በእርግዝና ወቅት መመገብ የሌለብዎ ምግቦች

Preg food

 

 

 

 

 

 

 

በእርግዝናዎ ወቅት መመገብ/መዉሰድ የሌለብዎን የምግብ አይነት ማወቅ ለእርስዎና ለልጅዎ ጤናማ ምርጫ እንዲያደረጉ ያግዝዎታል፡፡

በደንብ ያልበሰለ/ጥሬ ስጋ፣ የዶሮ ዉጤቶችን(የዶሮ ስጋና እንቁላል) ያለመጠቀም

በእርግዝናዎ ወቅት ነፍሰጡር ካልሆኑት አንፃር ሲታይ በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰት የምግብ መመረዝ የመጋለጥ እድልዎ ከፍ ያለ ነዉ፡፡ ስለሆነም ከምግብ ወለድ ህመሞች እራስን ለመከላከል

  • ሁሉንም የስጋና የዶሮ ተዋፅኦዎችን ከመመገብዎ በፊት በሚገባ ማብሰል
  • እንቁላል ነጩና አስኳሉ በደንብ እስኪጠነክሩ ድረስ በደንብ መቀቀል፡- ጥሬ እንቁላል አደገኛ በሆኑ ባክቴሪያዎች ሊበከል ይችላል፡፡ ስለሆነም ከጥሬ ወይም በደንብ ካልበሰ እንቁላል የተዘጋጁ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

ፓስቸራይዝድ ያልተደረጉ ምግቦችን ያለመመገብ

ብዙዎቹ መጠናኛ ስብ የያዙ እንደ ክሬም የወጣለት ወተትና ማንኛዉም ጃስቸራይዝድ ያልተደረገ ወተት የያዙ ምግቦችን መመገብ ለምግብ ወለድ ህመሞች ሊዳርግዎ ይችላል፡

በደንብ ያልታጠቡ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ያለመጠቀም

ጤናዎን ሊጎዱ ከሚችሉ ባክቴሪዎች እራስን ለመከላከል በደንብ ያልታጠቡ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ያለመመገብ

ከመጠን ያለፈ ካፊን/ caffeine/ ያለመጠቀም

ካፊን የእንግዴ ልጁን በማለፍ በማህፀንዎ ዉስጥ ያለዉን ፅንስ ሊጎዳ ይችላል፡፡ ምንም እንኳ ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልግም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከመጠን ያለፈ ካፊን ያላቸዉን ነገሮች መጠቀም ለዉርጃ የመጋለጥ እድሉን ሊጨምር እንደሚችል ያሳያል፡፡

መጠጥ ያለመጠጣት

ምንም እንኳ ትንሽ አልኮሆል መጠጣት ፅንሱን ይጎዳል ተብሉ ባይታመንም፤ ምን ያህል አልኮሆል ቢወሰድ ፅንሱን እንደሚጎዳና እንደማይጎዳ በጥናት የተረገገጠ ነገር የለም ጽንሱን ሊጎዳ የሚችል ትንሹ የአልኮሆል መጠን ምን ያህል እንደሆነ በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም/የሚታወቅ ነገር የለም)፡፡ ስለሆነም የሚሻለዉ በእርግዝናዎ ወቅት ምንም አይነት አልኮሆል ከመዉሰድ/ከመጠጣት መቆጠብ ነዉ፡፡ አልኮሆል የሚጠጡ እናቶች ለዉርጃና ፅንሱ በሆዳቸዉ ዉስጥ ሞቶ የመወለድ እድላቸዉ በጣም ከፍተኛ ነዉ፡፡ በእርግዝና ወቅት ከመጠን ያለፈ አልኮሆል መዉሰድ ፅንሱን ለፌታል አልኮሆል ሲንድረም የማጋለጥ እድሉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡ ይህ መጠን በፅንሱ የፊትና ልብ ላይ ተፈጥሮያዊ ችግሮችና ለአእምሮ ዘገምተኝነት ይዳርገዋል፡፡ ሌለኛዉ ነፍሰጡር እናቶች መካከለኛ አልኮሆል ጠጪ ቢሆኑም እንኳአልኮሆሉ በፅንሱ የአእምሮ እድገት ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል፡፡

ጎጂ ከሆኑ ባክቴሪያና ቫይረሶች እራስን ለመከላከል

  • ጥሬ አሳ ያለመመገብ
  • በፍሪጅ የቆየ ወይም በደንብ ያልበሰለ የባህር ምግቦችን/ seafood. ያለመመገብ
  • የባህር ምግቦችንነ በደንብ ማብሰል

 

Recent Posts

Comments

comments