መጥፎ የአፍ ጠረን(ሃሊቶስስ) የአፍን ንፅህና በደንብ ካለመጠበቅ የሚከሰት ችግር ቢሆንም ሌሎች የአፍና የጥርስ ንፅህና ቢጠበቅም ለህክምና አስቸጋሪ የሆኑ መንስኤዎችም አሉት፡፡ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ከማስጨነቁም በላይ የታማሚዉን ሁለንተናዊ ግንኙነት (በትዳርም ይሁን በሌሎች ግንኙነቶች፤በስራ ቦታ) ሊጎዳ ይችላል፡፡
መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡
• የአፍ ንፅህናን ያለመጠበቅ
• የድድ ህመም መኖር
• ሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በአፍና የአንጀት ክፍሎች ዉስጥ መራባት
• እንደ ካንዲዲያስስ ያሉ የፈንገስ ህመሞች መከሰት
• የሳይነስ እንፎክሽን
• መድኃኒቶች(በተለይ አፍን የሚያደርቁ መድሃኒቶች)
• ሲጋራ ማጨስ
• የተወሱ የምግብ አይነቶች(ነጭ ሽንኩርት፤ሽንኩርት፤ሰርዲን፤ከፍተኛ የገንቢ ምግብ(ፕሮትን) ያላቸዉ ምግቦች)
• የምግብ ያለመፈጨት ችግርና የጉበት ችግር
• የሆድ ድርቀት
መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት ሊያዉቁ ይችላሉ?
• መጥፎ ወይም የሚመር የአፍ ጣዕም ሲሰማዎት
• በጣም የሚመከረዉ ዘዴ ግን የሚያምኑት ሰዉ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደአለዎትና እንደሌለዎት እዉነቱን እንዲነግሮት መጠየቅ ናቸዉ፡፡
መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች/ምክሮች
• ምግብ ከተመገቡ በኃላ ጥርስዎትን መታጠብ(መቦረሽ)
• ቢያንስ በቀን አንዴ በጥርስ መካከል ያሉትን የምግብ ተርፍራፊ በጥርስ መጎርጎርያ ወይም ፍሎስ ማዉጣት
• ምላስዎትን መቦረሽ
• አርትፊሽል ጥርስ ወይም ድድ ካለዎት ማፅዳት
• የአፍ ድርቀትን መከላከል፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፤ዉሃ በብዛት መጠጣት(ቡና፣ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የአፍን መድረቅ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ስለዚህ አያዘወትሩ)፤ማስቲካ ማኘክ ወይም ከረሜላ መምጠጥ
Recent Posts
- ከምግብ ዉጪ የደም ስኳር መጠንዎን ሊጨምሩ/ሊያዛቡ የሚችሉ ነገሮች
- የሴቶች የወሲብ ችግር
- የእትብት እንክብካቤ፡-
- የአይን አለርጂ/ Allergic conjunctivitis
- እንቅርት/ Goiter