ሕፃናት በዚህ እድሜ ምን ነገሮችን ሊተገብሩ ይችላሉ?
ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional
• ሌሎች/ ቤተሰቦቻዉ ወይም ታላላቅ ልጆች የሚሉትን ነገሮች መኮረጅ መቻል
• ከሌሎች ልጆች ጋር ሲሆኑ መደሰት መቻል
• እራሳቸዉን መቻል/ሌሎችን ያለመፈለግ
• ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወት መቻል
ቋንቋ /መግባባት (Language/Communication)
• ነገሮች/እቃዎች ስማቸዉ ሲጠራ ማመልከት መቻል
• የሚያዉቁትን ሰዎች ስምና የተወሰኑ የሰዉነታቸዉን ክፍሎች ማወቅ መቻል
• ባለ ሁለት እስከ አራት ቃላትን በመጠቀም አረፍተነገር መናገር/መስራት
• ቀለል ያሉ ትእዛዛትን መከተል መቻል
አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና ችግርን መፍታት መቻል)
• መጫወቻ/ ሌላም ነገር ከሁለትና ከዚያ በላይ በሆነ ነገር ስር ቢደበቅም ከተደበቀበት ቦታ ፈልጎ ማዉጣት መቻል
• አራትና ከዚያን በላይ የሆነ ደረጃ ወደ ላይ መጫወቻዉን አንዱን ባንዱ ላይ መደርደር መቻል
• አንደኛዉን እጁን ከሌለኛዉ በላይ መጠቀም መቻል
• ባለሁለት ደረጃ ትዕዛዞችን ተቀብሎ መተግበር መቻል፤ ለምሳሌ ጫማህን አንሳዉና እዚህ /እዚያ ቦታ አስቀምጠዉ ሲባል ማድረግ መቻል
• በስዕል ላይ የሚያያቸዉን ነገሮች ስም መጥራት መቻል ( ድመት፣ዉሻ፣ ወፍ)
እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development
• ኳስ መምታት/መለጋት መቻል
• መሮጥ መቻል
• ያለእርዳታ እቃ ላይ መዉጣትና መዉረድ መቻል
• ተይዞ ወደ ደረጃ ዉጣትና መዉረድ መቻል
• ከጭንቅላቱ/ከራሱ በላይ ኳስን መወርወር መቻል
• ቀጥታ መስመርናና ክብን መሳል/ኮፒ ማድረግ መቻል ናቸዉ፡፡
Your Comment
የኔ ልጅ በጣም ፈጣን ነው ማንኛውም ነገር ማድረግ ኣያቅተውም ኣሁን እድሜው 10 ነው ት/ት ላይ ድክምት ኣለው። 3ኛ ክፍል ሲሆን ጨዋታ ብጣም ይወዳል። ብዙ ኣጋዥ ነገሮች ማለት ቤት ውስጥ ተቀጥረሎት ነበር ግን ለውጥ የለም ቶሎ ይረሳል ምን ይሻለኛል መላ በሉኝ ስልኬ 0914314785። ነው።