የታይፎይድ ህመም እያደጉ ባሉ ሃገሮች ዉስጥ በተለይ በህፃናት ላይ ከፍተኛ የጤና ጉዳት ሊያመጣ የሚችል የህመም አይነት ነዉ፡፡ ህመሙ የሚከሰተዉ ሳልሞኔላ ታይፊ በሚባል የባክቴሪ አይነት ሲሆን ህመሙ ከታማሚዉ ሰዉ ወደ ጤነኛዉ ሰዉ በተበከለ ዉሃና ምግብ አማካይነት ይተላለፋል፡፡
የህመሙ ምልክቶች
- ሲጀምር መጠነኛ ሆኖ እያደር እየጨመረ የሚመጣ ትኩሳት
- የራስ ምታት
- መደካከምና የሰዉነት መዛል
- የጡንቻ ላይ ህመም
- ማላብ
- ደረቅ ሳል
- የምግብ ፍላጎት መቀነስና ክብደት መቀነስ
- የሆድ ህመም
- ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት መከሰት
- የሆድ መነፋት የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ሕመሙ የሚተላለፍባቸዉ መንገዶች
የታይፎይድ ህመምን የሚያመጣዉ ባክቴሪያ የሚተላለፈዉ በተበከለ ዉሃ ወይም ምግብና አንዳንዴ ደግሞ ከታመመዉ ሰዉ ጋር በሚኖረን ቀጥተኛ ግንኙነት አማካይነት ነዉ፡፡
ለህመሙ የሚያጋልጡ ነገሮች
- የታይፎይድ በሽታ ሁሌ በሚታይባቸዉ አካባቢዎች መስራት ወይም መሄድ
- በታፎይድ ከተያዘ ሰዉ ጋር ቅርበት ያለዉ ግንኙነት/close contact/ መኖር
- የተበከለ ዉሃ መጠጣት (በተለይ ከተበከለ ቱቦ ጋር የሚገናኝ ከሆነ)
- የተበከሉ ምግቦችን መመገብ ናቸዉ፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ህመሙን ለመፈወስ ብቸኛዉ መንገድ ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መዉሰድ ስለሚያስፈልግ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
የቤት ዉስጥ ህክምና
- ፈሳሽ በበቂ መጠን መዉሰድ/መጠጣት፡- ይህ በትኩሳት ምክንያት ሊከሰት የሚችለዉንየሰዉነት ፈሳሽ እጥረትን ሊያስቀር ስለሚችል ነዉ፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ/ከመጠን ያለፈ የፈሳሽ እጥረት ካለዎ በደም ስር ፈሳሽ መዉሰድ አአስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ወደ ህክምና ድርጅት መሄድ ያስፈልጋል፡፡
ታይፎይድን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የእጅ ንፅህናዎን መጠበቅ፡-
-
ታይፎይድ ኢንፌክሽንን ለመከላከል አስተማማኙ መንገድእጅን በዉሃና በሳሙና መታጠብ ነዉ፡፡ ምግብ ከመመገብዎና ከማዘጋጀትዎ በፊት እንዲሁም መፀዳጃ ቤት ተጠቅመዉ ከወጡ በኃላ እጅን በደንብ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ ዉሃ ማግኘት በማይችሉበት ወቅት አልኮሆል ያላቸዉ የእጅ ማፅጃዎች/ሃንድ ሳኒታዘሮች/ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
ያልታከመ ዉሃ ያለመጠጣት፡-
- ታፎይድ የሚዛመተዉ በተበከለ ዉሃ ስለሆነ መጠጣት የሚያስፈልገዉ ፈልቶ የቀዘቀዘ ዉሃ አሊያም የታሸገ ዉሃ ቢሆን ይመከራል፡፡
ጥሬ የሆኑ አታክልትና ፍራፍሬዎችን በደንብ በንፅህና አጥቦ መጠቀም፡፡
- ይህን ማድረግ ካልቻሉና አታክልቱ ንፁህ በሆነ ዉሃ ያልታጠበ ከሆነ አሊያም እርግጠኛ ካልሆኑ ጥሬ አትክልትና ፈራፍሬዎችን አለመጠቀም ይበጃል፡፡
Recent Posts
- 534
- የማስታወስ ችሎታዎን ለማሻሻል የሚመከሩ 7 ምክሮች
- የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን/ Infant jaundice
- የአመት በዓል ጤናና ደህንነት ጥንቃቄ ምክሮች
- የኩላሊት ጠጠር