Posted by hellodoc on
አንዳንድ ህመሞች ያለግብረስጋ ግንኙነት ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡
1. ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ፡-
ይህ ቫይረስ በቆዳ ለቆዳ ንኪኪ ኣማካይነት ሊተላለፍ የሚችል ሲሆን በእርግዝናና ወሊድና በጡት ማጥባት ወቅት ከእናት ወደ ልጅ፣በግብረስጋ ግኑነት ወቅት የአካል ንኪኪ በሚኖርበት ሊተላለፍ ይችላል፡፡ይህ ቫይረስ የብልት አካባቢ ቁስለት/ዋርትና ቅድመካንሰር ችግሮችን ያመጣል፡፡
2. ሞሊዩስከም ኮንታጅዮሰም፡-
ይህ ቀይ፣ ህመም የሌለዉ፣ መሃሉ ክፍት የሆነ ትንንሽ የቆዳ ላይ ችግሮች ከሰዉ ወደ ሰዉ በቆዳ ለቆዳ ንኪኪ(በመጨባበጥ፣በመተቃቀፍ) የሚተላለፉ ናቸዉ፡፡ሞሊዩስከም በራሱ ሰዓት ሊድን የሚችል ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መድሃኒት መዉሰድ ይቻላል፡፡
3. ሀርፐስ፡-
ሀርፐስ በመሳሳም፣ህመምተኛዉ የተጠቀመበትን የመመገቢያ እቃዎችን በመጠቀምና እንዲሁም በመላጫ እቃዎች ሊዛመት ይችላል፡፡ሁለት አይነት ሀርፐስ ቫይረሶች አሉ-ሀርፐስ ታይፕ 1 እና ታይፕ 2.
Related Posts
-
የወንዶች የወሲብ ችግር( sexual dysfunction)
የብልት ያለመቆም ችግር( Erectile dysfunction)የብልት ያለመቆም ችግር አለ የምንለዉ የወንድ ብልት ለግብረ ስጋ ግንኙነት ሲዘጋጅ…
-
የጉበት ላይ ስብነት (ፋቲ ሊቨር)
ከአልኮልነት ጋር ያልተያያዘ የጉበት ላይ ስብ ማለት በጣም ትንሽ ወይም ምንም አይነት አልኮሆል ሳይጠቀሙ/ሳይጠጡ በጉበት…
-
ሄፓታይትስ ሲ/ Hepatitis C
ሄፓታይትስ ሲ የጉበት ህመምን ከሚያመጡ የጉበት ቫይረስ አይነቶች አንዱ ሲሆን በጉበት ላይ በአጭር ጊዜ ምልክት…