Posted by hellodoc on
ሪህ(ጋዉት) የሚባለዉ ህመም በደም ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ዩሬት ክሪስታልስ በመገጣጠሚያ አካባቢዎች እንዲጠራቀም በማድረግ መገጣጠሚያዎቹ ላይ ህመም እንዲከሰት የሚያደርግ የህመም አይነት ነዉ፡፡
ስለሆነም ለሪህ ህመም የሚስማማዉን የአመጋገብ ዘዴዎችን መከተል በደም ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠንን መቀነስ ያስችላል፡፡ ምግቦቹ ህመሙን ለማዳን ባይረዱም ህመሙ በተደጋጋሚ እንዳይከሰትና በህመሙ ምክንት የሚከሰተዉን የመገጣጠሚያ ላይ ጉዳት ለመቀነስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ህመሙን እንዲሁም በደም ዉስጥ ያለዉን የዩሪክ አሲድ መጠን ለመቀነስ መድሃኒቶችን መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡
የአመጋገቡ ዝርዝር፡
በአጠቃላይ የአመጋገብ መርሆዉ ከተመጣጠ አመጋገብ ስርዓት ጋር የሚመሳሰል ነዉ፡፡
- ክብደት መቀነስ፡- ክብደትዎ ሲጨምር የሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን የሚጨምር ሲሆን ክብደትዎን መቀነስ ግን ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎ እንዲቀንስ ይረዳል፡፡
- ኮምፕሌክስ ካርቦሃይድሬትስ/ኃይል ሰጪ ምግቦቸ፡- አታክልት፣ ፍራፍሬና ጥራጥሬ ምግቦችን ማዘዉተር፡፡ እንደ ነጭ ዳቦ፣ኬክ፣ ከረሜላ ፣ ስኳርነት ያላቸዉን መጠጦችን/ፈሳሾችን መተዉ/አለመመገብ ይመከራል፡፡
- ዉሃ፡- በቀን ዉስጥዉሃን አብዝቶ መጠጣት ለሪህ ህመም መቀነስ ጋር ተያያዥነት አለዉ፡፡ ስለሆነም በቀን ዉስጥ ከ8 እስከ 16 ብርጭቆ ፈሳሽ እንዲጠጡ ከዚያ ዉስጥ ግማሹ ዉሃ ቢሆን ይመከራል፡፡
- ስብ፡- ስብነት/ ጮማነት የበዛበት የእንስሳትም ይሁን የዶሮ እንዲሁም የወተተት ተዋፅኦዎችን አለመመገብ/መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
- ፕሮቲን፡- ከቀይ ስጋ፣ አሳና ከወተት ተዋፅኦ የሚገኘዉን የፕሮቲን መጠን መጥኖ መመገብ (ከ113 እስከ 170 ግራም)፡፡ የሚመገቡት ምግብ ዉስጥ የስብነት ይዘታቸዉ አነስተኛ ወይም ምንም የሌላቸዉ እርጎ ወይም የስብነት መጠኑ የቀነሱ መተቶች/ skim milk/መጠቀም፡፡
ለተወሰኑ ምግቦች ወይም ምግብ ዉስጥ ለሚጨመሩ ነገሮች የሚመከሩ
- ከፍተኛ ፕዩሪን ያላቸዉ አታክልቶች/ High-purine vegetables:- ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከፍተኛ ፕዩሪን ያላቸዉ እንደ ቆስጣ፣የአበባ ጎመንና መሽሩም ያሉ ምግቦችን መመገብ የሪህ ህመም ተጋላጭነትንና መከሰትን አይጨምሩም/አያመጡም ፡፡ በተጨማሪም ባቄላ ወይም የአበባ እህሎች መካከለኛ የፒዩሪን መጠን ግን ጥሩ የፕሮቲን ምንጮች ስለሆኑ መመገብ ይችላሉ፡፡
- ከአካላት/ኦርጋን ወይም ግላንዲዉላር ስጋ/፡- ከፍተኛ ፕዩሪን ያላቸዉና የደምን የዩሪክ አሲድ መጠን የሚጨምሩ እንደ ጉበት፣ኩላሊት፣ጣፊያና የበግ አንጎል የመሳሰሉ ምግቦችን ያለመመገብ
- መጠጥ/አልኮሆል፡- አልኮሆል የዩሪክ አሲድ መመረትን ይጨምራል፤የሰዉነትን የፈሳሽ ምጣኔን ያዛባል፡፡ ስለሆነም አልኮሆል ያለመጠጣት፡፡ ለምሳሌ ቢራ ለሪህ ህመም በተደጋጋሚ መከሰት ምክንት ሊሆን ይችላል፡፡
- ቡና፡- አንዳንድ ጥናቶች እንዳሳዩት ቡናን በመጠኑ መጠጣት የሪህ ህመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ያሳያል፡፡ ነገር ግን ቡና ሲጠጡ ከሌሎች ህመሞች ጋር ያለዉን ሁኔታ አመዘዝነዉ መሆን አለበት
- የተወሰኑ የባህር ምግቦች፡- እንደ ሰርዲንና ቱና ያሉ ምግቦችን ያለመመገብ
- ፕሪም፡- ፕሪም መመገብ ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን እንደሚቀንሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
Related Posts
-
የእርግዝና ክፍለጊዜዎች/ወቅቶች (Pregnancy by Trimester)
ጤናማ እርግዝና፡-ነፍሰጡር መሆንዎን ሲያዉቁ ስለእርግዝናዎ በየሳምንቱ እቅድ ማዉጣት ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ከእርግዝናዎ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ምን አይነት…
-
ለጥርስ ህመም- የመጀመሪያ እርዳታ
እርስዎ በቤቶ ሊተገብሩት የሚችሉ ምክሮች• ሞቅ ባለ ዉሀ አፍዎትን መጉመጥምጥ• በጥርስ መጎርጎሪያ በጥርስዎት መካካል የቀሩ…
-
የግብረ ስጋ ግንኙነት ሳያደርጉ/ሳይፈፅሙ ሊተላለፉ የሚችሉ የአባለዘር ህመሞች
አንዳንድ ህመሞች ያለግብረስጋ ግንኙነት ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ 1. ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ፡-ይህ ቫይረስ በቆዳ ለቆዳ…