የአጠቃቀም ሁኔታ፡-
የወሊድ መከላከያ እንክብሎች አስተማማኝና የማይጎዱ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዴትና መቼ እንደሚወሰዱ እና ምን አይነት ዉጤት እንደሚኖራቸዉ/እንደሚጠበቅ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
• መድሃኒቶቹን መዉሰድ በጀመሩ በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የማቅለሽለሽ ስሜቶችን ለመቀነስ/ለመከላከል እንክብሎችን ከምግብ ጋር መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡መድሃኒቱን በመኝታ ሰዓት አሊያም በተከታታይነት ከወሰዱ የማቅለሽለሽ ስሜቶቹ ይጠፋሉ፡፡
• የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን መዉሰድ ሲጀምሩ ሰዉነትዎ እስኪለማመድ ድረስ መድሃኒቶቹ ለመስራት 7 ቀናት ይፈልጋል/ያስፈልጋል፡፡ስለሆነም ለመጀመሪያዎቹ 7 ቀናት ተጨማሪ/ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል( ለምሳሌ ኮንደም)፡፡
• በመድሃኒቶቹ ምክንያት የሚከሰትን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስና እርግዝናን ለመከላከል እንክብሎቹ መወሰድ ያለባቸዉ 24 ሰዓታት ባልበለጠ ልዩነት መሆን አለበት፡፡
• መድሃኒቶቹን በመጀመሪያዉ የማስቀመጫ ስፍራ/እቃ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፤ መድሃኒቶቹም መወሰድ ያለባቸዉ መያዣዉ ላይ በተቀመጠዉ ትዕዛዝ መሰረት መሆን አለበት፡፡
እንክብል ሳይወስዱ ቢረሱ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
• አዲስ እየጀመሩ ካለዉ ዉስጥ የመጀመሪያዋን እንክብልና አንድ እንክብል ከመሃሉ ቢረሱ፡-
የረሱትን እንክብል ባስታወሱበት ሰዓት መዉሰድና ቀጣዩን በመደበኛ ሰዓቱ መዉሰድ፡፡ በቀን ዉስጥ ሁለት እንክብል በአንዴ መዉሰድ ይቻላል፡፡ከዚያን ቀሪዉን መደበኛዉን ጊዜ ተከትሎ መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡ መድሃኒቱን መዉሰድ ከጀመሩ ለ7 ቀናት ያህል ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ (ለምሳሌ ኮንደም) መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
• የወሊድ መከላከያ እንክብል መዉሰድ በጀመሩ የመጀመሪያዉ ወይም ሁለተኛዉ ሳምንት ዉስጥ በተከታታይ ሁለት እንክብል መዉሰድ ቢረሱ፡-
ባስታወሱበት ቀን 2 እንክብሎችን በሚቀጥለዉ ቀን ደግሞ 2 እንክብል መዉሰድ፤ ከዚያን አንድ እንክብል በየቀኑ መቀጠል፡፡ ሌላ አዲስ የወሊድ መከላከያ እስኪጀምሩ ድረስ ሌላ የወሊድ መከላከያ( ለምሳሌ ኮንደም) በተጨማሪነት መጠቀም
• መከላከያ መዉሰድ በጀመሩ በሶስተኛዉ ሳምንት 2 እንክብል በተከታታይነት አሊያም ሶስትና ከዚያን በላይ እንክብሎችን በተከታታይነት በየትኛዉም ወቅት መዉሰድ ቢረሱ:
አሁን እየወሰዱ ያለዉን/መዉሰድ የጀመሩትን ሙሉ በሙሉ ትተዉ አዲስ የወሊድ መከላከያ እንክብል በአዲስ መልክ መጀመር፡፡ አዲስ ከጀመሩት እንክብሎች ለ7 ቀናት መዉሰድ እስኪችሉ ድረስ ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ (ለምሳሌ ኮንደም) በተጨማሪነት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በዚህኛዉ ወቅት የወር አበባ ዑደትዎ ላይኖር ይችላል፡፡ በተከታታይነት ለሁለት ወራት ከሌለ ግን የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ስፈልጋል፡፡
የትኛዉንም ከ28 ቀናት ሳይክል/ዑደት ዉስጥ ከሚወሰዱት የመጨረሻዎቹ 7 እንክብሎች ዉስጥ አንዱን ቢረሱ ሊፈጠር የሚችል የእርግዝና ስጋት የለም፡፡ ነገር ግን የትኛዉም እንክብል ሳይወሰድ ቢቀር፤ የሚቀጥለዉ ወር የመጀመሪያዉ ቀን የወሊድ መከላከያ እንክብል በቀኑ መወሰድ መጀመር አለበት፡፡
እርግዝናን የመከላከል ብቃት ያላቸዉና የሌላቸዉ እንክብሎች በተለያየ ቀለም የተሰሩ ናቸዉ፡፡
Recent Posts
- የታይፎይድ ህመም
- የማስታወስ ችሎታዎን ለማሻሻል የሚመከሩ 7 ምክሮች
- የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን/ Infant jaundice
- የአመት በዓል ጤናና ደህንነት ጥንቃቄ ምክሮች
- የኩላሊት ጠጠር