ከመጠን በላይ የሆነ ላብ ማላብ ሀይፐርሀይድሮስስ ይባላል፡፡
ሀይፐርሀይድሮስስ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ በእጅ መዳፍ፤በእግር መዳፍ(የዉስጥ እግር)ና ብብት ዉስጥ ሲሆን እንደ ጤና ችግር የሚቆጠረዉ የእረስዎን የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን የሚያስተጓጉል ከሆነ ነዉ፡፡ ሀይፐርሀይድሮስስ የእለት ከዕለት እንቅስቃሴዎትን ከማስተጓጎሉም በተጨማሪ ማህበራዊ ጭንቀትንና እፍረትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
ሃኪሞትን ማማከር የሚገባዎት መቼ ነዉ?
• ላቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን ካስተስጓጎሎት
• ያልተለመደ ከበፊቱ የተለየ ብዙ የሚያልቦት ከሆነ
• ምክንያቱን ያላወቁት ማታ ማታ ላብ ካለዎት
ይኸንን ችግር ለማሻሻል ከሚረዱ ዘዴዎች ዋነኛዉ የላብን መመረት የሚቀንሱ መድሀኒቶችን መጠቀም ሲሆን ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ከሆነ ደግሞ ላብን ከመጠን በላይ የሚያመርቱትን የላብ ዕጢዎች ወይም ወደ ላብ ዕጢዎች የሚሄዱትን ነርቮች በቀዶጥገና እንዲስተካከል ማድረግ ይቻላል፡፡
አጠቃላይ ምክሮች
• በየቀኑ መታጠብ፡ ይህን ማድረግዎ በሰዉነትዎ ላይ ያሉትን የባክቴሪያ መጠን ይቀንሳል
• ሻወር ከወሰዱ በኃላ እግሮትን በደንብ ማድረቅ፡ በጣትዎት መካከል በደንብ ማድረቅ፤ፓዉደር መጠቀም
• የሚጠቀሙትን ጫማና ካልሲ መምረጥ፡ ጫማዎትንና የጫማዎትን ሶል ከቆዳ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል
• ጫማዎትን መቀያየር፡ አንድን ጫማ ከሁለት ቀን በላይ ያለማድረግ
• የሚጠቀሙት ካልሲ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከጥጥ ወይም ከሱፍ የተሰሩ ካልሲዎች እርጥበትን የመምጠጥ ባህሪይ ያላቸዉ ሲሆን እንቅስቃሴ በጣም በሚያበዙበት ወቅት ደግሞ እርጥበትን በደንብ ሊመጡ የሚችሉ የአትሌት ካልሲ የሚባሉትን መጠቀም ይመረጣል
• እግሮት አየር እንዲያገኝ ማድረግ፡ በሚመቾት ሰዓት እግሮትን ከጫማ ማዉጣትና ማናፈስ፤እቤት ዉስጥ ደግሞ ባዶ እግር ወይም ነጠላ ጫማ ማድረግ
• ከጥጥ፤ ሱፍ ወይም ናይለን የተሰሩ ልብሶችን ማዘዉተር፡ እነዚህ አየር በደንብ እንዲዘዋወር ያደርጋሉ
Related Posts
-
የማህፀን አንገት ካንሰር/ cervical cancer
የማህፀን አንገት ካንሰር ከማህፀን አንገት ሴሎች የሚነሳ የካንሰር አይነት ነዉ፡፡ ለብዙዎቹ የማህፀን አንገት ካንሰር መከሰት…
-
ልጅዎ የአምስት አመት እድሜ ሳለ
ከዚህ በፊት የህፃን ልጅዎን የአጨዋወት፣ አነጋገር/ ቋንቋ፣ እንዴት እንደሚማር እና እንቅስቃሴዎችን እንዴት እንደሚተገብር በመከታተል ስለልጅዎ…
-
ለአዳዲስ ወላጆች ስለ ጨቅላ ህፃናት አመጋገብ ምክር
ጨቅላ ህፃንዎን መመገብ ያለማቛረጥ የሚደረግ ሃላፊነት ነዉ፡፡ አዲስ ከመጣዉ የቤተሰብ አባልዎ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመመስረት…