቃሉ
  • ግጥም ወይም ዘፈን አስታዉሰዉ ማለት ይችላሉ
  • ተረት መንገር ይችላሉ
  • ስማቸዉን እስከ አያታቸዉ መናገር ይችላሉ፡፡

አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና  ችግርን መፍታት መቻል)

·         የተወሰኑ የከለር አይነቶችንና ቁጥሮችን መለየት መቻል

  • መቁጠር ምን እንደሆነ መረዳት መቻል
  • ሰዓት/ጊዜን መረዳት መቻል
  • የተነገረዉን የታሪክ/ተረት ክፍል በተወሰነ መልኩ ማስታወስ መቻል
  • አንድ አይነትና የተለያዩ የሚባሉ ሃሳቦችን መለየት መቻል
  • አንድን ሰዉ ከሁለት እስከ አራት የሚደርሱ የሰዉነት አካላቶቹን በማካተት መሳል መቻል
  • የፊደላትን ትላልቁን /ካፒታል ሌተሮችን/ መፃፍ መቻል
  • በካርድ የተሰሩ መጫወቻዎችን በመጠቀም መጫወት መቻል፡፡

እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development

  • በአንድ እግሩ እስከ ሁለት ሰኮንድ መቆም መቻል
  • የምትነጥርን ኳስ መያዝ መቻል
  • ክትትል እየተደረገባቸዉ ዉሃ ማንቆርቆር መቻል፣ መቁረጥ መቻል

Recent Posts

Comments

comments