ልጅዎ የአምስት አመት እድሜ ሳለ

10611899_m

ከዚህ በፊት የህፃን ልጅዎን የአጨዋወት፣ አነጋገር/ ቋንቋ፣ እንዴት እንደሚማር እና እንቅስቃሴዎችን እንዴት እንደሚተገብር በመከታተል ስለልጅዎ የእድገት ሁኔታ ፍንጭ ማግኘት እንደሚቻልና የአራት ዓመት ህፃን ሊያሳይ የሚችላዉን ነገሮች መነጋገራችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዚያ የቀጠለ የአምስት አመት ልጅ የእድገት ክትትልን እናያለን፡፡

 

አብዛኞቹ ህፃናት በዚህ እድሜ ምን ምን ነገሮችን ይተገብራሉ?

ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional

  • እንደጓደኛ መሆን ይፈልጋሉ
  • በህግ/በደንብ መስማማት ይችላሉ/ ደንብ ያከብራሉ
  • መዝፈን፣ መደነስና መተወን ይወዳሉ
  • ለሌሎች መጨነቅና ማዝንን ያሳያሉ
  • ስለ ፆታ ልዩነት ያዉቃሉ
  • ምን ሊያሳምን እንደሚችልና ምን ትክክል እንደሆነ መናገር ይችላሉ
  • በራስ መተማመንን ያሳያሉ( ለምሳሌ ሳይፈሩ ጎረቤት ብቻቸዉን መሄድ) ይችላሉ፡፡
  • አንዳንዴ በጣም አስቸጋሪ ይሆናሉ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተባባሪ

ቋንቋ /መግባባት (Language/Communication)

  • ጥርት አድርገዉ ማዉራት ይችላሉ
  • ሙሉ አረፍተነገር በመጠቀም ተረት/ታሪክ መንገር ይችላሉ
  • ወደ ፊት የሚመጣዉን ድርጊት ቃላት/ future tense/ መጠቀም ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ አክስቴ ነገ/በኃላ ትመጣለች ብለዉ ቃላትን በአግባቡ ተጠቅመዉ መናገር ይችላሉ
  • ስምና አድራሻን መናገር ይችላሉ፡፡

አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና  ችግርን መፍታት መቻል)

  • አስርና ከዚያ በላይ የሆኑ እቃዎችን/ ነገሮችን መቁጠር መቻል
  • አንድን ሰዉ ስድስት የሰዉነት ክፍሎችን በማካተት መሳል ይችላሉ
  • የተወሰኑ ፊደላትን/ቁጥሮችን መፃፍ ይችላሉ
  • ትሪያንግል ወይም ሌሎች የጂኦሜትሪ ቅርፆችን ኮፒ ማድረግ ይችላሉ
  • በየቀኑ የምንጠቀምባቸዉን ነገሮች መረዳት/ማወቅ ይችላሉ፡ ለምሳሌ ገንዘብ፣ ምግብ

እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development

  • በሁለት እግር መዝለል መቻል
  • በሹካ/ማንኪያ መጠቀም መቻል
  • ሶፋ/ምንጣፍ ላይ ወደፊት መገለባበጥ መቻል
  • ራሳቸዉን ችለዉ መፀዳጃ ቤት መጠቀም መቻል
  • ዥዋዥዌ መጫወትና መሰላል/ሌሎች ነገሮች ላይ መዉጣት መቻል ናቸዉ፡፡

Comments

comments