Month: February 2016

18815668_l

የታለበ የእናት ወተት ምን ያህል ጊዜ ማቆየት እንደሚችሉ የሚወሰነዉ የሚያስቀምጡበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ለጤነኛ ህፃናት የሚከተለዉን መመሪያ መከተል ይችላሉ፡፡

በቤት ሙቀት ማስቀመጥ/ Room temperature፡-

በቅርቡ የታለበ/ትኩስ/ የእናት ወተት ፍሪጅ ዉስጥ ሳይገባ/በቤት ሙቀት ካስቀመጥነዉ እስከ 6 ሰዓታት ድረስ መቆየት ይችላል፡፡ ነገር ግን የክፍሉ ሙቀት ከፍተኛ ከሆነ መቀመጥ ያለበት እስከ 4 ሰዓታት ነዉ፡፡

 

በፍሪጅ ዉስጥ፡-

ትኩስ የታለበ የእናት ወተት በፍሪጅ ዉስጥ በንጽህና ከተቀመጠ እስከ 5 ቀናት መቆየት ይችላል፡፡ ነገርግን በፍሪጅ ዉስጥ የተቀመጠ የእናት ወተትን በ 3 ቀናት ዉስጥ ቢጠቀሙት ይመረጣል፡፡

 

ዲፕ ፊሪዘር(የበረዶ ሰንሰለት)/Deep freezer፡-

ትኩስ የታለበ የእናት ወተት በዲፕ ፈሪዘር ዉስጥ እስከ 12 ወራት ድረስ ሊቀመጥ/ማስቀመጥ ይችላል፡፡ ነገርግን በዲፕ ፍሪዘር ዉስጥ የተቀመጠ የእናት ወተትን በ 6 ወራት ዉስጥ ቢጠቀሙት ይመረጣል፡፡

 

መገንዘብ የሚገባዎ ነገር ቢኖር የእናት ጡት ወተት ለረጅም ጊዜ ታልቦ በቆየ ቁጥር/በፍሪጅ ዉስጥም ይሁን በዲፕ ፍሪዘር ዉስጥ/ በዉስጡ ያለዉን ቫይታሚን ሲ እያጣ ሊመጣ ይመጣል፡፡እናት ጡት ወተት መልክ እናትየዋ እንደምትመገበዉ የምግብ አይነት ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ሌለኛዉ ታልቦ የቆየዉ የእናት ወተት ትኪስ ከታለበዉ ወተት ጋር ሲነፃፀር በመልክና በይዘቱ ሊለያይ ይችላል፡፡ ይህም ቢሆን ህፃኑ ላይ የሚያመጣዉ ጉዳት ስለሌለዉ መመገብ ይችላሉ፡፡ ታልቦና በፍሪጅ ዉስጥ የቆየዉን ወተት ልጅዎ አልጠጥም ካለዎ የቆይታዉን ጊዜ መቀነስ ይችላሉ፡፡

Recent Posts

backpain

እንደ የአሜሪካ ናሽናል የጤና ኢንስቲትዩት መረጃ ከ10 ሰዎች ዉስጥ 8ቱ በህይወታቸዉ ዘመን የሆነ ጊዜ የጀርባ ህመም ሊያማቸዉ እንደሚችል ይገልፃል፡፡ ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንክብሎችን መዉሰድ ለጊዜዉ ህመምዎን ሊያስታግስ ቢችልም ዘላቂነት ያለዉ የጀርባ ጤንነት እንዲኖርዎ የሚከተሉትን ምክሮች /ነገሮች ሊተገብሩ ይችላሉ፡፡

  1. ዮጋ፡- ዮጋ በመስራትና የጀርባ ህመምዎን መቀነስ ይቻል፡፡
  2. ማሳጅ፡- መጨናነቅ የጀርባ ህመም እንዲመጣ የሚያደርግ ሲሆን ይህን ለመቀነስ ማሳጅ ማድረግ ይመከራል
  3. የደረቅ መርፌ ህክምና፡- መርፌዉ ሊያስፈራዎ አይገባም፡፡ይህ የቻይና የደረቅ መርፌ ህክምና ዘመናትን የተሸገረ ሲሆን መርፌዉን በተወሰነ የሰዉነት ክፍል በመዉጋት የሚሰራ ነዉ፡፡በጥናቶች እንደተረጋገጠዉ ይህ የህክምና አይነት እንደ ዘመናዊ የህመም ማስታገሻ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከህመሙ የመፈወስ ብቃት አለዉ፡፡
  4. ወክ ማድረግ፡- አንድ ቦታ ለረጅም ጊዜ መቀመጥ ወደጀርባ አጥንትዎ ዲስክ የሚሄደዉን የደም ዝዉዉር ስለሚቀንስ መጨናነቅን ያመጣል፡፡ስለሆነም ህመሙን ለመቀነስ በየቀኑ ወክ ማድረግ ይመከራል፡፡ለረጅም ሰዓት የሚቀመጡ ከሆነ ለተወሰነ ጊዜ ከተቀመጡበት ቦታ እየተነሱ መንቀሳቀስ ህመምዎን ለመቀነስ ይረዳዎታል፡፡

ይህን ፅሁፍ ከወደዱ ለተመሳሳይ አስተማሪ ፅሁፎች ከዚህ በታች መርጠው ያንብቡ።

Recent Posts

sinus

 

 

 

 

 

 

 

የሳይነስ ችግር በብዛት የሚመጣዉ በጉንፋን ምክንያት ነዉ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ በአለርጂዎች ይመጣል፡፡

የሳይነስ የህመም ምልክቶች

• ከአፍንጫዎ ወይም ከጉሮሮረዎ በስተጀርነባ ወፍራም፣ ቢጫ ወይም አረንጓዴ መልክ ያለዉ ፈሳሽ መዉጣት
• በአፍንጫ መዘጋት ወይም መጠቅጠቅ ምክንያት በአፍንጫ ለመተንፈስ መቸገር
• በአይንዎ ዙሪያ፣በጉንጭዎ፣ በአፍንጫዎና ግንባርዎ ላይ እብጠትና ህመም መከሰት
• ማታ ማታ የሚባባስ ሳል መከሰት
• የራስ ምታት

የቤት ዉስጥ ህክምናና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ

• በቂ እረፍት ማድረግ
• ፈሳሽ በበቂ መጠን መዉሰድ
• ሲተኙ ትራስዎን ከፍ ማድረግ

የሚከተሉ ነገሮችን በመተግበር ህመሙ እንዳይመጣብዎ መከላከል

• የላይኛዉ መተንፈሻ ፈካላት እንፌክሽንን መከላከል
• አለርጂ ካለዎ ህክምና ማድረግ
• የተበከለ አየር ካለ በተቻለዎ መጠን ተጋላጭነትዎን መቀነስ ወይም ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ መተዉ ናቸዉ፡፡

Recent Posts

zikra

ዚካ ቫይረስ በወባ ትንኝ የሚተላለፍ የቫይረስ አይነት ነዉ፡፡ ብዙዎቹ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ምንም የህመሙ ምልክት ባያሳዩም ጥቂት በሆኑ ሰዎች ላይ ህመሙ ትኩሳት፣የቆዳ ላይ ሽፍታና የጡንቻ ላይ ህመም ይታይባቸዋል፡፡ ሌሎቹ የህመም ምልክቶች ደግሞ የራስ ምታት፣የአይን መቅላት (ኮንጀክትቫይትስ) ና በአጠቃላይ ሰዉነት ላይ የጤነኝነት ስሜት ያለመሰማት ናቸዉ፡፡ የዚካ ቫይረስ የህመም ምልክቶች በዚካ ቫይረስ በተያዘች የወባ ትንኝ በተነከሱ ከሁለት እስከ ሰባት ቀናት ባሉት ጊዜያት ዉስጥ መታየት ይጀምራል፡፡

(more…)

Influenza

እንፉሌንዛ በኢንፉሉዌንዛ ቫይረስ አማካይነት የሚተላለፍና የመተንፈሻ አካላትን ( አፍንጫ ቶኒስል፣ ሳንባ) የሚያጠቃ የህመም አይነት ነዉ፡፡ ሲዲሲ እንደሚለዉ ከሆነ ከ6 ወርና ከዚያ በላይ የሆኑ እድሜ ያለዉ ማንኛዉም ሰዉ በየዓመቱ የእንፉሉዌንዛ ቫይረስ ክትባት ማግኘት አለበት፡፡ በየዓመቱ የሚሰጡት ክትባቶች ሶስት ወይም አራት የእንፉሉዌንዛ አይነቶችን የሚከላከል ሲሆን ክትባቱ በመርፌ የሚወጋ ወይም በስፕሬይ/በሚነፋ መልክ ሊገኝ ይችላል፡፡ ክትባቱ መቶ በመቶ የመከላከል ብቃት ስለሌለዉ ህመሙ ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ የሚከተሉትን መንገዶች መተግበር ያስፈልጋል፡፡

Recent Posts