የአይን አለርጂ የሚከሰተው አይንዎ ላይ የመቆጥቆጥ ስሜት እንዲሁም የመቅላት ባህሪይ ሲከት ሲሆን ይህ ችግር ህፃናትንና አዋቂዎችን ያጠቃል፡፡ዋነኛዎቹ የህመሙ መገለጫዎች የአይን መቅላትና ከአይን ፈሳሽ ሲኖር መኖር ናቸዉ፡፡
የህመሙ መንስኤ፡-
የአይን አለርጂ የሚከሰተዉ አለርጂዉ እንዲከሰት የሚያደርጉ አለርጂኖች በንፋስ ምክንያት ወደ አይንዎ በሚገባበት ወቅት ነዉ፡፡የህመሙ ምልክቶች አለርጂዉን በሚያመጡ/አለርጂኑን ተከትለዉ የሚከሰቱ ሲሆን በድንገት የሚጀምሩ፣ወቅትን ተከትለዉ አሊያም አመቱን በሙሉ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
የህመሙ ምልክቶች፡-
በብዛት ከሚታዩት የአይን አለርጂ ምልክቶች ዉስጥ የአይን መቅላት፣ዉሃ የመሰለ የአይን ፈሳሽና ሁለቱንም አይን ማሳከክ ናቸዉ፡፡ሌሎቹ የህመም ምልክቶች ብርሃን ሲያዩ ማቃጠልና የአይን ቆብ እብጠት መከሰት ናቸዉ፡፡ችግሩ ብዙዉን ጊዜ ሁለቱንም አይን የሚያጠቃ ቢሆንም ህመሙ በአንደኛዉ አይን ሊብስ ይችላል፡፡ ዐይንን ማሸት የህመሙ ምልክቶች እንዲባባሱ ያደርጋል፡፡
Recent Posts
- እንቅርት/ Goiter
- ልጅዎ የሦስት አመት እድሜ ሳለ
- የሚመገቡትን የጨዉ መጠን መመጠን/መቀነስ የሚገባበት ምክንያቶች
- የታለበ የእናት ወተት ምን ያህል ጊዜ ሊቆይ ይችላል?
- ያለ መድሃኒት የታችኛዉ የጀርባ ህመምን ለማቃለል/ለማከም የሚረዱ 4 መንገዶች