ለክብደት መቀነስ ሚስጥሩ ምንድን ነዉ? (What is the secret to healthy loss of weight?)

ዛሬ በክብደት መቀነስ ላይ ምክሮች እንሰጥዎታለን፡፡ስለክብደት መቀነስም ይሁን ስለሌላ የጤና ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 8896 ሃሎ ዶክተር ላይ በመደወል በቂ ልምድና ሙያ ያላቸዉን ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡ እርስዎን ለማማከር ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ፡፡

ክብደትን ለመቀነስ የሚረዱ ዘዴዎችና ፕሪንስፕሎች(መመሪያዎች) ተመሳይ የሆኑ ምክሮች ሲሁኑ እነሱም ጤናማ የምግብ አመጋገብ ዘዴን መከተል፣የሚመገቡትን የምግብ መጠን መወሰንና ተከታታይ የአካል እንቅስቃሴን ማዘዉተር ናቸዉ፡፡በየጊዜዉ የተወሰነ ክብደት እየቀነሱ ለመቀጠል ከፈለጉ ከዕለት ተዕለት የአኗኗር እንቅስቃሴዎት ዉስጥ ጤናማ ባህሪያትን በማካተት የአኗኗር ዘይቤዎ አካል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ክብደትን ለመቀነስ ከፈለጉ ምንም አይነት ተዓምር መጠበቅ አያስፈልግም፡፡ጤናማ አኗኗሮትን ለማጠናከርና ቀጣይንት ያለዉ ክብደትን ለመቀነስ ካሰቡ የሚከተሉት 20 ምክሮች እነሆ፡-

1. በየቀኑ ከ30 እስከ 60 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

2. በቀን ሦስት ጊዜ ጤናማ ምግብ መመገብ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ አንዱን ወይም ሌላዉን መዝለል መራብን ስለሚያመጣ መክሰስን በብዛት እንዲመገቡ ያደርገዎታል፡፡ ስለዚህ ይህን ከማድረግ መቆጠብ

3. አትክልትና ፍራፍሬ ምግቦችን ማዘዉተር

4. በየጊዜዉ የክብደት ክትትል ማድረግ/መለካት

5. በቀላሉ የሚገኙ ጣፋጭ ምግቦችን በቤት ዉስጥ ያለማስቀመጥ

6. ከቤተሰብ ጋር ሊደረጉ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ማከናወን

7. ጤናማ ምግቦችን በመጀመሪያ መመገብ፡- ለምሳሌ ፓስታና ሰላጣ መመገብ ቢገባዎ አስቀድመዉ ሰላጣዉን በመመገብ የመጥገብ ስሜትዎን ያምጡ

8. ለሚመገቡት ምግብ መጠን ትኩረት መስጠት

9. እንቅስቃሴ ሊፈጥሩ ለሚችሉ ነገሮች እድል መፍጠር

10. ከቤተሰብ ጋር አብረዉ መመገብ ጥሩ ነዉ፡፡ነገር ግን ቴሌቪዥን እያዩ መመገብ ምን ያህልና ምን እየተመገቡ እንደሆነ ለመገመት ስለሚያስቸግርዎ ጥንቃቄ ያድረጉ፡፡

11. እየተመገቡ ያሉትን ምግብ ማወቅ

12. እንቅስቃሴዎትን ማቀያየር

13. ጭንቀትን መቀነስ

14. የቤት ምግብን መመገብ

15. ጤናማ መክሰስ መመገብ

16. ቀኑን ብዙ ፋይበር ባላቸዉ ምግቦች በመመገብ ይጀምሩ

17. በምሳ ሰዓት ለ10 ደቂቃዎች ወክ ማድረግ

18. ለሳምንቱ የሚጠቀሙበትን የምግብ ፕሮግራግራም/መርሃ ግብር አስቀድሞ ማዉጣት

19. ምግብ ሲያምሮት/የምግብ መጓጓት ካለዎት ሀሳብዎትን ለመርሳት በሌላ ነገር መጠመድ

20. እራስን መሸለም/ማበረታታት

Comments

comments