ጡትዎን በራስዎ የመመርመር ዘዴ

ጡትዎን በራስዎ የመመርመር ዘዴ

እራስ በራስ ጡትዎን በየጊዜዉ የሚያዩና የሚከታተሉ ከሆነ እራስ በራስ ጡት የመመርመር ዘዴ ይባላል፡፡ ስለጡትዎ ያለዎትን ግንዛቤ ለመጨመር አይንዎንና እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን በመዳሰስና በማየት በቀላሉ ጡትዎ ላይ ያሉ ለዉጦችን መለየት ይችላሉ፡፡

ለምን ይህን ማድረግ ያስፈልጋል?

ጡትዎን እራስዎ መርምረዉ መገንዘብ ጥቅሙ የጡትዎን ኖርማል/ትክክለኛ የሆነዉን ይዘትና ሁኔታ ለማወቅ ስለሚረዳ ነዉ፡፡ጡትዎ ላይ ትክክለኛ ነገር ያልሆነና የተለወጠ ነገር ካጋጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ስለሚያስችልዎትም ነዉ፡፡
የጡት ካንሰርን ጨምሮ የጡትዎን ሁኔታ ሊለዉጡ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እራስን በራስ ጡትን የመመርመር ዘዴ የጡት ካንሰርን ለማወቅ/ለመመርመር የሚተማመኑበት ሁነኛ መንገድ/ዘዴ አይደለም፡፡ ይሁንና ቁጥራቸዉ ብዙ የሆኑ ሴቶች ሪፖርት እንዳደረጉት ከሆነ የጡት ካንሰር የመጀመሪያዉ ምልክት የሆነዉ የጡት ዉስጥ እብጠት/ሴቶች እራሳቸዉ ጡታቸዉን በሚዳብሱበት ወቅት የተገኘ ነዉ፡፡በዚህ ምክንያት የተነሳ የህክምና ባለሙያዎች የሚመክሩት ሴቶች ኖርማል የሆነዉን የጡታቸዉን ይዘት እንዲያዉቁ ነወ፡፡
እጅዎትን በሰዉነትዎ በጎን በኩል በማድረግና ከወገብ በላይ ራቁት በመሆን በመስታወት ፊት መቆም፡፡ ከዚያን ጡትዎ ላይ የሚከተሉትን ነገሮች/ለዉጦች ካሉ ማየት
  • • ወደፊት ዘምበል በማለት ጡት ላይ የመሸብሸብ፣ የመሰርጎድ፣የመጠን የቅርፅና በሁለቱ ጡት መካከል የመጠን ልዩነት መኖሩን
    • የጡት ጫፍዎ ወደዉስጥ መግባት ያለመግባቱን
    • ሁለቱን እጅዎን በዳሌዎ ላይ በመጫን ጡትዎን ማየት/መመርመር
    • እጅዎን ከራስዎ በላይ ከፍ በማድረግና ሁለቱን መዳፍና መዳፍዎን አንድ ላይ መጫን
    • ጡትዎን ወደላይ ከፍ ማድረግና በታች በኩል ያሉት የጡት ጠርዞች በሁለቱም በኩል ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ
    ከዚያን እጅዎን በመጠቀም ጡትዎን መመርመር፡ ብዙዉን ጊዜ የሚመከሩ ዘዴዎች
    • መንጋለል፡- በጀርባዎ ለመተኛት እንዲመችዎ በአልጋ ላይ ወይም ለጥ ያለ ቦታ መምረጥ
    • በሻወር ወቅት፡- ጡትዎንና ጣትዎን ሳሙና በመቀባት በደንብ እንዲያሟልጭ በማድረግ በቀላሉ በቆዳዎ ላይ እንዲሸራተት ማደረግ
    ጡትዎን በሚዳስሱበት/በሚመረምሩበት ወቅት ሊከተሉት የሚገባ ምክር
    • የእጅዎን መዳፍ መጠቀም
    • ጡትዎን በሚመረምሩበት ወቅት በተለያየ ደረጃ መጫን(አንዳንዴ በስሱ ሌላ ጊዜ በደንብ ጫን በማድረግ)
    • በደንብ ጊዜ ወስዶ መመርመር
    • የሚመረምሩበትን ዘዴ/ንድፍ አዉቆ መከተል

ዉጤት

በወር አበባ ዑደት ወቅት የሚከሰቱ ለዉጦች ብዙዎቹ ኖርማል ናቸዉ፡፡ በጡትዎ ላይ ለዉጥ ወይም የሆነ እብጠት/የጠጠረ ነገር ቢያገኙ መደናገጥ የለብዎትም፡፡ በጡትዎ የታችኛዉ ጠርዝ ላይ የሚታዩ ጠንከር ያሉ ነገሮች እምብዛም የሚያሳስቡ ነገሮች አይደሉም፡፡ እድሜዎ በጨመረ ቁጥር የጡትዎ ሁኔታ እየተቀየረ ይመጣል፡፡

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያለብዎ መቼ ነዉ?

  • • በጡትዎ ላይ ጠንካራ/ጥጥር የሆነ እብጠት ወይም በብብትዎ ስር ጥጥር የሆነ እብጠት ካለ
    • ጡትዎን ሲዳስሱት ወይም ሲያዩት የተለወጠ ከመሰለዎ፡- የመወፈር፣ በዙሪያዉ ካለዉ አካል በተለየ ሁኔታ ማበጥ/መለየት ካለዉ
    • የሰረጎደ፣የተሸበሸበ፣ያበጠ ወይም ጠርዝ ያወጣ ነገር በጡትዎ ላይ ከተመለከቱ
    • በቅርቡ የተከሰተ ወደ ዉስጥ የገባ የጡት ጫፍ
    • የመቅላት፣የመሞቅ፣የማበጥ ወይም ህመም ጡትዎ ላይ ካለ
    • የማሳከክ፣ሽፍታ፣ቁስለት ጡትዎ ላይ ካዩ
    • ደም የተቀላቀለበት የጡት ፈሳሽ ካለዎ ናቸዉ፡፡

Comments

comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *