ሄፓታይትስ ሲ/ Hepatitis C

ሄፓታይትስ ሲ የጉበት ህመምን ከሚያመጡ የጉበት ቫይረስ አይነቶች አንዱ ሲሆን በጉበት ላይ በአጭር ጊዜ ምልክት የሚያሳይ ወይም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጉበት ላይ እንፌክሽን እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ የሚከሰተዉ ህመም አጭር ጊዜ/ለሳምንታት ከሚቆይ መጠነኛ ደረጃ እሰከ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅና በጉበት ለይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ህመም ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡ እስከአሁን ድረስ በአለማችን ሄፓታይትስ ሲን የሚከላከል ክትባት የሌለ ሲሆን ጥናቶች ግን እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በሄፓታይትስ ሲ ቫይረተስ ከተጠቁ ሰዎች ዉስጥ ከ15 እስከ 45 በመቶ የሚሆኑት ቫይረሱን በ6 ወራት ዉስጥ ከሰዉነታቸዉ  ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ የሚጠፋ/የሚድን ሲሆን ከ 55-85 በመቶ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ግን ቫይረሱ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጉበት ላይ እንፌክሽን/ chronic HCV infection/ እንዲከሰት ያደርጋል፡፡

 

መተላለፊያ መንገዶች

·         አደንዛዥ እፅ የሚጠቀሙ ሰዎች የሚወጉበትን መርፌ በጋራ ሲጠቀሙ

·         ያልተመረመረ የደምና የደም ተዋፅኦን መዉሰድ

·         በመጠነኛ ደረጃ ቢሆንም በግብረ ስጋ ግነኙነትና ከእናት ወደ ልጅ ይተላለፋል፡፡

 

የማይተላለፍባቸዉ መንገዶች፡-

በጡት ወተት፣በምግብ፣ በዉሃና በማህበራዊ መስተጋብር ግንኙነቶች ( መተቃቀፍ፣ መሳሳምና ምግብ አብሮ በመብላት)

 

የህመሙ ምልክቶች

እንፌክሽኑ ከተከሰተ በኃላ እስከ 80 በመቶ የሚደርሱ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክት ላይኖራቸዉ ይችላል፡፡ የህመም ምልክቶች ከተከሰቱ ደግሞ እንደ ትኩሳት፣፣ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣የሆድ ህመም፣ የሽንት ወደ ኮካኮላነት መልክ መቀየር፣የመገጣጠሚያ ላይ ህመምና የአይንና የቆዳ ወደ ቢጫነት መቀየር ናቸዉ፡፡

 

ምርመራዎች

ምርመራን በጊዜዉ/በወቅቱ ማድረግ በእንፌክሽኑ ምክንያት ሊደርሱ የሚችሉ የጤና ችግሮችንና የህመሙን ከአንዱ ወደ ሌላዉ የመተላለፍ እድልን መቀነስ ይቻላል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት ለህመሙ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡ እነርሱም

·         አደንዛዥ እፅ የሚወጉ ሰዎች

·         የደምና የደም ተዋፅኦዎችን የሚወስዱ ሰዎች

·         በሄታይትስ ሲ ከተያዘች እናት የሚወለዱ ህፃናት

·         የፍቅር/የትዳር ጓደኛቸዉ ሄፓታይትስ ሲ የተያዙ ሰዎች

·         የኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸዉ ያለ ሰዎች

·         ከዚህ በፊት ንቅሳት የተደረገላቸዉ/የነበራቸዉ ሰዎች ናቸዉ፡፡

 

ሊደረግ የሚችል ህክምና

የሄፓታይትስ ሲ እንፌክሽን አለማለት ሁሌ ህክምና ያስፈልገዋል ማለት አይደለም፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የበሽታ መከላከል ስርዓታቸዉ እንፌክሽኑን ከሰዉነታች በራሱ ጊዜ እንዲድን/እንዲጠፋ ሊደርግ ይችላል፡፡ በሌሎች አንዳንድ ሰዎች ላይ  ደግሞ ምንም እንኳ ለረጅም ጊዜ የቆየ የጉበት ላይ እንፌክሽን ቢኖራቸዉም ጉበት ላይ የከፋ ጉዳት ላይከሰት ይችላል፡፡ ህመሙ ለመዳን ብዙ የሚወስኑት ነገሮች ቢኖሩም የቫይረሱ ስትሬይን (አይነትና) የሚሰጠዉ የህክምና አይነት ግን ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡

Comments

comments