ለደም ግፊት የሚያጋልጡ ነገሮች

 

ለደም ግፊት ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡

• እድሜ፡-  እድሜዎ ሲጨምር የደም ግፊት እየጨመረ ይመጣል፡፡
• በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር፡- የደም ጊፊት ከቤተሰብ ሊወረስ ይችላል፡፡
• ከመጠን ያለፈ ዉፍረት ወይም ክብደት ካለዎ፡- ክብደትዎ በጨመረ ቁጥር ሰዉነትዎ ተጨማሪ ኦክሲጅንና ንጥረ ነገር ይፈልጋል፡፡ ይህ የደም መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርግ የግፊት መጠንም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• መደበኛ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ከሆነ፡- መደበኛ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎች ክብደታቸዉ ስለሚጨምር ለደም ጊፊት የመጋለጥ እድላቸዉ ይጨምራል፡፡
• ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ የደም ግፊትን ከመጨመሩ ባሻገር በሲጋራ ዉስጥ ያለዉ ኬሚካል የደም ስሮች ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ይህ የደም ስሮች እንዲጠቡ ስለሚያደርግ የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• ከምግብዎ ጋር ጨዉ በብዛት መጠቀም፡- በሚመገቡት ምግብ ዉስጥ ጨዉ በብዛት መጠቀም ፈሳሽ ሰዉነትዎ ዉስጥ በብዛት እንዲኖር ስለሚያደርግ የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• የፖታሲየም ይዘታቸዉ አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር፡- ፖታሲየም የሶዲየምን መጠን ለማመጣጠን ስለሚረዳ እነደ ሙዝ ያሉ ከፍ ያለ የፖታሲየም ይዘት ያላቸዉ ምግቦችን እንዲያዘወትሩ ይመከራሉ፡፡
• አልኮሆል በብዛት መጠጣት፡- አልኮሆል ልብንና የደም ስሮችን ይጎዳል፡፡ ወንዶች በየቀኑ ከሁለት ጠርሙስ ቢራ በላይና ሴቶች በየቀኑ ከአንድ ቢራ በላይ የሚጠጡ ከሆነ በደም ግፊትዎ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል፡፡ አልኮሆል የሚጠጡ ከሆነ መመጠን አለብዎ፡፡
• ጭንቀት፡- ከፍተኛ ጭንቀት የደም ግፊትን ሊጨምር ይችላል፡፡
• በምግብዎ ዉስጥ የቫይታሚን ዲ መጠን አነስተኛ መሆን፡- ምንም እንኳን የቫታሚን ዲ እጥረት የደም ግፊትን እንደሚጨምር/እንደማይጨምር ባይታወቅም የቫይታሚን ዲ እጥረት ከኩላሊት የሚመጣዉን ኢንዛየም ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለደም ግፊት ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
• የዉስጥ ደዌ ችግሮች፡- የኩላሊት፣ የስኳርና ሌሎች ችግሮች ለደም ግፊት ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡


ምንም እንኳ ደም ግፊት በአዋቂዎች ላይ በብዛት የሚከሰት ቢሆንም በህፃናት ላይም ሊከሰት ይችላል፡፡ ህፃናት ላይ የኩላሊትና የልብ ችግሮች ለደም ግፊት የሚዳርጉ ሲሆን ጥሩ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ዉስጥ የሚመደቡ ጤንነቱን ያልጠበቀ አመጋገብ፣ ዉፍረት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለመኖር ለደም ግፊት መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

Recent Posts

Comments

comments