አንዲት ሴት ያለምንም ችግር ምን ያህል ጊዜ በኦፕራሲዮን ልትወልድ ትችላለች?

አንዲት ሴት ያለምንም ችግር ምን ያህል ጊዜ በኦፕራሲዮን ልትወልድ ትችላለች?

 

በተደጋጋሚ የሚሰራዉ /የሚደረገዉ ኦፕራሲዮን ከበፊቱ ይልቅ የሚኖረዉ ጉዳት ከፍ እያለ ይመጣል ፡፡ ምንም እንኳ ጥናቶች አንዲት እናት ያለምንም ችግር ምን ያህል ጊዜ በኦፕራሲዮን መዉለድ እንደምትችል በዉል ባያረጋግጡም/ባያስቀምጡም ከሶስትኛ ጊዜ በኃላ የሚደረግ ኦፕራሲዮን የሚያደርሰዉ/የሚያመጣዉ ጉዳት እየከፋ እንደሚመጣ በትትክል ተዘግቧ፡፡

በተደጋጋሚ ኦፕራሲዮን የሚደረጉ እናቶች ለሚከተሉት ነገሮች ሊጋለጡ ይችላሉ፡-

 

• ጠባሳ በማህፀናቸዉና አከባቢዉ ላይ ባሉ አካላት ላይ መከሰት፡- ምንም እንኳ ደረጃቸዉ ቢለያይም በማህፀንና በአካባቢዉ ባሉ አካላት ላይ መጣበቅ ሊፈጠር ይችላል፡፡

 

• የአንጀትና የሽንት ፊኛ ላይ ከኦፕራሲዮን ጋር የተያያዘ አደጋዎች መድረስ፡- የሽንት ፊኛ ላይ አደጋ በመጀመሪያዉ ኦፕራሲዮን ወቅት የመድረስ አጋጣሚዉ ቢኖርም የተለመደ ግን አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህ አደጋ በሚቀጥሉት ኦፕራሲዮኖች ላይ በፊት በተደረገዉ ኦፕራሲዮን ምክንያት ከማህፀንና ከሌሎች አካላት ጋር ሲድን ስለሚጣበቅ ለአደጋ የመጋለጡ እድል እየጨመረ ይመጣል፡፡ ይህ አንጀትም በበፊቱ ኦፕራሲዮን ምክንያት ከማህፀን ጋር ስለሚጣበቅ አደጋ እንዲከሰት ያደርጋል

 

• መጠኑ ከፍ ያለ የብልት መድማት መከሰት፡- ከማንኛዉም ኦፕራሲዮን በኃላ የመድማት እድሉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡ ነገር ግን የሚደረገዉ የኦፕራሲዮን ቁጥር እየጨመረ በመጣ ሰዓት ብዙ የመድማቱ እድል እየጨመረ ይመጣል፡፡ የሚደረጉት ኦፕራሲየኖች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ የእናትየዋን ህይወት ለመታደግና መድማቱን ለመቆጣጠር ማህፀን ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ የማድረጉ እድልም እየጨመረ ይመጣል፡፡

 

• ከእንግዴ ልጅ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ችግር፡- የሚሰራልዎ የኦፕረሰሲዮን ቁጥር በጨመረ በመጣ ቁጥር ከእንግዴ ልጅ ጋር ተያይዞ ሊደርስ የሚችለዉ ችግር እየጨመረ ይመጣል፡፡ ይህም የእንግዴ ልጁ ወደ ማህፀንዎ ግድግዳ ከመጠን ባለፈ ሁኔታ መጣበቅ(ፕላሴንታ አክሬታ) አሊያም በትክክለኛዉ ቦታ ያለመቀመጥ(ለምሳሌ የማህፀን አንገትን መሸፈን–ፕላሴንታ ፕሬቪያ) ሊሆን ይችላል፡፡

 

ሁለቱም ማለትም በማህፀንም(አምጦ መዉለድም) ይሁን በኦፕራሲዮን መዉለድ የየራሳቸዉ ጉዳትና ጥቅም አላቸዉ፡፡ ከኦፕራሲዮን በኃላ በሚቀጥሉት ጊዜ በየትኛዉ መንገድ መዉለድ እንዳለብዎ መወሰን የተወሳሰበ ነዉ፡፡ ስለሆነም ከህክምና ባለሙያዎ ጋር ስለቀጣይ የመዉለጃዉ መንገድና ቀጣይ ቢያረግዙ ሊኖሩ ስለሚችለዉ ችግር እንዲወያዩ ይመከራሉ፡፡

Comments

comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *