የሴቶች የወሲብ ችግር

 

ብዙ ሴቶች በግብረስጋ ግንኙነታቸዉ ላይ የሆነ ጊዜ ችግር ሊገጥማቸዉ ይችላል፡፡ የሴቶች የወሲብ ችግር በህይወት ዘመናቸዉ በየትኛዉም ጊዜ ሊከሰት የሚችል ሲሆን የችግሩ ምልክቶች እንደሚከሰተዉ የግብረስጋ ግንኙነት ችግር አይነቶች ሊለያይ ይችላል፡፡

አነዚህም ችግሮች

· የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ
· የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መነቃቃት ችግር/ Sexual arousal disorder
· የእርካታ ችግርና
· በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም መኖር ናቸዉ፡፡

የወሲብ ችግር ምክንያቶች

· ስነልቦናዊና ማህበራዊ፡- ህክምና ያልተደረገለት ጭንቀት/ድብርት ና ለረጅም ጊዜ የቆየ መጨናነቅ ወይም ከዚህ በፊት ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የደረሰባት ችግር (መደፈር) ከነበረ ለችግሩ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
· የሆርሞን መለዋወጥ፡-ከማረጥ ጋር በተያያዘ በሰዉነትዎ ዉስጥ የሚገኘዉ ኢስትሮጂን ሆርሞን መጠን መቀነስ በብልትዎ አካባቢ የሚገኙ አካላት ላይ ለዉጥ እንዲከሰት ስለሚያደርግ
· አካላዊ ችግሮች፡- ማንኛዉም የዉስጥ ደዌ ችግሮች የግብረስጋ ግንኙነት ችግሮችን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡

 

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች

የሴቶች የወሲብ ችግሮች ብዙ አይነት የህመም መገለጫ፣ የህመም ምክንያቶችና ህክምናዎች አላቸዉ፡፡ ስለሆነም ለግብረስጋ ግንኙነት ችግሮችዎ መፍትሄ ለማግኘት የህክምና ባለሙያዎን ማነጋገር ያስፈልጋል፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና፡- የግብረስጋ ግንኙነት ጤንነትዎን ለመገንባት የሚከተሉትን ጤነኛ ባህሪያቶችን ማዳበር ያስፈልጋል፡፡
· ከመጠን ያለፈ አልኮሆል ያለመዉሰድ፡- ከመጠን ያለፈ አልኮሆል መዉሰድ የግብረስጋ ግንኙነት ተነሳሽነትዎን ይቀንሳል፡፡
· ሲጋራ ያለማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ በሰዉነትዎ ዉስጥ የሚደረገዉን የደም ዝዉዉርን ይቀንሳል፡፡ ስለሆንም ወደብልትዎ የሚሄደዉን የደም ዝዉዉር ስለሚቀንሰዉ የግብረ ስጋ ግንኙነት መነቃቃትንና እርካታን ይቀንሳል፡፡
· የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘዉተር፡- ተከታታይነት ያለዉ የኤሮቢክስ እንቅስቃሴ ስሜትዎን ስለሚቀሰቅስና ስለራስዎ የሰዉነት አቋምልከታ እንዲቀየር ስለሚያደርግ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
ሰዉነትን ለማፍታታተትና ዘና ለማለት ጊዜ መስጠት፡- እንዴት ዉጥረትን መቀነስና ሰዉነትዎን ዘና እንደሚያደርጉ ማወቅ፡፡ ዘና ሲሉ በግብረስጋ ግንኙነት ልምድዎ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ከመርዳቱም በላይ የተሳካ የግብረ ስጋ ግንኙነት መነቃቃትና እርካታ እንዲኖርዎ ያግዛል፡፡

Recent Posts

Comments

comments