የሳይነስ ህመም

sinus

 

 

 

 

 

 

 

የሳይነስ ችግር በብዛት የሚመጣዉ በጉንፋን ምክንያት ነዉ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ በአለርጂዎች ይመጣል፡፡

የሳይነስ የህመም ምልክቶች

• ከአፍንጫዎ ወይም ከጉሮሮረዎ በስተጀርነባ ወፍራም፣ ቢጫ ወይም አረንጓዴ መልክ ያለዉ ፈሳሽ መዉጣት
• በአፍንጫ መዘጋት ወይም መጠቅጠቅ ምክንያት በአፍንጫ ለመተንፈስ መቸገር
• በአይንዎ ዙሪያ፣በጉንጭዎ፣ በአፍንጫዎና ግንባርዎ ላይ እብጠትና ህመም መከሰት
• ማታ ማታ የሚባባስ ሳል መከሰት
• የራስ ምታት

የቤት ዉስጥ ህክምናና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ

• በቂ እረፍት ማድረግ
• ፈሳሽ በበቂ መጠን መዉሰድ
• ሲተኙ ትራስዎን ከፍ ማድረግ

የሚከተሉ ነገሮችን በመተግበር ህመሙ እንዳይመጣብዎ መከላከል

• የላይኛዉ መተንፈሻ ፈካላት እንፌክሽንን መከላከል
• አለርጂ ካለዎ ህክምና ማድረግ
• የተበከለ አየር ካለ በተቻለዎ መጠን ተጋላጭነትዎን መቀነስ ወይም ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ መተዉ ናቸዉ፡፡

Recent Posts

Comments

comments