ብጉር (Acne)

ብጉር በሰዉነት ቆዳ ላይ የሚከሰት ችግር ሲሆን የላብ መዉጪያ ቀዳዳዎች( hair follicles) በስብ፣ በሞቱ የቆዳ ሴሎችና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በባክቴሪያዎች በሚደፈንበት ወቅት የሚመጣ ነዉ፡፡

ብጉር በብዛት የሚከሰተዉ በጣም ብዙ የሆኑ የስብ አመንጪ ዕጢዎች በብዛት የሚገኝባቸዉ የቆዳ ክፍሎች ባሉበት የሰዉነት ክፍሎች እንደ ፊት፣አንገት፣ደረት፣ጀርባና ትከሻ ያሉ ቦታዎች ላይ ነዉ፡፡ ብጉር ከሰዉነት ላይ ሳይጠፋ በሚቆይበትና ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ያለ ከሆነ እንደ እፍረትና መንፈስ ጭንቀትን የመሳሰሉ ስነልቦናዊ ጉዳቶችንና የቆዳ ጠባሳን ሊያመጣ ስለሚችል እነዚህ ነገሮች የተጎጂዉን ማህበረዊና የስራ ቦታ ጫናን ሊያመጣ ይችላል፡፡ብጉር ጥሩ የሆነ ህክምና ያለዉ ሲሆን በወቅቱ ከታከመ የሚያመጣዉን የአካልና መንፈስ ጉዳት መቀነስ ይቻላል፡፡

 

ለብጉር መከሰት ምክንያቶች ምንድናቸዉ

· የስብ ከመጠን በላይ መመረት

· የሞቱ የቆዳ ሴሎች በአግባቡ ያለመወገድ( Irregular shedding of dead skin cells)
· የባክቴሪያዎች መራባት(መጠራቀም)

 

ለብጉር ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች( Risk factors)


· ለሰዉነት ሆርሞን መለዋወጥ ምክንት የሆኑ ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት፡-ጉርምስና፣እርግዝና፣የሴቶች የወር አባበ ዑደት ከመከሰቱ ከ 2 እስከ 5 ቀናት በፊት ያሉ ቀናት፣የተወሰኑ መድሃኖቶችን የሚወስዱ ሰዎች(አንድሮጅን፣ሊትየምና እስቴሮይድ)

· በቆዳ ላይ የሚቀቡ ዘይትነት ወይም ግሪሲ የሆኑ ነገሮች( greasy or oily substances) ወይም የተወሰኑ የመዋቢያ ቅባቶች(ኮስሞቲክሶች)

· በቤተሰብ ዉስጥ የሚከሰት

· በቆዳ ላይ ፍትጊያና ግፊት የሚያሳድሩ ነገሮች፡-ሄልሜንት፣ስልክ፣ጥብቅ ያሉ አልባሳት

ብጉርን የሚያባብሱ ነገሮች(Agravating factors)

· ሆርሞኖች፡-ለምሳሌ በጉርምስና ወቅት አንድሮጂን፣እርግዝና፣ብጉር እያለ የተወሰኑ መድሃኒቶችን መዉሰድ፡-አንድሮጅን፣ሊትየምና እስቴሮይድ

· የተወሰኑ ምግቦች፡-የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን እንዲሁም ሃይልሰጪ በብዛት ያላቸዉ ምግቦችን መጠቀም (dairy products and carbohydrate-rich foods)

· ጭንቀት( Stress)


የብጉር ህክምና


የብጉር ህክምና የስብ መመረትን በመቀነስ፣የቆዳ ሴሎች ቶሎ ቶሎ እንዲቀያየሩ በማድረግ፣የባክቴሪያ ኢንፌክሽንን በመቀነስና የቆዳ መቆጣትን በመቀነስ የሚሰራ ሲሆን በህክምናዉ ጥሩ ዉጤት ሳያዩ ከ4 እስከ 8 ሳምንታት ሊቆዩ ስለሚችሉ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ መድሃኒቶቹን በአግባቡ እየወሰዱ ብጉሩ ሊባባስ ስለሚችል ህክምናዎትን ሳያsርጡ በትዕግስት መከታተል ያስገልጋል፡፡ለብጉር ህክምና የሚረዱ የተለያዩ መዱሃኒቶች ያሉ ሲሆን እነሱም በቆዳ ላይ የሚቀቡ፣የሚዋጡ አንቲባዮትክሶች እንዲሁም ሌዘርና ላይት ቴራፒ የሚባሉ ዘዴዎች ያሉ ሲሆን የትኛዉን መንገድ መጠቀም እንደሚሻል ለመወሰን የቆዳ እስፔሻሊስት ሀኪሞችን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

በብጉር ምክንያት የሚከሰተዉን የቆዳ ላይ ጠባሳም ቢሆን የራሱ የሆነ የተለያዩ ህክምናዎች ያሉት ስለሆነ ለዚህም የቆዳ እስፔሻሊስት ሀኪሞችን ማማከር ያስፈልጋል

 


ብጉርን እንዴት መከላከል ይቻላል


· ለብጉር ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መታጠብ፡-ይህ ከመጠን በላይ የሆነዉን የቆዳ ቅባትና የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ያስወግዳል፡፡ከመጠን ያለፈ መታጠብ ቆዳዎትን ስለሚቆጠቁጥና ለብኩር ስለሚያጋልጥዎ ይህን ከማድረግ ይቆጠቡ

· ከመጠን ያለፈ ፋዉንዴሽን ሜካፕ ያለመጠቀም፡- ከክሬምነት ይልቅ ፓዉደር ኮስሞቲክሶችን ይምረጡ፡፡ምክንቱም ፓዉደር ኮስሞቲክስ ከክሬም አንፃር ሲታዩ ቆዳን እምብዛም አይቆጠቁጡም

· ከመተኛትዎ በፊት ሜክአፕ ተቀብተዉ ከሆነ ማስወገድ/መታጠብ፡-በቆዳ ላይ ከነተቀባዉ ኮስሞትክሰዎ መተኛት የላብ መዉጪ ቀዳዳዎችን ስለሚደፍነዉ ለብጉር መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡የሜካፕ መቀቢያ ብሩሾችም በየጊዜዉ በዉሀና ሳሙና መታጠብ አለባቸዉ፡፡

· ለቀቅ ያሉ ልብሶችን መልበስ፡-ጥብቅ ያሉ ልብሶችን መልበስ ሙቀትንና እርጥበትን ስለሚይዝ ለሰዉነት መቆጣት ምክንያት ይሆናሉ፡፡ሄልሜንቶች፣የስፖርት አልባሳትም ቢሆኑ ከሰዉነት ጋር ያላቸዉን ፍትግያ ለመቀነስ ከተቻለ በጣም ጥብቅ ያሉ መሆን የለባቸዉም፡፡

· ከበድ ያለ ስራ ወይም የአካል እንቅስቃሴ ካደረጉ በኃላ ሰዉነትን መታጠብ፡-የሰዉነት ላብና ስብ ቆሻሻንና ባክቴሪያዎችን ስለሚስቡ ሻወር መዉሰድዎትን አይርሱ፡፡

· በሰዉነት ላይ ያለዉን ከመጠን ያለፈ ቅባት ለማድረቅ ያለሀኪም ትእዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ ወይም ሳሊሲሊክ አሲድን ያያዙ የብጉር ክሬም ወይም ጄል መጠቀም

 

Comments

comments