ሕፃናት በዚህ እድሜ ምን ምን ነገሮችን ሊተገብሩ ይችላሉ?
ህፃን ልጅዎ አንድ ዓመት ሲሞላዉ የሚከተሉትን የእድገት ደረጃዎችን ሊያሟላ ይችላል፡፡
ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional
• እንግዳ ሰዉ ሲያዩ መፍራት ወይም ማፈር
• እናት ወይም አባት ሲሄዱ ማልቀስ
• መርጠዉ የሚወዷቸዉ ነገሮች ወይም ሰዎች ይኖራቸዋል
• ፍራቻን ማሳየት
• ትኩረትን ለማግኘት ድምፅን ወይም እንቅስቃሴን መድገም
• ልብስ በምናለብሳቸዉ ወቅት እጅንና እግርን በማዉጣት/በማስገባት ለመርዳት መሞከር
• እንደ አየሁሽ ያሉ ጨወታዎችን መጫት መቻል
ቋንቋ /መግባባት (Language/Communication)
• ቀላል ለሆኑ ጥያቀዎች መልስ ለመስጠት መሞከር
• ቀላል የሆኑ የአካል እንቅስቃሴዎችን ለምሳሌ እጅን በማንቀሳቀስ ቻዉ ቻዉ ማለትና አይሆንም/አይደለም ለማለት እራስን ማነቅነቅ መቻል
• ድምፅን መቀያየር መቻል( እንደ ንግግር ያለ)
• እማማ ወይም አባባ ማለት መቻል፤ እንዲሁም እንደ ኦሆ! ያሉ የግነት ቃላትን ማለት መቻል
• ቤተሰብ ሲያናግረዉ ቃላቶችን መልሶ ለማለት መሞከር
አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና ችግርን መፍታት መቻል)
• የተደበቀን ነገር በቀላሉ ፈልጎ ማግኘት
• ፎቶ/ስዕል ወይም የሆነ ነገር ስሙ ሲጠራ ትክክለኛ ወደሆነዉ ነገር ማየት/ማመልከት መቻል
• እንቅስቀቃሴን መኮረጅ መቻል
• ነገሮችን በትትክል መጠቀም መቻል፤ ለምሳሌ ፀጉር ማበጠር፣ ከኩባያ ዉስጥ መጠጣት
• ነገሮችን ማስቀመጫ ዉስጥ የመክተትና ከማስቀመጫዉ ዉስጥ ማዉጣት መቻል
• ቀላል የሆኑ ትፅዛዞችን መተግበር መቻል፤ ለምሳሌ አሻንጉሊቱን አንሳዉ ሲባል ማንሳት መቻል
እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development
• ያለእርዳታ መቀመጥ መቻል
• ስንስባቸዉ/ስንረዳቸዉ መቆም መቻል፣ እቃዎችን በመደገፍ/በመያዝ መሄድ መቻል
• ሳይያዙ የተወሰነ ርቀት ለመሄድ መቻል/መሞከር
• እራስን ችሎ መቆም መቻል/መሞከር
በዚህ እድሜ ልጅዎ የሚከተሉትን መተግበር ካልቻለ የህክምና ባለሙያዎን በወቅቱ ያማክሩ፡፡
• መዳህ ያለመቻል
• ተደግፎ መቆም ያለመቻል
• እማማ ወይም አባባ ማለት ያለመቻል
• ከዚህ በፊት ይተገብራቸዉ የነበሩ ነገሮችን መልሶ ማከናወን ያለመቻል