ጉንፋን

21870470_m

ጉንፋን የላይኛው የመተንፈሻ አካልን (አፍንጫን፣ጉሮሮሮንና ሳንባን) የሚያጠቃ በቫይረስ ኢንፌክሽን አማካይነት የሚመጣ የህመም አይነት ነዉ፡፡ ከአምስት አመት በታች በተለይ ደግሞ ከ 2 አመት በታች ያሉ ህፃናት፣ነፍሰጡር እናቶችና የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ የተዳከመ ሰዎች ለህመሙ በብዛት የተጋለጡ ናቸዉ፡፡

 

የህመሙ ምልክቶች

በብዛት የሚከሰቱት የህመም ምልክቶች

  • ትኩሳት
  • የጡንቻ ላይ ህመም በተለይ የጀርባ፣ እጅና እግር ላይ
  • ብርድ ብርድ ማለትና ማላብ
  • የራስ ምታት
  • ተከታታይነት ያለዉ ደረቅ ሳል
  • የአፍንጫ መጠቅጠቅና
  • የጉሮሮ መከርከር/ህመም ናቸዉ፡፡

 

እንዴት ሊተላለፍ ይችላል

ጉንፋንን የሚያመጣዉ ቫይረስ ታማሚዉ በሚያስነጥስበት፣ በሚያወራበትና በሚያስልበት ወቅት በአየር ዉስጥ በቅንጣቢ/በድሮፕሌት መልክ ይጓዛል፡፡ጤነኛዉ ሰዉ ይህን አየር ወደዉስጥ በሚስብበት/በሚተነፍስበት ወቅት ይኸንን ድሮፕሌት ወደ ዉስጥ ያስገባል፡፡

በተጨማሪም ታማሚዉ የነካቻቸዉ እቃዎች ካሉ ለምሳሌ የበር እጀታ፣ ጠረንጴዛ፣ስልክ፣ የኮምፒዩተር ፣  የመሳሰሉትን ነክቶ ጤነኛዉ ሰዉ ቢነካቸዉ እንዲሁም እጅ ለእጅ ከተጨባበጡ በኃላ ጤነኛዉ ሰዉ አይኑን፣ አፍንጫዉንና አፉን ቢነካ ቀጥታ ቫይረሱ ሊተላለፍበት ይችላል፡፡በጉንፋን ህመም የተያዙ ሰዎች ቫይረሱን የበሽታዉ ምልክቶች ከመታየታቸዉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ወይም የህመም ምልክቶቹ ከታዩበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ቫይረሱን ወደ ጤነኛዉ ሰዉ ሊያስተላልፉ ይችላሉ    (ምንም እንኳ አንዳንዴ  የህመሙ ምልክቶች መታየት ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ባሉት10 ቀናት ዉስጥ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ የሚችሉ ሰዎች ቢኖሩም)፡፡

 

ህመሙን እንዴት ማከም ይቻላል

አብዛኛዉ የጉንፋን ህመም ያላቸዉ ሰዎች የህክምና ባለሙያ ማየት ሳያስፈልጋቸዉ በቤታቸዉ ሆነዉ እራሳቸዉን ማከም ይችላሉ፡፡

 

የቤት ዉስጥ ህክምና

  • ፈሳሽ በብዛት መጠጣት (የአልኮል መጠጥን አይጨምርም)፡-

    ዉሃ፣ ጁስ/የፍራፍሬ ጭማቂና ሞቅ ያለ ሾርባ በብዛት መዉሰድ የሚከሰትብዎንየፈሳሽ እጥረት ለመከላከል ይረዳል፡፡

  • በቂ እረፍት ማድረግ፡-

    የበሽታ መከላከል አቅምዎን ለማጎልበትና ቫይረሱን መዋጋት እንዲችሉ በቂ እንቅልፍ ያግኙ፡፡

  • የህመም ማስታገሻ፡-  

    ያለሃኪም ትእዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንደ ፓራስታሞል ያሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን መዉሰድ

  • እንፋሎት መታጠን/መማግ፡- ፎጣ/ማንኛዉንም ነገር ጭንቅላትዎ ላይ በመሸፈን እየፈላ ባለ ዉሃ እንፋሎቱን መታጠን፡፡ ይህ የመቆጥቆጥና የአፍንጫ መጠቅጠቅ ስሜቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

 

Recent Posts

Comments

comments