እንቅርት/ Goiter

12419291_620615218102702_8875992845249531341_o

 

እንቅርት የታይሮይድ እጢ በሚያብጥበት ወቅት የሚከሰት ህመም ነዉ፡፡የታይሮይድ እጢ በአንገት ላይ በፊትለፊት በኩል የሚገኝ አካል ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

ሁሉም የእንቅርት ችግሮች የህመም ምልክቶች ላይኖራቸዉ ይችላል፡፡የህመም ምልክቶች ከታዩ ደግሞ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡፡
·የሚታይ የአንገት ላይ እብጠት
·ጉሮሮዎ ላይ የመወጠር ስሜት መኖር
·ማሳል
·የድምፅ መጎርነን
·የመዋጥ ችግር
·የመተንፈስ ችግር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡


ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች


·በምግብዎ ዉስጥ የአዮዲን ንጥረነገር ከሌለ፡-አዮዲን በበቂ መጠን በማይኖርበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እና በአዮዲን የበለጸጉ ምግቦችን ማግኘት በማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡
·ሴት መሆን፡- ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለታይሮይድ እጢ ችግሮች የተጋለጡ ስለሆኑ ከወንዶች ይልቅ ለእንቅርት የመጋለጥ እድላቸዉ የሰፋ ነዉ፡፡
·እድሜ፡- እድሜ እየጨመረ በመጣ ቁጥር እንቅርት የመከሰቱ እድል እየጨመረ ይመጣል፡፡
·መሰል ችግር በቤሰብ ዉስጥ ከነበረ
·እርግዝናና ማረጥ፡- መክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ እንቅርት በነፍሰጡሮችና ባረጡ ሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል፡፡
·መድሃኒቶች፡- የበሽታ መከላከልን የሚቀንሱ መድሃኒቶች፣የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒቶችና ለልብ ችግር የሚሰጠዉ እንደ አሚዳሮን እንዲሁም ለስነአዕምሮ ችግር የሚሰጠዉ ሊቲየም እንቅርትን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡
· ለጨረር መጋለጥ


ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች፡-


የእንቅርት ህክምና እንደ እንቅርቱ መጠን፣የህመም ምልክትና እንቅርቱ እንዲከሰት እንዳደረገዉ መሰረታዊ ችግር ሊለያይ ይችላል፡፡ ስለሆን የህክምና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ዘዴዎች ሊከተሉ ይችላሉ፡፡
·በቅርበት መከታተል፡- የእንቅርትዎ መጠን አነስተኛ ከሆነ፣ህመም ከሌለዉና ስራዋን በአግባቡ እየተወጣች ከሆነ የህክምና ባለሙያዎ መከታተሉን ብቻ ሊመርጡ ይችላሉ፡፡
·መድሃኒቶች፡- የታይሮይድ ዕጢዉ የሚያመነጨዉ ሆርሞን መጠን ማነስ/መብዛት ካለዉ መድሃኒቶች ሊጀመርልዎ ይችላል፡፡
·የቀዶ ጥገና
·ራዲዮአክቲቭ አዮዲን የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

Recent Posts

Comments

comments

2 Comments on “እንቅርት/ Goiter

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *