ጤናማ እርግዝና፡-
ነፍሰጡር መሆንዎን ሲያዉቁ ስለእርግዝናዎ በየሳምንቱ እቅድ ማዉጣት ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ከእርግዝናዎ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ምን አይነት ምግብ መዉሰድ እንዳለብዎና እንደሌለብዎ፣ስለየአካል እንቅስቃሴና የግብረስጋ ግንኙነትም ሆነ ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
የመጀመሪያዉ የእርግዝና ክፍለ ጊዜ (First trimester) ፡-
ይህ የመጀመሪያዎቹን 14 ሳምንታት የእርግዝና ወቅቶች የያዘ ሲሆን በእርስዎና በፅንሱ ላይ ፈጣን የሆኑ ለዉጦች የሚታዩበት ወቅት ነዉ፡፡በዚህ ጊዜ
• በእርስዎ ላይ፡- የጡት ላይ ህመም፣ድካም፤ ማቅለሽለሽ ያሉ አካላዊ ለዉጦችና ከደስታ እስከ መጨናነቅ ሊደርሱ የሚችሉ የስሜት መለዋወጦች ሊታዩ ይችላሉ፡፡
• በፅንሱ ላይ፡- ይህ ክፈለ ጊዜ ፅንሱ በፍጥነት የሚያድግበትና የሚጎለብትበት ወቅት ነዉ፡፡የፅንሱ አእምሮ፣ህብለሰረሰርና ሌሎች አካላቶች ይፈጠራሉ፤ እንዲሁም የፅንሱ ልብ መምታት ትጀምራለች፡፡
ስለሆነም በመጀመሪያዉ የእርግዝና ክፍለጊዜዎ የቅድመወሊድ ክትትል ለመጀመር የህክምና ባለሙያዎ ጋር መሄድ ይገባዎታል፡፡ በክትትልዎ ወቅት ምን ነገሮችን በዚህ ወቅትና ለወደፊቱ መተግበር እንደሚገባዎ ለመረዳት ይረዳዎታል፡፡
ሁለተኛዉ የእርግዝና ክፍለጊዜ፡-
ይህ ከ14ኛዉ እስከ 28ኛዉ ሳምንት ያለዉ የእርግዝናዎ ወቅት ሲሆን በዚህ ጊዜ ከመጀመሪያዉ የእርግዝና ክፍለጊዜ ይልቅ መልካም ጤንነት ስለሚሰማዎ እርግዝናዎን የሚያጣጥሙበት ወቅት ነዉ፡፡
• በእርስዎ ላይ የሚታይ፡-እርግዝናዎ በደንብ የሚያስታዉቅበት ጊዜ ሲሆን የጡት መጠን መጨመር የሆድ መግፋትና የቆዳ ላይ ለዉጦች የሚታዩበት ጊዜ ነዉ፡
፡
• በፅንሱ ላይ፡- 20ኛዉ ሳምንት የእርግዝናዎ እኩሌታ ሲሆን በዚህ የእርግዝና ክፍለጊዜ ፅንሱ መገለባበጥና መስማት ይችላል፡፡
ሶስተኛዉ የህክምና ክፍለጊዜ፡-
ይህ የመጨረሻዉ የህክምና ክፍለጊዜ ከ28ኛዉ እስከ 40ኛዉ ሳምንታት ድረስ ያለዉ ሲሆን ፈታኝ የሆኑ አካላዊና ስነልቦናዊ ጫናዎች የሚታዩበት ነዉ፡፡ በዚህን ጊዜ የጀርባ ህመም፣የእግር እብጠት መጨናነቅ ሊመጣ ይችላል፡፡
• በፅንሱ ላይ፡- አይኑን መክፈትና መዝጋት ይችላል፤ክብደት ይጨምራል፡፡ ፈጣን የሆነ እድገት ስላለዉ እንቅስቃሴ እንዲጨምር ሊያደርገዉ ይችላል፡፡ 39ኛዉን ሳምንት ላይ ልጁ ሙሉ በሙሉ ያደገ ነዉ፡፡
• በእርስዎ ላይ፡-በዚህ የእርግዝና ክፍለጊዜ በመደበኛ ሁኔታ ክትትልዎን መቀጠል፡፡ የህክምና ባለሙያዎ የፅንሱን አቀማመጥ፣የማህፀን አንገት ለዉጦችንንና የመሳሰሉትን ይመረምራሉ፡፡ እርስዎም የመዉለጃ ወቅትዎ እየተቃረበ ስለሆነ መጠየቅ ያለብዎን ሁሉ መጠየቅ ይገባዎታል፡፡
Related Posts
-
የጉበት ላይ ስብነት (ፋቲ ሊቨር)
ከአልኮልነት ጋር ያልተያያዘ የጉበት ላይ ስብ ማለት በጣም ትንሽ ወይም ምንም አይነት አልኮሆል ሳይጠቀሙ/ሳይጠጡ በጉበት…
-
ለጥርስ ህመም- የመጀመሪያ እርዳታ
እርስዎ በቤቶ ሊተገብሩት የሚችሉ ምክሮች• ሞቅ ባለ ዉሀ አፍዎትን መጉመጥምጥ• በጥርስ መጎርጎሪያ በጥርስዎት መካካል የቀሩ…
-
የግብረ ስጋ ግንኙነት ሳያደርጉ/ሳይፈፅሙ ሊተላለፉ የሚችሉ የአባለዘር ህመሞች
አንዳንድ ህመሞች ያለግብረስጋ ግንኙነት ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ 1. ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ፡-ይህ ቫይረስ በቆዳ ለቆዳ…