የአባለዘር ህመም ህክምና

የአባለዘር ህመም ህክምና

መድሃኒቶች

በባክቴሪያ የሚከሰቱ የአባለዘር ህመሞችን በቀላሉ በፀረባክቴሪያ ማከም ይቻላል፡፡በቫይረስ አማካይነት የሚመጡትን የአባለዘር ህመሞች ማከም ቢቻልም ሁሌ ሙሉ በሙሉ ማዳን አይቻልም፡፡የአባለዘር ህመም ህክምና እንደ እንፌክሽኑ አይነት የሚከተለዉ ሊሆን ይችላል፡፡

• ፀረባክቴሪያ

ፀረባክቴሪያዎች ብዙዎችን በባክቴሪያና በፓራሳይት ምክንያት የሚከሰቱትን የአባለዘር ህመሞች ለማከም ይረዳሉ፡፡እነርሱም ጨብጥ፣ቂጥኝ፣ክላሚዲያ እና ተሪኮሞኒያሲስን የመሳሰሉትን ያክማል፡፡ ጨብጥና ክላሚዲያ ብዙዉን ጊዜ አብረዉ የሚከሰቱ ስለሆነ ህመም ሲመጣ ሁለቱም በአንዴ ይታከማሉ፡፡
አንዴ ህክምና ከጀመሩ በሚገባ ተከታትለዉ መጨረስ ይገባዎታል/ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የአባለዘር ቁስለት/ ህመሙ ሙሉ ለሙሉ እስኪድን ድረስ ከግብረስጋ ግንኙነት መታቀብ ይኖርብዎታል፡፡

• ፀረቫይረስ

ፀረቫይረሶች የቫይረስ እንፌክሽኑን ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡
የትዳር/ፍቅር አጋርን ማሳወቅና የመከላከል ህክምና
እርስዎ የአባለዘር ህመም እንዳለብዎ ከታወቀ የትደር አጋርዎ፣ አሁን አብረዉ ያሉ የፍቅር አጋርዎ አሊያም ከሌላ የፍቅር አጋር/አጋሮች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ባለፈዉ 3 ወር እስከ አንድ አመት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ከነበረዎ ሁሉም አዉቀዉ ምርመራና ህክምና እንዲያደርጉ ሊነገራቸዉ ይገባል፡፡

የአባለዘር ህመምን መከላከል

የአባለዘር ህመም ተጋላጭነትዎን ለመቀነስ የሚመከሩ መንገዶች

• መታቀብ

የአባለዘር ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ ዋነኛ መንገዶች ዉስጥ ዋናዉ መታቀብ ነዉ፡፡

• አንድ ለአንድ ተማምኖ መኖር

ሌለኛዉ ከአባለዘር ህመም እራስን ጠብቆ ለመኖር የአባለዘር እንፌክሽን ከሌለዉ አንድ የፍቅር/ትዳር አጋር ጋር ተማምኖ መዝለቅ

• መዘግየት/መረጋጋትና ማረጋገጥ

ሁለታችሁም ለአባለዘር ህመም ምርመራ አድርጋችሁ ነፃ መሆናችሁን እስክታረጋግጡ ድረስ ማንኛዉንም የግብረስጋ ግንኙነት ሳያደርጉ መቆየት/መዘግየት

• ኮንደምን መጠቀም

በእያንዳንዱ የግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ኮንደምን ሁሌ በትክክል መጠቀም

• ከአልኮሆል/አደንዛዥ ዕፅ መቆጠብ

አልኮልን ከመጠን አልፈዉ ያለመጠጣት፤ እራስን ከአደንዛዥ ዕፅ መጠበቅ፡፡ አለበለዚያ እራስዎን ለአላስፈላጊ የግብረስጋ ግንኙነት ተጋላጭነትዎን ይጨምራሉና

• መነጋገር

ከግብረስጋ ግንኑነት በፊት ከፍቅር/ትዳር አጋርዎ ጋር ጥንቃቄ ስለተሞላበት የግብረስጋ ግንኙት መነጋገር።

Comments

comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *