Posted by hellodoc on
ከአልኮልነት ጋር ያልተያያዘ የጉበት ላይ ስብ ማለት በጣም ትንሽ ወይም ምንም አይነት አልኮሆል ሳይጠቀሙ/ሳይጠጡ በጉበት ላይ የስብ መጠራቀም ችግር በሚከሰትበት ወቅት ነዉ፡፡
የህመሙ ምልክቶች
ችግሩ ምንም የህመም ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ነገር ግን የህመም ምልክቶች ከታዩ የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
- የሰዉነት ድካም
- በቀኝ የላይኛዉ የሆድ ክፍል ህመም መሰማት
- የክብደት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
የህመሙ ምክንያቶች
የጉበት ላይ ስብ መጠራቀም የሚከሰተዉ ጉበት ስብን ለመሰባበር በሚየደርገዉ ሂደት ላይ ችግር ሲገጥመዉ ሲሆን ይህ ክስተት ስብ በጉበት ላይ እንዲጠራቀም ያደርገዋል፡፡
ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች
- የሰዉነት የኮለስትሮል መጨመር
- በደም ዉስጥ ያለዉ የትራይግላይስራድ ስብ መጠን መጨመር
- ሜታቦሊክ ሲንድረም
- ዉፍረት
- ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም የሚባለዉ የጤና ችግር ሲኖር
- ስሊፕ አፕኒያ( ከእንቅልፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ችግሮች)
- የስኳር ህመም ሲኖር
- የታይሮይድ ችግር ሲኖርና የመሳሰሉት ናቸዉ፡
Related Posts
-
ፎረፎር
የተከበራችሁ ወዳጆቻችን፤ በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ ብዙዎቻችሁ ስለፎረፎር መረጃ እንድንሰጣችሁ አስተያየቶቻችሁን ኢንቦክስ ባደረጋችሁልን መሰረት በፎረፎር…
- የቅድመ ወሊድ ክትትል
የቅድመ ወሊድ ክትትልማንኛዋም ነፍሰጡር እናት ነፍሰጡር መሆንዋን ካወቀችበት ጊዜ አንስቶ የቅድመ ወሊድ ህክምና ክትትል መጀመር…