የቅድመ ወሊድ ክትትል

 pregtestfinal

 

 

 

 

 

 

የቅድመ ወሊድ ክትትል

ማንኛዋም ነፍሰጡር እናት ነፍሰጡር መሆንዋን ካወቀችበት ጊዜ አንስቶ የቅድመ ወሊድ ህክምና ክትትል መጀመር አለባት/ይጠበቅባታል፡፡ የቅድመወሊድ ክትትል ለነፍሰጡር እናቶችና ቤተሰቦቻቸዉ ስለጤናማ እርግዝና፣ወሊድና የድህረወሊድ ክትትል በተለይ ስለጨቅላ ህፃን እንክብካቤ፣ ስለጡት ማጥባትና ስለወደፊቱ የእርግዝና ሁኔታ መረጃና ምክር ለመስጠት ይረዳል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት እንዲሁም የኛ ሃገር የቅድመወሊድ መመሪያ እንድንከተል የሚያዘዉ አንዲት እናት ነፍሰጡር መሆንዋን ካወቀችበት ጊዜ አንስቶ እስክትወልድ ድረስ 4 ጊዜ የቅድመወከሊድ ክትትል ማድረግ ይገባታል፡፡ይህ ፎከስድ አንቲናታል ኬር ይባላል፡፡

 

የመጀመሪያዉ ክትትል (ከ8 እስከ 12 ሳምንታት ዉስጥ

 

• እርግዝናዉን ማረጋገጥና የሚወለድበትን ቀን መቀመር(EXPECTED DATE OF DELIVERY)
• የትኛዉ የእርግዝና ክትትል ዘዴ እንደሚያስፈልግዎ ማወቅ (መሰረታዊ ወይስ ልዩ ክትትል)
• የተለያዩ ምርመራዎች ማድረግ፣ ህክምና የሚያስፈልግዎ ከሆነ መዉሰድና የሚወሰዱ የቅድመመከላከል እርምጃዎች ካሉ ማከናወን
• አስፈላጊ ምክሮችንን ማግኘት

 

ሁለተኛዉ የክትትል ወቅት (ከ24 እስከ 26 ሳምንት ዉስጥ)

 

• የእናትና የፅንሱን የጤንነት ሁኔታ መመርመር
• ስለወሊድና ድንገተኛ ችግር ሲገጥምዎ ስለሚተገበረዉ እቅድ መነጋገር
• አስፈላጊ ምክሮችን ማግኘት

 

ሶስተኛዉ የክትትል ወቅት (32ኛዉ ሳምንት ላይ)

 

• የእናትና የፅንሱን የጤንነት ሁኔታ መመርመር
• የደም ማነስ ፣ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት አለመኖሩን ማረጋገጥ
• ስለወሊድና ድንገተኛ ችግር ሲገጥምዎ ስለሚተገበረዉ እቅድ መነጋገር
• አስፈላጊ ምክሮችንን ማግኘት

 

አራተኛዉ የእርግዝና ክትትል ወቅት (36 ሳምንት)

 

• የእናትና የፅንሱን የጤንነት ሁኔታ መመርመር
• የደም ማነስ ፣ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት አለመኖሩን ማረጋገጥ
• ስለወሊድና ድንገተኛ ችግር ሲገጥምዎ ስለሚተገበረዉ እቅድ መነጋገርና ለዉጥ ካስፈለገዉ ማድረግ
• አስፈላጊ ምክሮችን ማግኘት

Comments

comments

7 Comments on “የቅድመ ወሊድ ክትትል

  1. አመሠግናለው ዶክተር እኔ የምጠይቃችሁ ማርገዝ የሚቻለው የወረ አበባ ከመጣ በምን ያህል ግዜ ነው ማርገዝ የሚቻለው????

  2. የወር አበባየዬ እየተዛባ አስቸግሮጋል ማርገዝ እፈልጋለሁ ምንም አይነት መከላከያ አልጠቀምም ምን ትመክሩናላችሁ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *